ግሪኮች ኤተር ይሉታል፣ የምስራቅ እምነቶች ዘንድ ቺ ተብሎ ይጠራል። ስለ መኖሩ፣ እውን ስለመሆኑ ለዘመናት ይታወቅ ነበር። የነጮች ሳይንስም ለብዙ ዘመናት ተመራምሮታል፣ የአልበርት አንስታይን "ሪሌቲቪቲ" እስከመጣበት ድረስ። ከዛ በኋላ ኤተር የሚባል ነገር የለም ተባለ።
ከርሱ በፊት ግን እነ ኒውተን፣ እነ ማክስዌል ሲመራመሩበት፣ ግራቪቲን እና ኤሌክቶሮ-ማግኔቲዝምን ከርሱ አንፃር ሲገልጹ ነበር። አንዳንዶች ኤሌክትሮን የምንለው ጭምር የዚህ የኤተር መገለጫ ነው እስከማለት ይደርሳሉ። ይህ ነገር ምንድን ነው?
የጥንቱ ዘመን ህዝቦች አረዳድ፣ ዓለም በሙሉ የተፈጠረችው ከአራት ባሕርያት (elements) ነው የሚለው ነበር። ዓለም ስንል ምድርና ሰማይን፣ ፀሐይ ጨረቃና ከዋክብትን ጨምሮ ማለት ነው። እናም እነዚህ አመት ባሕርያት የተባሉት የተገኙበት ሌላ አምስተኛ አለ የሚሉም ነበሩ። ይህ ሳይሆን አይቀርም ኤተር የሚባለው። ከአተም የረቀቀ ነገር፣ ቁስ አካል የምንለው ሁሉ ከርሱ የተገኘ፣ የሁሉም ፍጥረት መሠረት መሆን አለበት።
ሙቀትና ብርድ፣ ብርሃንና ኤሌትሪክ በርሱ ውስጥ የሚያልፉ ነገሮች ናቸው። አተም የምንላቸው በሙሉ እርሱን በተለያየ መልኩ በመቀያየር የተፈጠሩ ናቸው። እሳት፣ ንፋስ፣ ውሃ፣ መሬት የተባሉት አራቱ ባሕርያትም በዛው መልኩ እርሱኑ በመቀያየር የተፈጠሩ መሆን አለባቸው።
ታዲያ በመጽሐፈ አክሲማሮስ እንደምናገኘው፣ እግዚአብሔር ከራሱ ባሕርይ አውጥቶ ነው እሳትን፣ ነፋስን፣ ውሃን፣ ምድርን የፈጠረው። ስለዚህ ይህ ኤተር የተባለው እግዚአብሔር የፈጠረው የአራቱ ባሕርያት መነሻ መሠረት መሆን አለበት ማለት ነው። እግዚአብሔር ከራሱ ባሕርይ ነስቶ ያስገኘው፣ አራቱንም ባሕርያት ከዛ ያስገኘበት መሆን አለበት። እናም ዓለምን በሙሉ ከፈጠረ በኋላ ያንን ከራሱ ባሕርይ የፈጠረውን ነገር በሙሉ በዛ ነገር ሞላው። ስለዚህ ወደላይም ብንወጣ ወደታችም ብንወርድ፣ ግራ ቀኝ ብንሄድ ሰሜን ደቡብ ምስራቅ ምዕራብ ብንል ያንኑ ከእግዚአብሔር ባሕርይ የተፈጠረውን ነገር በሁሉም ቦታ ሞልቶ እናገኘዋለን። እግዚአብሔርም በርሱ አድርጎ ሁሉንም ነገር ይዞታል ማለት ነው።
አባቶቻችን በኒቅያ የሃይማኖት መሠረትን ሲዘረጉ "ነአምን በእግዚአብሔር አብ አኃዜ ኩሉ ገባሬ ሰማያት ወምድር" ያሉት ያንን በመንፈስ ቅዱስ ተረድተው መሆን አለበት። አማርኛ ትርጉሙ ተበላሽቶ ስለተተረጎመ፣ "ሁሉን የያዘ ሰማይና ምድርን በፈጠረ እግዚአብሔር አብ እናምናለን" መሆን ሲጠበቅበት፣ በስህተት "ሁሉን በያዘ" ወይም በግዕዙ "አኃዜ ኩሉ" የሚለው "በሁሉን በፈጠረ .." ተብሎ ስለተተረጎመ ጠፍቶብናል። ነገር ግን ሁሉን የያዘ ብለው ነበር አባቶቻችን የጻፉልን። እግዚአብሔር መላውን ዓለም፣ ምድርና ሰማይን፣ ፀሐይና ከዋክብትን በሙሉ በእጁ ይዟል እያሉን ነው። ሳይንስ አብዶና መስመር ስቶ ያ የእግዚአብሔር ባሕርይ መሠረቱ የሆነው ነገር የለም ቢለንም፣ ህዋ የሚባል ምናባዊ አካል አለ እጅግ የትየለሌ ሰፊ ባዶ ቦታ ምንም ንጥረ ነገርም ሆነ ቁስ አካል የሌለበት ቫኪዩም (vacuum) አለ ቢለንም፣ ፀሐይ ከምድር በልጣ ከዋክብትም ከፀሐይ በልጠው በቢሊዮን ኪሎሜትሮች ርቀው ይገኛሉ ቢሉንም ያ ፍጹም ከእውነቱ የራቀ እብደት እና ሞኝነት ነው።
ይልቁንም ሁሉም በእጁ ነው ሁሉም ከርሱ ባሕርይ በወጣ ነገር የተፈጠረ ነው፣ በሁሉም ውስጥ በሁሉም ዘንድ እርሱ አለ። ወንዙን ደኑን እንስሳውን ጥቃቅን ነፍሳትን ሁሉ ስናይ ከራሱ ባሕርይ ባመነጨው ኃይል የፈጠራቸው በዛም ውስጥ የሚኖሩ ናቸው።
0 Comments