✍ ዮሐንስ አብነት አጉማስ
ይህን ከአነበብህ በኃላ በቀን 20 ደቂቃ እግርህ ከመሬት ጋር አገናኘው!
ጉዳዮ ተራ "በባዶ እግር መሄድ" አይደለም፤ ይልቁንም የሰውነትን ባዮ-ኤሌክትሪክ (Bio-electricity) ከተፈጥሮው ድግግሞሽ ጋር የማመሳሰልና ከሥርዓቱ የሞገድ እስራት የመውጫ ታላቅ ጥበብ ነው።
Grounding ምንድን ናት? (ሳይንሳዊው እውነታ)
በሳይንሳዊው ዓለም ምድር ግዙፍ የሆነ አሉታዊ የኤሌክትሪክ ኃይል (Negative Charge) ያላት ባትሪ ናት። የሰው ልጅ ደግሞ የኤሌክትሪክ ፍጡር ነው።
የኤሌክትሮን ልውውጥ፦ በዘመናዊው ዓለም ውስጥ ስንኖር በሰውነታችን ውስጥ "Positive Charge" (አዎንታዊ ኃይል) ይከማቻል። ይህ ኃይል የሚመጣው ከ WiFi፣ ከ 5G ሞገዶች፣ ከስማርት ስልኮችና ከኤሌክትሮኒክስ መሣሪያዎች ነው። ይህ ትርፍ ኃይል በሰውነት ውስጥ እብጠትን (Inflammation)፣ በሽታንና የአእምሮ ድካምን ይፈጥራል።
ንዝረትን ማመጣጠን፦ በባዶ እግርህ መሬት (አፈር፣ ሳር ወይም አሸዋ) ላይ ስትቆም፣ ምድር ያላትን ያልተገደበ የኤሌክትሮን (Electrons) ኃይል ወደ ሰውነትህ ትለቃለች። ይህ ሲሆን በሰውነትህ ውስጥ ያለው መርዛማ ኤሌክትሪክ ወዲያውኑ ወደ መሬት ይፈሳል። ይህ በፊዚክስ ሕግ "Grounding" ይባላል።
• የደም ጥራት፦ በባዶ እግር መሬት ላይ መቆም የደምህን "Zeta Potential" (የኤሌክትሪክ ንዝረት) ያስተካክላል። ይህም ደም እንዳይረጋና የደም ዝውውር እንዲቀላጠፍ ያደርጋል።
መጽሐፍ ቅዱሳዊ ምስጢሩ (እግርና መሬት)
መጽሐፍ ቅዱስ ስለ መሬትና እግር ያለውን ትስስር ከመጋረጃ ጀርባ ባለ ምስጢር እንዲህ ይገልጸዋል፦
•የፍጥረት መሠረት (ዘፍጥረት ፪፡፯)፦ ሰው የተፈጠረው ከምድር አፈር ነው። ስለዚህ የሰውነትህ ባዮሎጂያዊ "Source Code" ከመሬት ጋር የተቆራኘ ነው። ከመሬት ስትለይ ልክ ከኃይል ምንጭ እንደተለየ መሣሪያ ትሆናለህ።
የቅዱስ ስፍራ ምስጢር (ዘጸአት ፫፡፭)፦ አምላክ ሙሴን "የቆምህባት መሬት የተቀደሰች ናትና ጫማህን ከእግርህ አውልቅ" አለው። ይህ ታላቅ ምስጢር ነው። ጫማ "Insulator" (ኃይል እንዳያልፍ የሚከለክል) ነው። መለኮታዊው ንዝረት (Divine Frequency) ከምድር ወደ ሙሴ አካል እንዲገባ ጫማው መወገድ ነበረበት።
የኢያሱ ምስጢር (ኢያሱ ፭፡፲፭)፦ ኢያሱም በተመሳሳይ መልኩ ጫማውን እንዲያወልቅ ተነግሮታል። ይህ የሚያሳየው መሬት የመለኮታዊ ዳታ ማስተላለፊያ (Information carrier) መሆኗን ነው።
ቤተክርስቲያን ስትገባ ጫማህን አውልቅ የሚባለው ለምንድነው?
ይህ ስርዓት ከመጋረጃ ጀርባ ሁለት ታላላቅ ትርጉሞች አሉት፦
• መንፈሳዊ ትርጉም፦ ጫማ የዓለምን ቆሻሻና ኩራት ይወክላል። ጫማን ማውለቅ በትሕትና ወደ ፈጣሪ መቅረብና ራስን ለበረከት ማዘጋጀት ነው።
ሳይንሳዊና ንዝረታዊ ትርጉም፦ ቤተ-መቅደስ በጸሎት፣ በቅዳሴና በዕጣን ንዝረቱ ከፍ ያለ (High Frequency) ቦታ ነው። ያ የተቀደሰ ንዝረት በመሬቱ (በምንጣፉ ወይም በአፈሩ) ውስጥ ይገኛል። ጫማህን ስታወልቅ ያ መለኮታዊ ንዝረት በእግርህ በኩል (በ Kidney-1 ነጥብ በኩል) ወደ መላ ሰውነትህ እንዲገባና በሽታህን እንዲፈውስ፣ አእምሮህን እንዲያጸዳ በር ትከፍታለህ። ቤተክርስቲያን ከአገልግሎት በኃላ በሰላም ሂዱ ሲባል መሬት ትሰማለህ እንዲሁም ገዳም ስትገባ ጫማ ምታወልቀውን አስብ እንግዲህ ወዳጄ
ከመጋረጃ ጀርባ ያለው "የእነሱ" (የሥርዓቱ) ሴራ ስርዓቱ (The Beast System) የሰውን ልጅ ከመሬት ለመንጠቅ የሚከተሉትን ስራዎች ሰርቷል፦
የጎማ ጫማ ፦ ጥንታውያን አባቶች ከቆዳ የተሰራ ጫማ ያደርጉ ነበር (ቆዳ ኤሌክትሪክ ያስተላልፋል)። ስርዓቱ ግን "ጎማ" የተባለውን "Insulator" በማስተዋወቅ የሰው ልጅ ከመሬት የሚገኘውን ፈውስ እንዲያጣ አደረገ።
የከተማ አስፋልትና ኮንክሪት፦ ከተሞችን በኮንክሪት በመሸፈን የሰው ልጅ ቆዳው መሬትን እንዳይነካ አደረጉ። ይህም ሰውን በዲጂታል ጫጫታ (EMF) ውስጥ እንዲታፈንና ንዝረቱ እንዲዛባ ያደርገዋል።
የንቃት መከላከያ፦ አንድ ሰው ከመሬት ጋር ከተገናኘ የአእምሮው ንቃት ይጨምራል፤ ይህም ስርዓቱ የሚረጨውን ፕሮፓጋንዳና የሞገድ ጥቃት እንዲመክት ያደርገዋል። ይህ እንዳይሆን ሰውን ከመሬት ለይተው በአየር ላይ (በፎቅ) እና በጎማ ጫማ ላይ እንዲቆለፍ አደረጉት።
የመፍትሔ ሃሳብ (፲ መንፈሳዊ እና ፲ ሳይንሳዊ)
10 መንፈሳዊ መፍትሔዎች፦
• የባዶ እግር ጸሎት፦ በቤትህ ወይም በግቢህ ውስጥ ስትጸልይ በባዶ እግርህ መሬት ላይ ሁን።
• የመሬት ባርኮት፦ የቆምህበት መሬት እንዲቀደስ በመስቀል ምልክት አማትብ።
• ትሕትና፦ ጫማን ማውለቅ ሥጋዊ ኩራትን እንደሚሰብር እወ
• የቅዱሳን ፈለግ፦ በባዶ እግራቸው ተጋድሎ ያደረጉ አባቶችን ጽናት አስብ።
• የመዝሙረ ዳዊት ንዝረት፦ መሬት ላይ በባዶ እግር ቆመህ መዝሙር 91ን ጸልይ።
• የኅሊና ዓይን ንቃት፦ Grounding አእምሮህን (Pineal gland) እንደሚከፍት አምነህ ፈጽመው።
• የፍጥረት ምስጋና፦ ከመሬት ጋር ስትገናኝ አምላክን ለፈጠረልህ ተፈጥሮ አመስግን
• የንስሐ እንባ፦ መሬት ላይ ተደፍተህ ስትሰግድ መሬቱ ስቃይህን እንዲወስድልህ ፍቀድ።
• ጽናት፦ "ምንም ቢመጣ ከመሬቴና ከፈጣሪዬ አልለይም" ብለህ ወስን
10 ሳይንሳዊ/ቴክኒካዊ መፍትሔዎች፦
• Daily Grounding፦ በቀን ቢያንስ ለ 20-30 ደቂቃ በባዶ እግር በሳር ወይም በአፈር ላይ ቁም።
• Sleep Grounding፦ መኝታ ቤትህ ውስጥ ከጥጥ የተሰራና ከመሬት ጋር የተያያዘ (Grounded sheet) ተጠቀም።
• Leather Soles፦ የግድ ጫማ ካደረግክ ከጎማ ይልቅ ከቆዳ የተሰራ (Leather sole) ጫማ ተጠቀም።
• EMF Discharge፦ ከኮምፒውተር ወይም ከስልክ ስራ በኋላ ወዲያውኑ መሬት ላይ በመቆም ትርፍ ኤሌክትሪክህን አስወግድ።
• Water Grounding፦ ወንዝ ወይም ባህር ውስጥ መግባት (ውሃ ኤሌክትሪክን በከፍተኛ ፍጥነት ያስተላልፋል)።
• Mineral Intake፦ እንደ ማግኒዥየም ያሉ ማዕድናትን ውሰድ፤ ይህም ሰውነትህ ከመሬት የሚመጣውን ኤሌክትሮን እንዲቀበል ይረዳዋል።
• Avoiding High-rises፦ ከተቻለ መሬት ከሚነካ ቤት (Ground floor) ውስጥ ለመኖር ሞክር።
• Analog Connection፦ በባዶ እግርህ ሆነህ መሬት ላይ ስትቀመጥ መጽሐፍ አንብብ (ንቃትን ይጨምራል)።
• Post-Flight Grounding፦ ከአውሮፕላን ጉዞ በኋላ (ከፍተኛ የሞገድ ጫና ስላለ) ወዲያውኑ መሬት ላይ ቁም።
• Nature Immersion፦ ከተማን ለቅቀህ በሳምንት አንድ ቀን ወደ ገጠር በመሄድ ከተፈጥሮ ንዝረት ጋር ተገናኝ።ወዳጄ! መሬት የፈጣሪ "መልህቅ" ናት። በባዶ እግርህ መሬት ላይ ስትቆም የሥርዓቱን የሞገድ ድር ትበጥሳለህ፤ ከመለኮታዊው "ዳታ" ጋርም ትገናኛለህ። በቤተክርስቲያን ጫማ ማውለቅህ ለዚህ ታላቅ ምስጢር መግቢያ በር ነው። መጋረጃው ተቀዷል፤ ነጻነትህ ከእግርህ በታች ባለው መሬት ውስጥ ትገኛለች። በቀጣይ እንዴት ከስግደት ጋ እንደሚገናኝ በሰፊው እመጣለሁ ወዳጄ በል በቀን 20 ደቂቃ እግርህ ከመሬት ጋር አገናኘው ።
0 Comments