✍ ሔኖክ ኃይለገብርኤል
እውነትን ለመመስከር፣ በመሰከርከውም እውነት ጎን ለመቆም "የተማረ አእምሮ፦ምሁርነት" አይጠይቅም፤ ይልቁንስ ልባምነት እንጂ!
🚨 ትውልዳችን አደጋ ውስጥ ነው!
“ችግር ላይ ነው” አላልኩም፤ ይልቁንስ “አደጋ ውስጥ ነው” አልኩኝ እንጂ!
ሰውነቱን የሚያጠፉ፣ ሀገር መገንቢያ ጡቡ ቤተሰቡን የሚያፈርሱ በርካታ የጥፋት መንገዶች ሲዘረጉ እንደ አባወራነቴ “ይመለከተኛል” ስል በተለይም ከምሠራውጋር የሚገናኙትን በተለያዩ ጊዜያት ጠቁሜያለሁ።
ይህ ብቻ አይደለም! ጉዳዩን ለሕዝብ ለማሳወቅም ጥሬያለሁ! ይህንንም የበለጠ ተደራሽ ለማድረግ የሄድኩባቸው፣ ትውልድ የሚተርፍበትን proposal ያቀረብኩላቸው ጭምር፦
👉 ጊዜ የለንም፣
👉 ጊዜ ካገኘን እናየዋለን፣
👉 ዓይተንም ጭብጡ ከማረከን እንጠራሃለን ሲሉ ገፍተውታል።
(የሚያቀርቡት እንግዳ ምንያክል የከበረ፣ የሚያነሳውስ ሃሳብ ምን ያክል የከበደ ነው ብላችሁ ከቤታቸው ብትገቡ ግን.... አዬዬዬ)
ጠርተውኝ የደረስኩበትን የሰጠኋቸው እንኳ የቀረጹትን ቪዲዮ አርቀው ጥለውታል።
ለምን?
አንተስ ራስህ ይህንን ሰምተህ ምናደረግክ?
እንቅልፍ አጥቶ መመርመሩን፣ ሸፍጡን ነቅሶ መለየቱን፣ ትውልድ የሚታነጽበትን እሴት ማካፈሉን አድካሚውን ሥራ እንኳ ባትሠራ፤ ተሠርቶ የተገኘውን ጠይቀህ ተረድተህ ለሌሎች ሊሠሩት ላላቸው እንዳታካፍል ምን ያዘህ?
ንገረኝ እንጂ! ምን ያዘህ?
በእርግጥ ያለጭነው በጅምላ ነው!
“አላለጭኩም” ብለህ አታስቀኝ አልጫነትህን አምነህ ባልተቀበልክበት ከእርሱ ልትለይ አትችልም!
ደግመህም “አልጫ አይደለሁም!” ልትለኝ ትችላለህ! ነገር ግን ኾነህ የካድከው እርሱ በውል ሳታውቀው፣ በልብህም ሳታስተውለው ገዝፎ የሚገዛህ፣ ለባርነት የሚነዳህ፣ ባርነትንም የሚሰጥህ፣ የሚያለማምድህ ባርያም የሚያደርግህ ይኾናል!
በማንም አታሳብ!
አልጫነትህን እያጸናው የመጣውን፣ የኾነውን፣ አንድ አንተን ተመልከት!
tigi’s perspective የምትሠራውን ሥራ እጅግ አደንቃለሁ። ይህ ቪዲዮ ብዙዎች ጋር እንዲደርስም አጋሩት! ለእርሷም ኾነ ለእኔ ስትሉ አይደለም! ነገር ግን ለትውልድና ለሀገር እንጂ!
ካልተዋጠልህ ደግሞ አትከተለኝ! አጨብጫቢ ፈልጌ አልጽፍም! ጀማና ደቦ፣ አጃቢና አድናቂ ወዳጆቹ ጋር ሂድ!
መድኃኔዓለም ይባርክሽ ይጠብቅሽም!
0 Comments