ኢየሱስ ነው የሚያድነው ሃይማኖት አያድንም በሚሉት አዲስ ፈላስፋዎች አባባል ሃይማኖት ከኢየሱስ ተቃራኒ የቆመ ማንነት ማድረጋቸው ነው።
ግን አይደለም! መጽሃፍ ቅዱስ አንድ ሃይማኖት ይላታል። ኤፌ 4፥4 ብቸኛ የእግዚአብሔር መገለጥ ወይም ትምህርት ማለት ነው ወይም ኢየሱስንና ማዳኑን የምናውቅበትና የምናመልክበት እውቀት የሚሰጠን ማለት ነው። አንድ ጊዜ ለቅዱሳን የተሰጠች ይላታል። ይሁ1፥3 ለዚህች ሃይማኖት ተጋደሉ ብሎም፡በዚሁ ክፍል ይመክራል።
ይህ ከሆነ የትኛዋን ሀይማኖት ነው የሚለው ጥያቄ ይነሳል
ኦርቶዶክስን ነው? ካቶሊክን ነው? ወይስ ፕሮቴስታንትን ነው? ሰይጣንም ክፍተት መጠቀም ስለሚፈልግ እግዚአብሔር በኦርቶዶክስነትህ ወይም በካቶሊክነትህ ወይም በፕሮቴስታንትነትህ አያውቅህም መጽሃፍ ቅዱስ ላይ ኦርቶዶክስ ወይም ካቶሊክ ወይም፡ፕሮቴስታንት የሚል የለም ይላል።
ይህን የሚሉ የቤተክርስቲያንን ታሪክ የካዱ ናቸው እንጂ ኦርቶዶክስ፡ ካቶሊክና ፕሮቴስታንት የሚሉት ስያሜዎች የመለያየት ስም ናቸው። አርዮስ በ325 ወልድ ፍጡር ነው ብሎ ከቤ/ክ ሲለይ ቤ/ክ ኦርቶዶክስ ወይም ቀጥተኛ ተብላ ቀጠለች በመቀጠል ንስጥሮስ በ431 ኢየሱስ ሁለት ባህሪ ነው፡ ድንግል ማርያም የኢየሱስ እናት እንጂ የአምላክ እናት አትባልም ብሎ ከቤ/ክ ሲለይ ቤ/ክን ተዋህዶ ወይም ከሁለት ባህሪ ባለመለያየት ባለመጠፋፋት አንድ ባህሪ የሚለውን ይዛ ቀጠለች።
እስከዚህ ጊዜ ቤ/ክ በአንድነት ቆይታ ኖራ በ451 በፖለቲካ ጫና ምክንያት የንስጥሮስን ሁለት ባህሪ ከተጣለበት አንስታ ካቶሊክ ተመሰረተች ብኋላ በ1054 ኢስተርኖች እንዲሁም ካቶሊክን በመቃወም በ1517 ፕሮቴስታን በማርቲን ሉተር ተመሰረተ ማርቲን ሉተር በጊዜው ሲለይ የተቃውሞ ምክንያቱን እንዲሁም የእምነት መግለጫ አውጥቶ ቢሆንም የኋላ ኋላ ከእርሱ የእምነት መግለጫ የራቁና በተቃራኒ የሚንቀሳቀሱ የፕሮቴስታንት ዲኖሚኔሽን እንደ አሸን በዙ በሺ የሚቆጠሩ አሁን ሆነዋል፡ለክርስትና አስተሳሰብ ውጪ ሐዋሪያዊ ቤ/ክ፡ ሞርሞኒዝም ወዘተ የመሳሰሉት የሚወጡት ከዚሁ ነው።
ስለዚህ ኦርቶዶክስ ማለት አንዲቷን ሃይማኖት የተጠበቀበት ስም ነው። እንዲሁም ሐዋርያዊ ቅብብሎሽ ማለትም ሐዋርያዊ እምነትና ስልጣን ያልተቋረጠባት ናት። ካቶሊክ ሐዋርያዊ ቅብብሎሽ ያላት ቢሆንም ሐዋርያዊ ስልጣኑን እንጂ ሐዋርያዊ እምነት ሰብረዋል በአንጻሩ ፕሮቴስታንት ምንም አይነት ሐዋርያዊ ቅብብሎሽ የላቸውም። ሐዋርያዊ ቅብብሎሽ ለመስበክ ስልጣን ይሰጣል ሮሜ 10፣15 ለማጥመቅ ስልጣን ይሰጣል። ማቴ 28፣20 ለማቁረብ ስልጣን ይሰጣል። በጥቅሉ ከአንዲት ቤተክርስቲያን መለየትና ሌላ መመስረት በመጽሃፍ ቅዱስ የተወገዘ ነው መለየትን የሚወድ ምኞቱን ይከተላል ምሳሌ 18፣1 በማለት ሲገልጽ መለያየት መንግስተ ሰማይ የማያስገባ የስጋ ስራ ነው ደግሞ ይለዋል። ገላ 5፥20
መንፈስ፡ግን፡በግልጥ፦በኋለኛዎች፡ዘመናት፡አንዳንዶች፡የሚያስቱ፡መናፍስትንና፡በውሸተኛዎች፡ግብዝነት ፡የተሰጠውን፡የአጋንንትን፡ትምህርት፡እያደመጡ፥ሃይማኖትን፡ይክዳሉ። 1ጢሞ 4፥2
እግዚአብሔር አምላክ ወደ መጀመሪያው ትምህርትና አንድነት ይመልሰን፡ አሜን!
0 Comments