✍ ቲና በቀለ | ኢትዮጵያ አውታር
የጥንታዊ የሱሜሪያ የአሁኗ ኢራቅ አካባቢ የነበረ ስልጣኔ ሲሆን የእርሻ ስራ፣ ስነ ፈለክ ምርምር፣ በኪነጥበብ፣ በሂሳብ፣ የሕግ ስርዓት፣ ህክምና፣ የዘመን አቆጣጠር ወዘተ ክፍተኛ እውቀትእና ስልጣኔ የነበራቸው ነበሩ ግን ይህን ሁሉ እውቀት እንዴት በአጭር ጊዜ ውስጥ ሊያካብቱ እንደቻሉ ብዙ የታሪክ አጥኚዎች ግራ የሚያጋባ ሁኔታ ነበር።
ግን እራሳቸው የሱሜሪያኖቹ በጻፏቸው የድንጋይ ላይ ጽሁፎች ይህንን ሁሉ እውቀት እንዴት በአንድ ጊዜ እንዳገኙት ይተርካሉ... ይህም አኑናኪ "Anunaki" የተባሉ አማልክቶች ከሰማይ እንደመጡ እና በተለያየ ዘርፍ ክፍተኛ የሆነ እውቀት እንደነበራቸው፣ ይህንንም እውቀታቸውን ለሰው ልጆች እንዳሳዩአቸው በዚህም ምክንያት ከፍተኛ የሆን ስልጣኔ ላይ እንደደረሱ ጽፈው አሰቀምጠዋል...
አኑናኪ "Anunaki" መናፍስት ሳይሆኑ የሚዳሰስ አካል ያላቸው አማልክት እንደነበሩ... በዚያም ጊዜ አማልክት ከሰው ልጆች ጋር አብረው ይኖሩ እንደነበሩ በጣም በቴክኖሎጂ የረቀቁ ከተማዎች እንደነበራቸው ዓለም አቀፋዊ የነበረ ስልጣኔም እንደሆነ የሚተርኩም ጥንታዊ ታሪኮች አሉ
አኑናኪ "Anunaki" የተባሉት አማልክቶቻቸው በተለያየ ዘርፍ ከፍተኛ እውቀት ስለነበራቸው በዛ ዘርፍ አምላክ ተብለው በጥንታዊ ሱሚሪያኖች ይመለኩ ነበር...
ለምሳሌ፦ ስለ ህክምና እውቀት የሰጣቸውን እንደ ህክምና አምላክ ያመልኩት ነበር፣ የጦርነት መሳሪያ አሰራር ያሳያቸውን እንደ ጦርነት አምላክ፣ የስነ ፈልክ እውቀት የሰጣቸውን እንደ ሰማይ ወይም የፀሐይ አምላክ፣ የግብርና እውቀት የሰጣቸውን እንደ ግብርና አምላክ አድርገው ያመልኳቸው ነበር።
ከሱሜሪያ ቀጥሎም በግብጽ፣ በግሪክ፣ በሮም፣ በህንድ፣ በቻይና እና ሌሎቹም በዓለማችን ላይ የነበሩ ጥንታዊ ስልጣኔዎች ሁሉም የሚስማሙመበት እና አንድ የሚያደርጋቸው ታሪክ... በጥንት ጊዜ የሆኑ ከሰማይ ወደ ምድር የመጡ አማልክት ነበሩ እነዚህ አማልክት ለሰው ልጆች እውቀትን ሰጥተው ስልጣኔን አስጅምረዋል የሚል ነው።
ሁሉም #ስልጣኔዎች በተለያየ ቋንቋ የተለያየ ስም እየሰጡ የሚያመልኩአቸው እስከ አሁንም ድረስ በነዚህ አማልክት በስማቸው ቀናት እና ወራት(ሳተርን ጁፒተር ሜርኩሪ ማርስ ቬንስ ወዘተ) ተሰይሞላቸው እየተመለኩ ያሉት እውነተኛ ማንነት የሚነግረን የመጽሐፈ ሄኖክ ላይ ያለው ታሪካቸው ነው።
እነዚህ ጥንታዊ አማልክት በመጽሐፈ ሄኖክ ላይ የእውነትኛ አማልክት ሳይሆኑ የወደቁ መላእክት እንደሆኑ ስለሚናገር የአማልክቱን እውነተኛ አመጣጣቸውን እና ማንነታቸውን ስለሚያጋልጥ...
ይህ መጽሐፍ በሁሉም የሃይማኖት ስብስብ ተቀባይነት እንዳይኖረው በውስጡ ያለውንም ታሪኩን በትርጓሜ በማጣመም እውነተኛው ታሪካቸው እና ማንነታቸውም ለመደበቅ ይሞክራሉ... መጽሐፋ ሄኖክን ላይ ያለውን ታሪክ ካልተረዳን የዓለምን ታሪክ በትክክል መረዳት አንችልም።
ሁለት መቶዎች መላእክት ከሰማይ ወርደው ሚስት ለማግባት በአርሞኤም ተራራ ላይ እርስ በእርሳቸው እንደተማማሉ የሚገልጸውን የመጽሃፈ ሄኖክ ታሪክ.... በፊልሞች መግቢያ ላይ መላእክቱን ከዋክብቱ መስለዋቸው ከሰማይ ሲወርዱ እና በተራራ ራስ ላይ ሲቀመጡ አድርገው ፊልሙን ለነዚህ የወደቁ መላእክት መታሰቢያ እንዳደረጉላቸው ያሳዩናል።
0 Comments