✍ ቲና በቀለ | ኢትዮጵያ አውታር
ቀይ አይን ንቃተ ህሊና ውስጥ አንዱ ጥበብ ነው የኪሩብ መላዕክት ሰውነታቸው በአይን የተሞላ ነው በዚህም ጥበብ በጠለሰማቸው ለሊቃውንት አባቶች ይህንን አይን ይገልጣሉ አንድም የእውቀት ብርሀንን ይሰጣሉ ይህም ማለት ሰው በእግዚአብሔር አምሳል ከተፈጠረ ፈጣሪ መለኮት ነው ያያል ሰው የመለኮት ባህሪው ነፍሱ ናት ስለዚህ ነፍስ ታያለች የምታየው በ3ኛው አይን ነው እኛ ሰዎች የስጋ ባህሪ ያሸንፈናል።
ሶስተኛው አይናችን ግንባራችን መሀል ይገኛል ይህ አይን ልክ እንደ ጨረር ያለ ብርሀን አለው ፍፁም በስጋ አይን የማይታይ ቢታይ የስጋን አይን የሚያውር ነው።
ታዲያ ይህንን ሶስተኛ አይን የሚገልጡ መንፈሳውያን ናቸው ወይ ነጩ መንፈስ ወይ ጥቁሩ መንፈስ ነው እግዚአብሔር የሚገልጠው በመንፈስ ለጠነከሩ ለነ ሐ/ጴጥሮስ ለነ ኢሳይያስ ለነ ዮሐንስ ለነ ሔኖክ ነው ምክንያቱ ደሞ ያሳብዳል....!!!
ይህ ማለት ሶስተኛው አይን በራ ማለት የተደበቀውን ሚስጥር ጨለማ እና ብርሀኑን ሁሉ አየ ማለት ነው ከመላዕክት ወገን ይመደባል ማለት ነው ማለትም እንደ መላዕክት ሆነ ማለት ነው ምንም አይነት መለኮት ማየትም ይችላል ማለት ነው(ከፈጣሪ ውጪ) ልቡ የፀና እና ምንም አይነት የስጋ ስሜትም ከነፍሱ በታች የሆነ ነው ማለት ነው። ይሔ በቅዱሳን አባቶች ያለ ነው።
ሁለተኛው?
ይሔ ደሞ ከዳቢሎስ ወገን ለሆነ ሰው እርስ በእርስ ይገለገሉበት ዘንድ የሚገለጥ ጥበብ ነው። ለእናንተ ማስተማር ስላለብኝ ብቻ ይህን እፅፋለሁ በተለይ ወደ መንፈሳዊ ጥበብ ለሚቀርቡ ሰዎች ይህ አይን #በጥቁር_አስማት ሲመጣ በተለይ በልምምድ ይመጣል ፍፁም አይምሮአችሁን የሚቆጣጠር ሲሆን በአንዳንድ የሀይማኖት ተቁውማት ነብይ ትሆናለህ ሁሉን ታያለህ ፀልይ እያተባለ በተለይ በtv ቻናል ላይ እየወጣ ይገኛል የእግዚአብሔር አገልጋይ የምትሆኑት ፈጣሪ ራሱ ሲመርጥ እንጂ ሰው በመረጠው አይሆንም ነብይም ቢሆን ሌላም በእውነት በሀሰት ትምህርት ብዙዎች እየሳቱ ነው በተለይ የአንዳንድ ሐይማኖት በእውነት ለመተቸት አደለም ነብይ ነን የሚሉ ወደው እንዳይመስላቹ አዎ መላዕክት ሲወጡ ሲወርዱ ያያሉ ከሰው ቡዳ ጠቋር መተት ሊያስወጡ ይችላሉ ግን ግን በዛ መንፈስ ፋንታ እጥፍ የጨለማ መንፈስ ይገባል!!!
ፈጣሪ እንዲ ይላል በቅዱስ መፅሐፉ አንድ ሰው መንፈስ ይዞት ከወጣለት በኋላ ያመንፈስ ከሱ የተሻሉ ሌሎች መንፈሶችን ወደዛ ወደ መጣለት ሰው ይልካል እና ከዚ ተጠበቁ። እውነት አጋንንት አጋንንትን ያስወጣ ዘንድ ሀይል አለው አዎ አለቃ አላቸው አንዱን ያወጣል ግን ግዴታው ሌላ ይተካል በነብይ ነኝ እያሉ ግራውንድ የጨለማ ቤት እንፀልይላችሁ የሚሉ ፍፁም ፍፁም እውነት እንዳይመስላችሁ አትሸወዱ ስንቱ አብዶ (አንተ የኔ አገልጋይ ነህ እየተባለ )በየአማኑኤል ሆስፒታል እየተንከራተተ ነው ሶስተኛው አይን አለ አዎ ይህ ጥበብ ከዲያቢሎስ ጋር የተገናኘ ነው። በተለይ lord of the ring እና hobbis (ከኢትዮጵያውያን ብራና ላይ የተወሰደ ጥበቡ ሳይገባቸው ቢቀር ፊልም መስራት የጀመሩበት የሰሎሞንን ጥበብ የሚያሳይ ነው። አስተውሉ!!!
ልጨምርላችሁ
3ኛ አይን ያለው ሰው ይሰወራል
መናፍስትን ያያል ይነጋገራል በእነሱ ቋንቋ(ይገለጥለታል)
የሰውን አካላቶች ማየት ይችላል ልብ ኩላሊት ጨጓራ ሀሞት ወዘተ አደለም እነዚን በዚያ ሰው ውስጥ ምን መንፈስ እንዳለ ያያል ከመንፈሱም ጋር ማውራት ማስወጣት ይችላል።
እስከ አርያም ያለውን በምድር ውስጥ ያለውን ያያል ወዘተ....
0 Comments