✍ ሔኖክ ኃይለገብርኤል | አባወራ | ኢትዮጵያ አውታር
አንድን ማኅበረሰብ በአንትሮፖሎጂ ያጠና ሰው፣ ያንን ማኅበረሰብ የማፍረስም ኾነ የማሳደግ አቅም ሲኖረው፤ የማፍረሱ ግን በትውልዱ "አልጫነት" ላይ ይወሰናል!
ዛሬ በሀገራችን “በማስረጃ በተደገፈ ጥናት” ስም የሚቀርቡ የፖሊሲ ምክረ-ሐሳቦች፣ ሀገራችን ለሺህ ዘመናት የተገነባችባቸውን ማኅበራዊ ድርና ማጎች ለመበጠስ የሚወረወሩ “የጥፋት ቀስቶች” ናቸው።
ለዚህም ማስረጃው የአሉላ ፓንክረስት “Young Lives” ለመንግሥት ያቀረበው፤ አልፎ ተርፎም በሀገሯ አባወራዊ ሥርዓትን “የሚንዱ” ሕጎችን በማውጣት ከምትታወቀው የእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ ጸሐፊ፣ የሃያ አምስት ዓመት በልጆቻችን ላይ ሲያጠና የቆየውን መረጃ አጠናክሮ የመከረበት ይኸው የፖሊሲ ሰነድ ነው፦
“Policy recommendations to promote and improve SRH for young people in Ethiopia:
◽️ Challenging discriminatory gender stereotypes, which are often reinforced in times of crises, should be prioritised through targeted initiatives to engage whole communities.
◽️ It is crucial to engage boys and men to challenge patriarchal norms and the discrimination faced by girls and women; this should also include working with traditional and religious leaders, regional government leaders, local and national NGOs, and the media.”
ከርዕሱ እንደምታዩት ሸፍጡ ለትውልዱ በተለይም ለወጣቱ ያዘነ የሚመስል “ካባ” የደረበ ነው! ለወጣቱ የሥነ-ተዋልዶ ጤናን የሚያስተዋውቅና የሚያሻሽል የፖሊሲ ምክረሃሳብ እንዲል!
“የዘመቻው ኢላማ ግን ምንድነው?” ብትሉ ካባ-መሰወሪያው (its camouflage) “አድሏዊ ሥርዓተ-ጾታን ለማጥፋት” ይበል እንጂ፦ አባወራውን፣ አባታዊ ሥርዓቱንና ወጉን ማጥፋት እንደኾነ ዝቅ ስትሉ ትረዳላችሁ!
ከላይ ከፖሊሲ ምክረ ሃሳቡ ላይ ተቀንጭቦ የቀረበው ጽሑፍ በግልጽ እንደሚለው፣ ዓላማው የኢትዮጵያን አባታዊ ሥርዓት (Patriarchal Norms) መገዳደርና መናድ ነው።
ይህንን ለማድረግም የሃይማኖት አባቶችን፣ የማኅበረሰብ ሽማግሌዎችን፣ የሚዲያ ተቋማትንና ወንዶችን ራሳቸውንም “ሥርዓቱን እንዲያፈርሱ” መሳሪያ የማድረግ ስልት ነድፈዋል።
ይህ በምሁር አፍ የተነገረ የሀገር ክህደት ካልተባለ ምን ሊባል ይችላል?
በተጨማሪም ይህ ምክረ-ሐሳብ ትውልዱን ከነባር እሴቱ የማላቀቁን ተልዕኮውን ለማጠናከርና ለማዝለቅ ከልጅነት፣ ከመዋዕለ ሕጻናት እንዲጀምር በሚከተለው መልኩ ያዝዛል፦
◽️”Shifting gender norms among young people needs to start at an early age and continue throughout adolescence, including through inclusion in school curriculums and engaging young families.”
ልጆቻችን ገና “ሀ” ብለው ፊደል ሳይቆጥሩ፣ በትምህርት ቤታቸው ውስጥ አባታቸውን እንደ “ጨቋኝ”፣ እናታቸውን ደግሞ እንደ “ተበዝባዥ፣ ተጨቋኝና ተበዳይ” አድርገው እንዲያዩ፣ ይህም በትምህርት ፖሊሲው ውስጥ እንዲካተትም ነው።
ይህ የአንድን ሀገር የወደፊት ተረካቢ ትውልድ ገና በጠዋቱ የመስለብ፣ እርስ በእርስ(ወንዱን ከሴቷ) የማለያየት፣ የራሱን ተፈጥሮና በዚያም ያለ ሚናውን፤ ማለትም በአባወራነቱ፦ አባትነቱን፣ ባልነቱን፣ ወንድነቱን፣ ራስነቱን(መሪነቱን)፤ ሴቷም፦ ሚስትነቷን፣ እናትነቷን እንድትጠላ የማድረግ ዘመቻ ነው።
አልፎ ተርፎም ይህ የአባትን ሥርዓትና ወጉን በብዝበዛ፣ በጭቆናና በበደል ብሶት አቀጣጥሎ በትውልዱ የማስጠላቱን ሸፍጥ፤ የዚሁ መርዘኛ “ጠላ” በጥባጭና ጠማቂውም የሰማዩ አባታችንን የሚጠላ ነውና ጥላቻው ወደዚያው ያድጋል!
“አባት” የሚለውን የወል ስም እና “አባትነት” የተሰኘ “መሪ፣ ጠባቂ፣ መከታ፣ አርአያ” ሚናውን፣ እንዲሁም እነዚህን ይወጣበት ዘንድ፣ አንድም በእነዚህ ይገለጥባቸው ዘንድ በእርሱ ያሉ ባሕርያቱን (ጥንካሬውን፣ ድፍረቱን፣ ጀግንነቱን፣ ኃይሉን፣ ቆራጥነቱን፣ ቆፍጣናነቱን፣ ጽኑዕነቱን፣ አሸናፊነቱን፣ ሥልጡንነቱን...) እንዲጠላ ተደርጎ ያደገው ትውልድ ራሱንም ኾነ የሰማይ አባቱን የሚጠላ ይኾናል!
ማስረጃ፦ ምዕራባውያንን ተመልከት! ራሳቸውን ጠልተው ጾታቸውን፣ አባታቸውን ጠልተው አምላካቸውን ክደውና አመንዝረው መገኘታቸውን ልብ በል!
ምሁራዊ ባንዳነቱ ቀጥሎም አባወራውን ቤተሰቡን ከሚመራበት፣ ከሚጠብቅበትና አርአያ ከሚኾንበት ሚናው ይልቅ ሚስቱ ወደ ተፈጠረችለት ረዳትነት ለማዛወር እንዲህም ይላል፦
◽️ “...encouraging fathers to be more engaged in childcare and domestic work, can all help to discourage discriminatory gender roles.”
አድሏዊ የተባለውን “ሥርዓተ-ጾታ” ለማጥፋት በሚል ሰበብ፣ አባቶች አባወራዊ ግርማቸውን ሞገሳቸውጅ ጥለው በልጆች እንክብካቤና በቤት ውስጥ ሥራ ተሳታፊ እንዲሆኑ “ፖሊሲ” ይቀረጽላቸዋል።
ይህ አባወራውን ከሀገር፣ ከአህጉርና ከአጎራባች ሀገራት ጉዳዮች፣ እንዲሁም ከሀገር ውስጥ አስተዳደራዊ መስተጋብሮች፣ ከድንበር ጥበቃና ከንቁ ማኅበራዊ ተሳትፎዎች አውጥቶ፣ በቤት ውስጥ ሥራ እንዲወጠርና ጓዳ ጓዳውን ሲል ያልጠበቀውን ትውልድ ለባርነት እንዲመች የማድረግ ሸፍጥ ነው።
ለጊዜው ያቀረብኩት በስድስት ተራ ቁጥሮች ውስጥ ከተሰደሩ ሃያ አንድ አንቀጾች ውስጥ ሁለቱን ያውም የመጀመሪያዎቹን ብቻ ወስጄ ነው። ቀሪዎቹ አስራ ዘጠኙስ...?
ወንድምዓለም! “አባወራ” ባንዳ አይደለም፤ አይኾንምም! የኾነለት ሲጀመርም “አባወራ” አልነበረም፤ ሲቀጥልም ጽድቅ ይሠራበት ዘንድ የተሰጠውን ወንድነት መክሊቱን ለሀገር ክህደት አውሎ ሲገኝ “ባንዳ”፤ በአጉል ዘመናዊነትና መንፈሳዊነት አሳቦ ተሰልቦ ሲገኝ ደግሞ “ጃንደርባ” ቢባል እንጂ “አባወራ” አይሉትም!
እኛ አባወራዎቹ ግን፦
💪 የአባቶቻችን ልጆች፣
💪 የውድ ሚስቶቻችን ባሎች፣
💪 የጣፋጭ ልጆቻችን አባቶች፣
💪 የትዳራችንና የማኅበረሰባችን መሪዎች ነን!
በወንድነት ለመስዋዕትነት ከተለየንበት ሚናችን፣ ሠልጥነንበት አበልጽገነውም ባየልንበት ጸጋችን፤ ይህንን የጥፋት ዘመቻ በጽናት እንመክታለን! የሚመክቱትንም እናፈራለን! በባንዳነት ተባባሪ ኾነን ለልጆቻችን የሚያፍሩበትን ማንነት፣ ልብ-አልባ አልጫ ሰውነት፣ የታሪክንም ውርደት አናወርስም!
ከወዴት እንደ ኾንክ ራስክን ዕይ!
🚨 ዛሬን ለመኖር ስትል አስመሳይ ከኾንክ፣
🚨 ነገ ሲያድር ሲያድግብህ ከለመድከው ላትለይ አድርባይ፣
🚨 ከነገ ወዲያም በብዙ ተከፋይ ባንዳ በየደረጃው ትኾናለህ!
ሰዎች ላይ ጣትህን አትጠቁም!
ነገር ግን አንተ የትኛው ላይ እንደኾንክ ለይ እንጂ
0 Comments