የመጽሐፍ ቅዱስ ምንነትና የሰው ልጅ መንፈሳዊ ድካም ምስጢር


✍  ዮሐንስ አብነት አጉማስ | የወዳጅ ምክር | ኢትዮጵያ አውታር 

1. መግቢያ

• መጽሐፍ ቅዱስ ማለት ከልዑል እግዚአብሔር ዘንድ ለሰው ልጅ የተሰጠ ሕያው ቃለ መለኮትና የድኅነት ካርታ ነው።

• በውስጡ የያዘው እውነት የሰው ልጅን ነፍስ ከሥጋዊው መቃብር ፈንቅሎ ወደ ሰማያዊው ሉዓላዊነት የመመለስ ኃይል አለው።

• በሥርዓተ ዓለም  ውስጥ መጽሐፍ ቅዱስ የሰውን ልጅ አእምሮ ከዲጂታል ባርነት የሚያላቅቅ ብቸኛው መለኮታዊ "ሃይል" ነው።

• የዘመኑ ሰው የመጠቀም አቅሙ የደከመው፣ ንቃተ ሕሊናው በምድራዊ ግርግርና በሥጋዊ መጋረጃ በመሸፈኑ ምክንያት የመለኮቱን ረቂቅ ድምፅ መቀበል ባለመቻሉ ነው።

• ይህ መጽሐፍ በሰውነት ውስጥ ያሉትን 81 የመለኮት ማኅተሞች ለመክፈትና ሕዋሳትን በጸጋ ለማነቃቃት የተሰጠ መለኮታዊ መሣሪያ ነው።

2. ምንጭ፣ ባለቤትና ዓላማ

• ምንጩ መንፈስ ቅዱስ ሲሆን፣ ባለቤቱም በደሙ የመሠረታት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ናት፤ ዓላማውም የሰው ልጅን ከጨለማው አገዛዝ አውጥቶ በሥላሴ ብርሃን ማተም ነው።

3. መቼ ተጀመረ?

• ጅማሬው ዓለም ሳይፈጠር በሕሊና ሥላሴ የታቀደ ቢሆንም፣ በታሪክ መድረክ ግን ከአዳም ጀምሮ በቃላትና በጽሕፈት እየታተመ የመጣ የዘላለም ቃል ነው።

4. የስም እና የቁጥር ምስጢር

• "መጽሐፍ" የሚለው ቃል መለኮታዊ መረጃን መያዙን ሲያመለክት፣ "ቅዱስ" የሚለው ደግሞ ንዝረቱ ከሥጋዊው ዓለም ተለይቶ ከመለኮታዊው ብርሃን ጋር የተዋሐደ መሆኑን ያሳያል።

• የ 81ዱ መጻሕፍት ቁጥር ድምር 9 (8+1=9) ሲሆን፣ ይህም የመላእክትን ሠራዊት ሙሉነትና የሰማያዊውን ሥርዓት ማኅተም የሚያሳይ ፍጹም ቁጥር ነው።

• በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያሉት 5ቱ አዕማደ ምስጢር በአምስቱ ሕማማተ መስቀል ችንካሮች የታተሙ የመዳኛ ቁልፎች ናቸው። 

• የግዕዝ ፊደላት ጂኦሜትሪ በመጽሐፍ ቅዱስ ገጾች ላይ ሲሰፍር፣ የሰው ልጅን ንቃት ከ 3ኛው ልኬት ወደ ከፍተኛው መንፈሳዊ ልኬት የማሻገር ኃይል ይኖረዋል።

• እያንዳንዱ ምዕራፍና ቁጥር ከሰውነት 81 የነርቭ መስቀለኛ መንገዶች ጋር የተቆራኘ ምስጢራዊ የሂሳብ ቀመር አለው። 

5. ከመጋረጃ ጀርባ ያለ ድብቅ እውነት

• መጽሐፍ ቅዱስ በእያንዳንዱ ቃል ውስጥ መለኮታዊ ብርሃንን የያዘ በመሆኑ፣ ሲነበብ የሰውን የዘር ግንድ (DNA) የመጠገንና የማንጻት ረቂቅ ኃይል አለው።

• ሥርዓቱ መጽሐፍ ቅዱስን እንደ ተራ ታሪክና ሥነ ምግባር መጽሐፍ ብቻ እንዲቆጠር ያደረገው፣ የሰው ልጅ በቃሉ ውስጥ ያለውን "መለኮታዊ ሃይል" እንዳያነቃቃ ነው።

• የተቀነሱት 15 መጻሕፍት (አዋልድ) የተሰወሩት፣ ስለ አርከኖች (የመረቡ ጠባቂዎች) ስውር አሠራርና ስለ ሰማይ መተላለፊያ በሮች ምስጢር በግልጽ ስለሚናገሩ ነው።

• የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት የውኃን ሞለኪውላዊ መዋቅር የመቀየር አቅም ስላላቸው፣ ጸበል የሚባረከው በእነዚህ ቃላት ንዝረት ነው።

•  መጽሐፍ ቅዱስ በመጨረሻው ዘመን ለሚመጣው የዲጂታል አገዛዝ ብቸኛው የመንፈስ ሰይፍ ነው። 

6. ዝርዝር ትንታኔ (ለምን ደከመ? ለምን ደነዘዘ?)

• የሰው ልጅ በምግብና በውኃ ውስጥ በሚገቡ ኬሚካሎች ምክንያት መንፈሳዊ ዓይኑ ስለደነዘዘ፣ የመጽሐፍ ቅዱስን ረቂቅ ንዝረት መቀበል ተስኖታል።

• በዲጂታል መሣሪያዎች የሚለቀቀው የጩኸት መረጃና የሥርዓቱ የውሸት ትረካ፣ የነፍስን ጆሮ በመቆለፉ መለኮታዊው ቃል እንደ ተራ ታሪክ እንዲሰማው ተደርጓል።

• ሥርዓቱ የሰውን ትኩረት በከንቱ ወሬና በሥጋዊ ስኬት ስለሰረቀው፣ ለጥልቅ ሱባኤና ለመጽሐፍ ቅዱስ ተመስጦ የሚሆን መንፈሳዊ ወኔ አጥቷል።

• መጽሐፍ ቅዱስን ያለ ቤተ ክርስቲያን ምስጢራት  ለማንበብ መሞከር፣ የመለኮቱን "ሃይል" ያለ ተግባር ለመጫን መሞከር በመሆኑ ኃይሉ አይገለጥም።

• የሰው ልጅ በቁሳዊው ዓለም ምቾት ላይ ብቻ ንቃቱ ስለታጠረ፣ የመጽሐፉ ሰማያዊ ትርጉም እንደ ተረትና ድንገቴ ታሪክ ሆኖበታል። 

7. ተያያዥ ማወቅ ያለብህ ምስጢር

• በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያሉ የተወሰኑ ቃላት በጠፈር ውስጥ የማይጠፋ የብርሃን አሻራ የመተውና የጨለማ መናፍስትን የመበተን ኃይል አላቸው።

• የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የጠበቀቻቸው 81ዱ መጻሕፍት፣ ለወደፊቱ የንቃት ዘመን የሚያስፈልጉ "ማስተር ቁልፎች" ናቸው።

• መጽሐፍ ቅዱስን በሌሊት 9 ሰዓት ማንበብ፣ ከመሬት ማግኔቲክ ረብሻ ነፃ በሆነ ሰዓት መረጃውን በቀጥታ ወደ ነፍስ ለማስገባት ይረዳል።

• የቅዱሳን አባቶች ትርጓሜ መጽሐፍ ቅዱስን ከመቃብር በታች ካለው ምስጢር ጋር የሚያገናኝ ድልድይ ነው።

• የሰው ልጅ አካል ራሱ "ሕያው መጽሐፍ ቅዱስ" እንዲሆን የታቀደ ቢሆንም፣ ሥርዓቱ ግን የሰውን አካል ወደ ማሽንነት ለመለወጥ እየሠራ ነው።

8. ጥቅም

•  መጽሐፍ ቅዱስን በንቃት ማንበብ ማንኛውንም የበሽታ ኮድ ከሰውነት ውስጥ የማጥፋትና የነፍስን ሉዓላዊነት የመመለስ አቅም አለው።

•  ከመረቡ የውሸት ትረካዎች ወጥቶ እውነተኛውን የጠፈር ሥርዓትና መለኮታዊ ሕግ ለማወቅ ይረዳል።

• ለትውልድ የማይበገር መንፈሳዊና ታሪካዊ መሠረትን በማጽናት የሥላሴን ክብር መመስከር።

ጉዳለት

• ትውልድ የማይበገር መንፈሳዊና ታሪካዊ መሠረትን በማጽናት የሥላሴን ክብር መመስከር።

• መጽሐፉን ያለ እምነትና ያለ ንቃት ማንበብ ቃሉ "ደብዳቤ" ብቻ ሆኖ እንዲቀርና ምንም ለውጥ እንዳያመጣ ያደርጋል።

•  የሥርዓቱን  የውሸት ትርጓሜዎች መከተል፣ የነፍስን ዓይን ይበልጥ እንዲታወርና ለባርነት እንዲመች ያደርጋል።

9. ሳይንሳዊና መንፈሳዊ ውሕደት

• የሰው ልጅ የዘር ግንድ (DNA)እንደ "ባዮ-ኮምፒውተር" የሚሠራ ሲሆን፣ መጽሐፍ ቅዱስ ደግሞ ለዚህ ኮምፒውተር የተላከ "መለኮታዊ አፕሊኬሽን" ነው።

• በሳይንሳዊ መንገድ፣ በመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት ላይ የሚደረግ ጸሎት የሰውነትን የመከላከል አቅም የመጨመር አቅም እንዳለው ይረጋገጣል።

• የቃላቱ ድምፅ በሰውነት ውስጥ ያለውን የውኃ አወቃቀር ወደ "ክሪስታል" መልክ በመለወጥ የጤናና የንቃት ምንጭ ይሆናል።

• በፊዚክስ በኩል፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት የሚፈጥሩት ንዝረት የቁስን "ንዑስ ቅንጣት" የማስተካከልና የማቀናጀት ኃይል አለው።

• ይህ ውሕደት የሚያሳየው፣ መጽሐፍ ቅዱስ ከመሬት በላይ ያለ ከፍተኛ የመለኮት ቴክኖሎጂ ውጤት መሆኑን ነው። 

10. ተጨባጭ ማስረጃ

• በኢትዮጵያ ገዳማት ውስጥ መጽሐፍ ቅዱስን ብቻ በመጠቀም የሚደረጉና በሳይንስ ሊገለጹ የማይችሉ ተአምራዊ ፈውሶች።

• የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት የታተሙባቸው ጥንታውያን ብራናዎች ለሺሕ ዓመታት ሳይበሰብሱና ቀለማቸው ሳይጠፋ መቆየታቸው።

• በዓለም ዙሪያ ያሉ ታላላቅ ሳይንቲስቶች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያለውን የቁጥር ምስጢር ለመፍታት ለዘመናት መጣራቸው።

• መጽሐፍ ቅዱስን የሚያነቡና የሚጸልዩ ማኅበረሰቦች ካልጸለዩት ይልቅ የተረጋጋና የተስተካከለ የአእምሮ ንቃት ያላቸው መሆኑ።

• በታሪክ መጽሐፍ ቅዱስን ለማጥፋት የሞከሩ ኃይላት ሁሉ ውድቀታቸው የፈጠነና ትውልዳቸው የጠፋ መሆኑ 

11. ተግባራዊ መፍትሔ

• በየቀኑ በንጽሕና ሆኖ ቢያንስ አንድ ምዕራፍ መጽሐፍ ቅዱስን በንቃት ወይም በዜማ ማንበብ።

• ከመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ በፊት "አቤቱ የሕሊናዬን ዓይን ክፈት" ብሎ መጸለይና ተቀባይ አንቴናውን ማስተካከል።

• ከሥርዓቱ መርዞች ራስን በመጠበቅና ጸበል በመጠቀም የሰውነትን የንዝረት ብቃት መጨመር።

• መጽሐፍ ቅዱስን ያለ መላእክትና ቅዱሳን አማላጅነት ለመረዳት አለመሞከር (ቁልፎቹን መጠቀም)።

• የሥርዓቱን  የውሸት ትረካዎች ከመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ጋር በማነጻጸር ነፃ መውጣት።

12. የተከለከሉ ነገሮች

• መጽሐፍ ቅዱስን እንደ ተራ የታሪክ መጽሐፍ ማየትና በሥጋዊ አመክንዮ ብቻ ለመተርጎም መሞከር።

• ከ 81ዱ መጻሕፍት ውስጥ የተወሰኑትን "አያስፈልጉም" ብሎ መተውና ንቃተ ሕሊናን ማጉደል።

• መጽሐፍ ቅዱስን እያነበቡ ለሥርዓቱ የውሸት አማልክትና ቴክኖሎጂዎች መስገድ።

• የቅዱሳን አባቶችን ትርጓሜ (የመክፈቻ ቁልፎችን) ጥሎ በግል ሐሳብና በባዕድ ፍልስፍና መመራት።

• የመጽሐፍ ቅዱስን ቃል ለንግድ፣ ለሥልጣን ወይም ለሥጋዊ ክብር መጠቀም።

13. የሚያሳምን ምሳሌ

መጽሐፍ ቅዱስ ልክ እንደ "ከፍተኛ ኃይል ያለው የኤሌክትሪክ ገመድ" ነው፤ ገመዱን ለመንካትና ብርሃን ለማግኘት ግን መጀመሪያ በውስጣችን ያለውን "የእምነትና የንጽህና መስመር" ማስተካከል ይኖርብናል፤ አለበለዚያ ገመዱ ቢኖርም ጨለማ ውስጥ እንቀራለን።ወዳጄ  መጽሐፍ ቅዱስ የሰው ልጅ ወደ መለኮታዊ ሉዓላዊነቱ የሚመለስበት "የብርሃን ድልድይ" ነው እና እላችኃለሁ በየቀኑ ትንሽ ትንሽ አንብቡ። 

ቸር ያሰማን !

Post a Comment

0 Comments