ስለ ልጆቹ የሚገደው አባወራ


✍ ሔኖክ ኃይለገብርኤል | አባወራ

አባወራ ሴቶች ልጆቹን በ"እኩልነት፣ መብት፣ ነፃነትና ጸረ-ጾታዊ ጥቃት" ስም ከእርሱ ስር ነጥቀው ለሚያጠፏቸው "የበግ ለምድ ለባሽ ተኩላዎች" አሳልፎ አይሰጥም!

ይህ ልባም የኾነው ትውልድ የአባወራው ንቅናቄ ነው!

ጀግኖች! የአፍሪካ ሕብረትም ኾነ የተመድ (UN) የ2030ውን ግብ በተለይም "የጾታ እኩልነት" ለማሳካት በሚል እንደ እኔ ዓይነቱን መሃይም ሳይኾን ዶላር ተቀላቢ ሆዳደር ልሂቃንና ሊቃውንትን ተጠቅሞ እየተጣደፈ ነው።

እስከዚያው ብዙ "ጥናቶች" በተለይም በሴቶቻችን ይበልጡንም በልጃገረዶቻችን ላይ ትኩረት ያደረጉቱ እየተጠናከሩ፤ ለመንግሥት የፖሊሲ ግብዓት እንዲኾኑ ይቀርባሉ።

እነርሱም ደግሞ ነገ ወደ ትምህርት ቤት፣ የሕክምና ተቋማትና ሌሎችም የሀገሪቷ ተቋማት ውስጥ እንዲገቡ ተደርገው ልጆቻችንን ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የእኛ መኾን ያቆማሉ!

ይህንን የሚቀለብሰው ስሜታዊ የኾነ ብሶተኛ ትውልድ ሳይኾን እውቀትና እምነትን ይዞ በራሱ ላይ የሠለጠነው(እንዲያ የኾነ ልብ ያለው) ብቻ ነው!

"መጋደላችን ከደምና ከሥጋ ጋር አይደለምና፥ ከአለቆችና ከሥልጣናት ጋር ከዚህም ከጨለማ ዓለም ገዦች ጋር በሰማያዊም ስፍራ ካለ ከክፋት መንፈሳውያን ሠራዊት ጋር ነው እንጂ።" ኤፌ 6፥12 እንዳለ...

የሚሠሩትን ሥራ ከማጋለጥ ጀምሮ፣ እስከ ማብራራትና የሚያደርሰውን ተጽዕኖም ማሳወቅ ድረስ እየሠራን ነው። ልጆቻችንን የሚነጥቅ ጠላት ከመቼውም ጊዜ በላይ አፉን አሹሎ፣ ጥርሱን አግጦ፣ ጥፍሩን ዘርዝሮ ከደጅ ቀርቧል!

አንተ እውነት ልጆህን ትወዳቸዋለህን?
ወይንስ ካንተ በላይ ለሚያስብላቸው UN እና EU ትተዋቸዋለህን?



Post a Comment

0 Comments