✍ ቲና በቀለ | ኢትዮጵያ አውታር
በአለማችን ላይ እስከዛሬ ድረስ 'መፅሐፈ ሔኖክን' የሚያህል መፅሐፍ የለም! በመጀመሪያው ክፍል ስለ መፅሐፉ አፃፃፍና ስለ ፀሐፊው (ማለትም ስለ ሔኖክ) ትንሽ ልበላችሁና በቀጣይ ስለ መፅሐፉ ይዘት እፅፍላችኋለሁ።
ሔኖክ ማን ነው⁉️
ሔኖክ ማለት ከስሙ ትርጓሜ ስንነሳ ''ፀሐፊ" ማለት ነው። የአዳም ሰባተኛ ትውልድ የሆነ ታላቅ ሰው ነበር። እስከዛሬ ድረስ ማንም 100% አዕምሮውን የተጠቀመ ሰው የለም። ሔኖክ ግን ብቸኛው ሰው ነው። እስከዛሬ ሰው አዕምሮን ተጠቅሞበታል የሚባለው 0.06% ነው። ይሁን እንጂ በአሁኑ ጊዜም አዕምሮአቸውን እስከ 20 እና 30% ተጠቅመዋል የሚባሉ አባቶች በጥንታዊ ገዳማት ውስጥ ይገኛሉ። በአካል አግኝቻቸውም አውቃለሁ። እውነቱን ለመናገር ከነርሱ ጋር መግባባት በጣም ከባድ ነው። እጅግ ጥሩ ሰዎች ሆነው ግን አዕምሮአቸው ከኛ በጣም ልቆ ስለሄደ በንግግር ከነርሱ ጋር መግባባት ከባድ ነው። ወደ ሔኖክ ልመለስና፤ የሰው ልጅ የአዕምሮ ልዕልና ወይም (IQ) ብለን የምንጠራው የሚለካው በምድራዊ እውቀት ሳይሆን በሰማያዊ እውቀት ነው። ዓለም ላይ የምናየው ከተፈጠረው 5% የሚሆነውን ነው፤ ስለዚህ የማይታየው አለም ይሰፋል።
ሔኖክ ግን ያልታየውንም የታየውንም ዓለም አብጠርጥሮ ያየ ሰው ነው። እታች ወርዶ በርባኖስ ድረስ ላይ ወጥቶ እስከ ፅርሀ አርያም፣ እንዲሁም አንድም የአለም ጥበብ ሳይቀር ያየ፣ የመረመረ፣ የዳሰሰ ሰው ነው። ያየውንም ሁሉ በመፅሐፉ ፅፏል። ሔኖክ ሞትን ሳይቀምስ የተሰወረ ሰው ነው፤ አሁን ያለውም ከአምስቱ አለማተ መሬት 'በብሄረ ህያዋን' ተብሎ በሚጠራው አለመ መሬት ውስጥ ነው። ስለ አምስቱ አለማተ መሬት ከዚህ ቀደም ፅፌላችኋለሁ። የፃፈው መፅሐፍም በስሙ ተሰይሟል "መፅሐፈ ሔኖክ" በአማረኛው 'የሔኖክ መፅሐፍ' በመባል ተሰይሟል። ይህ መፅሐፍ ምድር ላይ የተፃፈው የመጀመሪያው መፅሐፍ ነው። ከሱ በፊት የተፃፈ ህግም መፅሐፍም የለም። ሰዎች ይኖሩ የነበሩት በህገ-ልቦና(Moral law) ነው።
መፅሐፈ ሔኖክ ስለ ፈለከ ፈለካት፣ ስለ መዋዕረ ከዋክብት፣ ስለ መላዕክት ስልጣን፣ ስለ መናፍስት ዓለም፣ ስለ ፕላኔቶች ኡደት...ወዘተ!። ብቻ የዓለም ጥበብ የተከማቸው በዚህ መፅሐፍ ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም። የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን መፅሐፍ ቅዱስ (81ዱ) ውስጥ ያለው መፅሐፈ ሔኖክ 42 ምዕራፎች አሉት። ሙሉው መፅሐፈ ሔኖክ ግን 182 ምዕራፎች አሉት። አሁን በመፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያለው መፅሐፈ ሔኖክ ግን በነጮች ሴራ ውስጡ ተበርዟል። ምን አልባት የቆየ መፅሐፍ ቅዱስ ካላችሁ አንብቡትና አባቶችን ለትርጓሜው ጠይቁ። አንዳንድ ሰዎች፤ መፅሐፈ ሔኖክ በኢትዮጵያ የለም በማለት ይናገራሉ። ዳሩ ግን መፅሐፉ ብቻ ሳይሆን ትርጓሜውም በውዷ ሀገራችን አለ። ለምሳሌ እኔ ካየሁበት ከዝዋይ ሀይቅ ደብረ ፅዮን ደሴት ውስጥ ተቀምጧል። ፎቶ ማንሳት ስለማይፈቀድ ማንሳት አልቻልንም። እንዲሁም በቁስቋም ማርያምና በላሊበላ እንደሚገኝ ከአባቶች ሰምቻለሁ። ዳሩ ግን የሚመረምርና የሚጠይቅ ትውልድ ስለጠፋ፤ ነጭ አምላኪ ኢትዮጵያዊ ሊባል የማይገባው ኢትዮጵያዊ ስለበዛ፤ አባቶች በክብር አስቀምጠው ይጠብቁታል።
ኦርጂናሉ መፅሐፍ በአንዳንድ ሀገራትና በኢትዮጵያ ነበረ። በ1722 ዓ.ም ጄምስ ብሩስ የተባለ የስኮቲሽ ዜግነት ያለው ሰው ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ነበር። የመጣበትን ምክንያት ሲናገርም "የአባይን መነሻ ለመፈለግ ነው የመጣሁት" ብሏል። ድብቅ አጀንዳው ግን ይህን መፅሐፍ ፈልጎ ነበር። ተሳክቶለትም መፅሐፉን ሁለት ኮፒ አድርጎ ወስዷል። መፅሐፉ ከተወሰደ ከአመታት በኋላ የኢንዱስትሪ አብዮትና ስልጣኔና ቴክኖሎጂ ተስፋፋ። ይህን መፅሐፍ ባያገኙ ኖሮ አሁን የሚመኩበት የህዋ ምርምር ማማ ላይ ባልደረሱ ነበር። አንድ ጥያቄ እንጠይቅ። መፅሐፈ ሔኖክ ግሪክ ውስጥና አንዳንድ ሀገራት ላይ ነበረ።
ለምን ኢትዮጵያ ያለውን ፈለጉ???
በኢትዮጵያ የሚገኘው 'መፅሐፈ ሔኖክ' በግዕዝ የተፃፈና እጅግ የተመሰጠረ ነበር። መፅሐፉን መተርጎምና ማመስጠር የሚችሉ አባቶቻችንም ነበሩ። አሁንም አሉን። በሌላ ሀገራት ላይ የነበረው የሔኖክ መፅሐፍ ግን ስም ብቻ እንጂ ያን ያህል ረቂቅ ምስጢራት የሉትም ነበር። አስቀድመውም ይህን በጥናት ስላወቁ ኢትዮጵያ የሚገኘውን ማደን ጀመሩ። ተሳክቶላቸውም ወሰዱ። አሁንም ድረስ የሚያሳዝነኝ ነገር ቢኖር አንድ ነጭ የተለየ አላማ ይዞ ሲመጣ 'ከየት ነህ? ወዴት ነህ?' ብሎ የሚጠይቅ የመንግስት አካል አለመኖሩ።
በአፄ ቴዎድሮስ ዘመነ መንግስት ጊዜ፤ እንኳንስ ይቅርና ነጭ መጥቶ መፅሐፍ ሊወስድ ቀርቶ፤ ኢትዮጵያ እግሩ ከገባበት ጊዜ አንስቶ ንጉስ ቴዎድሮስ በእስር ቤት አድርገው የጥያቄ መአት ይወርድበት ነበር። በአፄ ቴዎድሮስ ጊዜ ማለትም በመቅደላ ጦርነት ጊዜ ስለተወሰዱ መፅሐፍት ወደፊት መፃፌ ስለማይቀር ያኔ የሳቸውን ጊዜ ሰፋ አድርገን እናያለን።
የሔኖክ መፅሐፍ ላይ ስንመለስ፤ ለኛ ምንም ጥቅም እንደሌለው አድርገው እየሰበኩን "አፖክሪፋ" ከሚባሉት መፅሐፍት ውስጥ መድበውታል። #አፖክሪፋ ማለት 'የተጣሉ' ማለት ነው። ወይም 'The Hidden Book' ማለት ነው። ይህን ስም የሰጡት የፕሮቴስታንት እምነት መስራቾችና ተከታዮች ናቸው። በነሱ መፅሐፍ ቅዱስ ማለትም በ66ቱ ውስጥ የለም። ጥያቄ እንጠይቅ 'መልክተ ይሁዳ' የሚለው የመፅሐፍ ቅዱስ ክፍል በ66ቱ ውስጥ አለ። ያለውም 1 ምዕራፍ ብቻ ነው። ቁጥር 14 ላይ ሔኖክ ስለተናገረው ትንቢት ይናገራል። ሔኖክ"እነሆ ጌታ በሁሉ ላይ እንዲፈርድ በሀጢያተኝነትም ስላደረጉት ስለ ሀጢያተኛ ስራቸው ሁሉ አመፀኛዎችም ሀጥያተኛዎች በርሱ ላይ ስለተናገሩ ስለ ጭከና ነገር ሁሉ ሀጥያተኞችን ሁሉ እንዲወቅስ ከአዕላፋት ቅዱሳኑ ጋር መጥቷል "እንዲህ ብሎ ትንቢት ተናገረ ብሎ ፅፏል። ታዲያ ይህ ትንቢት የት እናግኘው??
ትንቢቱ የሚገኘው በመፅሐፈ ሔኖክ ምዕራፍ 1:9 ላይ ነው። መፅሐፈ ሔኖክ ደግሞ በ66ቱ ውስጥ የለም። ታዲያ ለዚህ ምን መልስ አላቸው??.።
መጽሐፈ ሄኖክ እኛ እንደምናስበው በ81 መፀሀፍ ያለው ትንሽዬ ጥራዝ ብቻ አይደለም። አንድ ራሱን የቻለ ትልቅ መፀሀፍ ነው። በአለማዊ እውቀት ደረጃ ስድስት ዋና ዋና ነገሮች ይዙዋል።
፩ኛ፦ #የሙት ባህርን ሚስጥር ይዙዋል፣ ሙት ባህር አለምን ለ300 አመት ያለምንም ረሀብ መመገብ የሚችል ሀብት ይዙዋል።
፪ኛ፦ አልበርት አንስታይን የጀመረው የክሩ ፅንሰ ሀሳብ ቲዎሪን ሄኖክ ከሺ አመታት በፊት ጨርሶታል። ስለ ዩኒቨርስ አቀማመጥ እና ሁኔታ ስለ ሀያዎቹ አለማት ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ።
፫ኛ፦ ስለ ኢትዮጵያ ትንሳኤ።
፬ኛ፦ ስለ ሞት መድሀኒት(እፀ-ህይወት)
፭ኛ፦ ስለ ስፔስ ሳይንስ
ወዘተ...
መጽሐፈ ሔኖክ በ16ኛው መ/ክ/ዘ የጎንደር ቤተ-መንግስትን ለማቆም መሰረት በመቆፈር ላይ እያሉ ነበር ከአፅመ ኖህ እና ከሌሎች ቅዱሳን መፀሀፍት ጋር ተቀብሮ ነው የተገኘው።
በ17ኛው መክዘ ጀምስ ብሩስ የአባይን ምንጭ ፍለጋ በሚል ሰበብ ታቦተ ፅዮንን ለመፈለግ ወደ ኢትዮጵያ የገባው ለዚህም እንዲረዳው ከሀሁ እስከ ቅኔ ሰዋስው ተምሩዋል። ታቦተ ፅዮንንም ፈልጎ አጣ። በዚህም መካከል አንድ ያላሰበው ነገር እጁ ገባ መፀሀፈ-ሄኖክ ባዶውን አልተመለሰም። የመፀሀፈ-ሄኖክን ሁለት ኮፒዎች እና ሌሎች 3000 የብራና መፀሀፍትን ሰርቆ ሄደ። አንዱን ለቅርስ አፈላላጊ ቡድን አንዱን ደሞ ለቫቲካን አስረከበ። በአሁን ጊዜ በአውሮፓ(በእንግሊዝ) በአመት ሁለት ጊዜ መፀሀፉን ለመፍታት እና ለመተርጎም ሳይንቲስቶች ይሰባሰባሉ።
0 Comments