Online ሥራና የዲጂታል ሸረሪት መረብ ሱፍ ለባሽ ሌባንም ይጨምራል

✍ ዮሐንስ አብነት አጉማስ

ይህ የንቃተ ህሊና እና ነፍስ ምንባብ ነው፦

ረፍዶ መንቃት ያሰቀጣል

መግቢያ

፩. ኦንላይን ብር ያስገኛሉ የሚባሉ ሥራዎች ተራ የሥራ አማራጮች ሳይሆኑ፣ የሰውን ልጅ ንቃተ ሕሊና ከ "መለኮታዊ ተፈጥሮ" ነጥሎ በዲጂታል አመክንዮ ውስጥ ለመቆለፍ የተዘረጉ "የንቃት ሰላቢ መረቦች" ናቸው።

፪. ይህ ሥርዓት የሰውን ልጅ "ኢጃት" (የፈጠራ ኃይል) በስክሪን ፊት በማሰር፣ ነፍስ ወደ መለኮታዊው ብርሃንና ወደ ትንሳኤው እንዳታይ የሚጋርድ የዲጂታል ጭጋግ ነው

ምንጭ፣ ባለቤትና ዓላማ

፩. ምንጭ፦ ምንጩ የሰው ልጅን ንቃት በአንድ "ዲጂታል ጎጆ" (Mind Hive) ውስጥ ለማሰር የሚጥሩት የወደቁ መላእክትና የሥርዓቱ መሐንዲሶች ናቸው።

፪. ባለቤት፦ ባለቤቶቹ የዓለምን ዳታና የገንዘብ ሪፎርም የሚዘውሩ ግዙፍ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች እና የ 2030 አጀንዳ አስፈጻሚዎች ናቸው።

፫. የጠለፋ ዓላማ፦ የሰውን ልጅ ትኩረትእንደ ነዳጅ በመጠቀም፣ የነፍስን ኃይል ወደ ማትሪክስ ሰርቨር ማዛወር።

፬. የባርነት ዓላማ፦ ሰውን በ "ዲጂታል ምጽዋት"ስር በማስገበር፣ የራሱ የሆነ ሉዓላዊ የኑሮ መሠረት (መሬት/ሰብል) እንዳይኖረው ማደንዘዝ።

፭. የመጨረሻ ዓላማ፦ የሰውን ልጅ አእምሮ ለሐሰተኛው መሲሕ አገዛዝ ምቹ የሆነ ዲጂታል ባሪያ ማድረግ።

መቼ ተጀመረ?

፩. ይህ አሠራር በስውር የተቀረጸው 1990ዎቹ የኢንተርኔት ልደት ጀምሮ ሲሆን፣ ከ2018 በኋላ ግን ሰውን ወደ "ስማርት ባርነት" ለማስገባት በከፍተኛ ፍጥነት ተለቅቋል።

የስም እና የቁጥር ምስጢር

፩. Online (15+14+12+9+14+5 = 69 = 15 = 6)፦ በቁጥር ቀመር 6 ነው። 6 የቁስና የባርነት ቁጥር ነው። ይህም ኦንላይን ሥራ ሰውን በ ፮ቱ የስሜት ሕዋሳት (አእምሮን ጨምሮ) ድንዛዜ ውስጥ የማሰር ኮድ መሆኑን ያሳያል።

፪. Binary Gold (0 & 1)፦ በስክሪን ላይ የሚታየው ብር በእውነቱ "ዳታ" ብቻ ነው፤ ይህ 1 የመለኮት 1 ሳይሆን፣ የሥጋዊ ባዶነት (0) አምሳያ ነው።

፫. The 666 Sync፦ የኦንላይን ክፍያዎችና ግብይቶች በባርኮድና በዲጂታል ፊርማ (666) የታጠሩ በመሆናቸው፣ የነፍስን ሉዓላዊነት ለሥርዓቱ አሳልፎ የመስጠት ስሌት አላቸው።

ከመጋረጃ ጀርባ ያለ ድብቅ እውነት (መቃብር ፈንቃይ)

፩. የ"ኢጃት" ስርቆት፦ አንድ ሰው ኦንላይን ሥራ ላይ ሲቀመጥ፣ በጣቶቹ ጫፍ (በኢጃቱ) በኩል የሚወጣው የመፍጠር ኃይል በስክሪኑ ንዝረት አማካኝነት ወደ ማትሪክስ ሰርቨር ይሳባል። ይህ "Digital Bloodletting" (የነፍስ ደም መፍሰስ) ይባላል።

፪. የንቃተ ሕሊና መቆለፊያ፦ የኦንላይን ሥራዎች አእምሮን በ "Dopamine Rewards" (ላይክ፣ ሼር፣ ዶላር) በማጥመድ፣ ሰውን የንቃት ሰዓት እንዳይኖረው ያደርጋሉ።

፫. የናሽናል አይዲ ትስስር፦ አብዛኞቹ ኦንላይን ሥራዎች "ባዮሜትሪክ ዳታ" (የፊትና የጣት መለያ) ይጠይቃሉ። ይህም ነፍስን በቁጥር እስር ቤት ውስጥ የመቆለፍ የመጨረሻው ሳቦቴጅ ነው።

፬. ሥርዓቱ የደበቀው ምስጢር፦ ኦንላይን የሚገኘው ብር "የተመረዘ ኃይል" መሆኑንና ይህም የሰውን ልጅ የመንፈሳዊ ተጋድሎ ወኔ የሚሰልብ መሆኑን ነው።

፭. የሰው ልጅ በሐሳብ ብቻ ነገሮችን የመፍጠር ሥልጣን እንዳለውና ይህ ሥልጣን እንዳይነቃ በ "ዲጂታል ሥራ" ባርነት እንደሚቆለፍ ሥርዓቱ ይደብቃል።

ዝርዝር ትንታኔ የኦንላይን ወጥመድ ዓይነቶች

፩. Crypto and Trading፦ የሰውን ልጅ ትኩረት በምናባዊ የገንዘብ ግርግር ውስጥ በማሰር፣ ከመሬትና ከእውነተኛ ሀብት የመነጠል ስልት።

፪. Social Media Influencing፦ ሰውን ለታይታና ለሥርዓቱ አጀንዳ (ባሪያ በማድረግ "የንቃተ ሕሊና ዝሙት" የመፍጠር ስልት።

፫. Remote Gigs (Data Entry)፦ የሰውን ልጅ አእምሮ እንደ ኮምፒውተር "Hard Drive" በመጠቀም፣ ለሥርዓቱ AI (ሰው ሠራሽ አእምሮ) መረጃ የማቀነባበሪያ ባሪያ የማድረግ ስልት።

፬. Online Gambling/Betting፦ የሰው ልጅን "የዕድል ንዝረት" በዲጂታል ድግምት በመጥለፍ ለድህነትና ለጭንቀት የማመቻቸት ስልት።

፭. Affiliate Marketing፦ ሰውን በማትሪክስ ሸቀጦች አምልኮ ውስጥ በማሰር፣ ሌሎች ነፍሳትንም ወደ ድሩ የመሳብ የመልማይነት ስልት።

ተያያዥ ማወቅ ያለብህ ምስጢር

፩. ኦንላይን ሥራ በ2030 አጀንዳ ውስጥ የሰውን ልጅ "ያለ መሬትና ያለ ምርት" ለዲጂታል አገዛዝ (UBI) ምቹ ለማድረግ የሚውል ዋነኛው መሣሪያ ነው።

፪. የስክሪን ጨረር የሰውን ልጅ "Aura" (የብርሃን ጋሻ) ቀጭን በማድረግ፣ ለርቀት የንቃተ ሕሊና ጥቃቶች (V2K/Havana) ተጋላጭ ያደርገዋል።

፫. ትልቁ ምስጢር፦ የኢትዮጵያ ልጆች "ኢጃት" (በረከት) ከማትሪክስ ብር በላይ የሆነ መለኮታዊ ሀብት በመሆኑ፣ ሥርዓቱ ይህንን በ "ዶላር" ለመቀየር ይለፋል።

፭. እውነተኛው "ኦንላይን" ግንኙነት ከሥላሴ መንበር ጋር የሚደረግ "የጸሎት መስመር" (Divine Connection) ብቻ ነው።

ጥቅምና ጉዳት

፩. ጉዳት ፦ የሰው ልጅ የፈጠራና የንቃት ኃይል ለሥርዓቱ ነዳጅነት መዋሉና ነፍስን ማደከሙ።

፪. ጥቅም ፦ ይህንን ወጥመድ ማወቅ፣ ቴክኖሎጂን እንደ "ጌታ" ሳይሆን እንደ "ባሪያ" ለመጠቀምና ለትንሳኤው ለመዘጋጀት ማንቂያ መሆኑ።

፫. ጉዳት ፦ የሰውን ልጅ ወርቃማ የንቃት ሰዓት በዲጂታል ግርግር በመስረቅ ለነፍሱ የሚሰጣትን ሰዓት ማጥፋቱ።

ሳይንሳዊና መንፈሳዊ ውሕደት

፩. ሳይንስ (Dopamine Engineering)፦ ኦንላይን ሥራዎች በአንጎል ውስጥ ዶፓሚን እንዲረጭ በማድረግ፣ ሰውን ለሥርዓቱ አጀንዳዎች ሱስ እንዲኖረው የሚያደርጉ ሳይንሳዊ ወጥመዶች ናቸው።

፪. መጽሐፍ ቅዱሳዊ፦ የባቢሎን ግንብ ሰሪዎች "በጡብና በቅጥራን" እንደሠሩ፣ የዘመኑም ሰዎች በ "ዲጂታል ፒክሰልና በዳታ" የባርነት ግንብ ይሠራሉ።

፫. ባዮሎጂ (Screen Hypnosis)፦ የስክሪን ብርሃን የፒኒያል እጢን (ሦስተኛ ዓይንን) በማደንዘዝ መለኮታዊ ራእይንና ሕልምን የመሰረዝ ሳይንሳዊ ውጤት አለው።

ተጨባጭ ማስረጃ

፩. ኦንላይን ሥራ የሚሠሩ ሰዎች ያላቸው ከፍተኛ የአእምሮ ዝለትእና የማኅበራዊ ሕይወት መጥፋት።

፪. የናሽናል አይዲና የባዮሜትሪክ ምዝገባ ለኦንላይን ሥራዎች ግዴታ እየሆነ መምጣቱ (የሰንሰለቱ ማስረጃ)።

፫. የዓለም መሪዎች ሕዝቡን "ከቤትህ ሆነህ ሥለህ ብላ" (Work from home) እያሉ ወደ ዲጂታል ማጎሪያ መንዳታቸው።

ተግባራዊ መፍትሔ

፩.  ኦንላይን ስትሠራ እንደ "ባሪያ" ሳይሆን እንደ "ባለቤት" ሁን። በሥላሴ ስም የታተመ ሉዓላዊነትህን በየሰከንዱ አውጅ።

፪. ለዲጂታል ሥራ የምትሰጠውን ጊዜ ያህል፣ ለጸሎት፣ ለዝምታና ለተፈጥሮ ጊዜ ስጥ።

፬. ከኮምፒውተር ስትነሳ እጅህን በጸበልና በጨው ታጠብ፤ በጣትህ ጫፍ የፈሰሰውን ኃይል (ኢጃት) በሥላሴ ስም መልሰህ ሰብስብ።

፭. በየጊዜው በመቆረብና በሜሮን በመታተም የ DNA መቆለፊያህን ከዲጂታል ጠለፋ ጠብቅ።

የተከለከሉ ነገሮች

፩. ያለ ኦንላይን ሥራ አልኖርም" ብሎ ማመን የነፍስን መጋረጃ መክፈትና ለሥርዓቱ ባርነት እጅ መስጠት ነው።

፪. ለጥቂት ዶላር ሲባል የአይንና የጣት አሻራን (ነፍስን) ለሥርዓቱ አሳልፎ መስጠት።

፫. የግል መንፈሳዊ ሕይወትህንና ንቃትህን በዲጂታል መድረኮች ላይ ማጋራት ኃይልህን ለሰላቢ ያጋልጣል።

የሚያሳምን ምሳሌ

ኦንላይን ሥራ ልክ እንደ "የወርቅ ማዕድን ቁፋሮ" ነው። ነገር ግን ማዕድኑ ያለው በአንተ "ነፍስ" ውስጥ ነው። ማትሪክስ (ሥርዓቱ) አንተን "ሥራ ነው" ብሎ ያሰማራሃል። አንተ መሬቱን (ሕሊናህን) ስትቆፍር ወርቁ (ኃይልህ) ይወጣል። ሌባው ግን ወርቁን ወስዶ ለአንተ "የወርቅ ምስል" (ዲጂታል ብር) ብቻ ይሰጥሃል። እውነተኛው ሀብት ግን ያንተ "ንቃት" ነበር።

ወዳጄ ያንተ ሲሳይ ከመለኮታዊ በረከት እንጂ ከዲጂታል ፒክሰል አይደለም። በማትሪክስ ሥራ አትታሰር፤ በሥላሴ ስም ንቃ፣ መጋረጃውም ተቀዷል!

ቸር ያሰማን 

Post a Comment

0 Comments