በሀገራችን ስያሜ አጊንተው ስራቸውን በሰፊው እየሰሩ ያሉ እርኩሳን #መናፍስት!!
ከተኛንበት የዘመናት እንቅልፍ የሚያነቃን ስለሆነ፤ ይልቁንም በሀገራችን ስያሜ አግኝተው እንደ ልማድና ተራ ነገር አይተን ስለዘነጋናቸው በሀገራችን በሰፊው ስራቸውን እየሰሩ ስላሉ ርኩሳን መናፍስት፤ ስለ ዛር፣ አይነጥላ፣ ጠቋር፣ መተት፣ ቡዳ (ከአይን ላይ የሚነሳ መንፈስ) ወዘተ... ስለሚባሉት ርኩሳን መናፍስት መንስኤያቸው፣ በውስጣችን ስለመኖራቸው ምልክት፣ እንዲሁም እነሱን እንዴት ከህይወታችንና ከኑሯችን እንደምናላቅቃቸው ሰፊ መረጃ ስለሚሰጥ እንድትከታተሉ ስል አሳስባለሁ።
መናፍስት ምንድን ነው?
የዛር_መንፈስ ምንድን ነው?
ከየት መጣ?
ዛር እንዴት ይመጣል?
በውስጣችን መኖሩን በምን እናውቃለን?
መናፍስት ስያሚያቸውን ያገኙት ከተፈጥሯቸው አንፃር ነው። ስጋና ደም ስለሌላቸውና የሚጨበጥ የሚዳሰስ አካል ስለሌላቸው መናፍስት ተባሉ።
መላዕክት የሚለውን ስያሜ ያገኙት ከፈጣሪ ዘንድ በመላክና በመታዘዝ ስለሚያገለግሉ ነው። መላዕክት (መናፍስት) በሁለት ይከፈላሉ፤ ቅዱሳንና ርኩሳን ወይም የወደቁ መላዕክት በመባል። አወዳደቃቸውም በሁለት መንገድ ነው። #ሳጥናኤልን አንተ ፈጠርከን ያሉት ቀጥታ ጥልቁ ወደሚባለው አስፈሪ ቦታ ተጥለዋል፤ ሁለተኛዎቹ ደግሞ ሳጥናኤልን ፈጠርከንም አልፈጠርከንምም ያላሉት አቋም አልባዎቹ ደግሞ አየር ላይ ተበትነዋል እነዚህ የአየር ላይ አጋንንት በመባል ይጠራሉ። እነዚህ መናፍቶች የሰውን ልጅ በፀሎት ሰዓት በከባድ ሁኔታ ይፈታተናሉ። የሚጥል በሽታ መሬት ላይ የሚያንከባልሉ እና አረፋ የሚያስደፍቁ አየር ላይ የተበተኑ አጋንንቶች ናቸው። ስለነዚህ መናፍስት በሰፊው በቀጣዮቹ ክፍሎች እመጣበታለሁ።
የዛር መንፈስ!
ስሙ በቀጥታ ይናገራል፡፡ <ዛር> ማለት <ዘር> ከምትለው ቃል የተነሣ ሲሆን በዘር የሚሄድ ወይም በዘር የሚያልፍ ማለት ነው፡፡
የመንፈስ መልካም ባይኖረውም የዚህ መንፈስ አደገኝነትና አስቸጋሪነት የሚያያዘው ከዚሁ በዘር ከመወራረሱ ጠባይና ገጽታ ምክንያት ሲሆን ከማኅጸን ጀምሮ ልክፍት እየሆነ፤ ቁራኛ እየሆነ፤ የሰውን ልጅ ሕይወት የሚያበላሽ፣ ዕድል ላይ የሚቆሞ፣ ከኛ አሳልፎ ቀጣዩን ትውልድ ገና ከማለዳ የሚያስር፤ ከሰማይም ተባሮ ሲወድቅ ደጋ ላይ አርፎ፤ በኋላ በሰው ልጆች ልብና ኑሮ ውስጥ ሰፊ አድማስ ያለው ቁጥጥርን ማግኘት የቻለ የርኩሳን መናፍስት ስምሪት ነው ዛር፡፡
ዛር ምንድን ነው?!
"በዛሮች ቁጥጥር ስር ምድር ወድቃለች"
የዛር መንፈስ ከየት መጣ?
ከእለታት በአንዱ ቀን የእግዚአብሔር መልእክት ወደ አዳምና ሔዋን መጣ:: ከገነት ተባረው በመሬት ላይ መመላለስ ከጀመሩ በኃላ ከመጡና የሰው ልጅ እጣፈንታ ከቀየሩ መልእክቶች አንዱ ነው:: እነኝህ ሁለት ጥንዶች 30 ጥንድ ልጆች ነበሯቸው:: እግዚአብሔር እነኝህን ልጆች ሊጎበኝ እንደሚሻ መልእክት አደረሳቸው:: የፍቃድ አምላክ ነውና:: እነርሱም ቆም ብለው ደካማ ሀሳብ አሰቡ:: " አሁን ለእግዚአብሔር ቆንጆዎቹን ልጆቻችንን ብናሳየው መርጦ ለእርሱ አገልግሎት ይወስድብናል:: ስለዚህ አስራ አምስቱን ቆንጆዎቹን ከዋሻ ውስጥ እንደብቃቸውና አስራ አምስቱን እናሳየው" ብለው መከሩ:: አሉኝ የሚሏቸውን ልጆች ሁሉ እርሱ እንደሰጣቸው አላስተዋሉም ነበር:: እንደመከሩትም አደረጉና አስራ አምስቱን ቆንጆዎቹን መርጠው ከዋሻ ደብቀው ያልተጋነነ ውበት ያላቸውን ወደ እርሱ ወሰዱ:: እግዚአብሔርም በምክራቸው አዘነ:: ከዋሻ የተደበቁት አስራ አምስት ልጆችና የልጅ ልጆች እንደተሰወሩ እንዲቀሩ ረገማቸው:: ከዛች ቅፅበት አንስቶ አዳምና ሔዋን ልጆቻቸውን ማየት ተሳናቸው:: ተሰወሩ:: መንፈስ ሆኑ:: ዛር ተብለውም ተጠሩ::
ዛሮች በእኛ በምንታየው የሰው ልጆች ላይም ቅናት ያደረባቸው ከዚያን ጊዜ አንስቶ ነው:: ዛሮች እንደኛው የራሳቸው ስልጣኔ አላቸው:: ይዋለዳሉ:: ስሜት አላቸው:: ያፈቅራሉ ይጠላሉ ያዝናሉ ይደሰታሉ:: በእኛና በእነርሱ መካከል ያለው ልዩነት እኛ እንታያለን እነርሱ መናፍስት ናቸው:: እኛ ስለምድር ያለን እውቀት አናሳ ነው:: ምክንያቱም ግዝፈታችን ይገድበናል:: እነርሱ ግን የማይታየን የምድር አካል ወይንም Dimension ስለሚመለከቱ ከእኛ ይልቅ የሚያውቁት አለ:: በተለይም በምድር ላይ ስላሉ ሀብቶች ጥልቅ እውቀት አላቸው:: ዛሮች ታድያ በማይታየው በእነርሱ ዓለም ላይ ብቻ ሳይሆን በሚታየው በእኛ ዓለም ላይም የመሰልጠን የበርካታ ሺህ ዘመናት እቅድ ነበራቸው:: ይህን ተግባራዊ ለማድረግ የሰው ልጆችን አእምሮ ይቆጣጠራሉ ከሰው ልጆች ጋር ይዳቀላሉ:: ታድያ ይህ እንቅስቃሴያቸው ኢትዮጵያ በምትባል አገር ምክንያት ላለፉት ሺህ ዘመናት አልተሳካም ነበር:: እንዴት ቢሉ ኢትዮጵያውያን ከእግዚአብሔር በነኢትኤል የተቀበሉትን ፀጋ መሰረት በማድረግ ዛሮችን ያስገዙ ወይንም ይቆጣጠሩ ነበር:: እኛ በነርሱ ላይ የበላይነት ነበረን እንጂ እነርሱ በኛ ላይ የበላይነት አልነበራቸውም:: ለዛ ነው ከተሸነፉላቸው ምእራባውያን ጋር ተጣምረው ተጋብተው ተሳስረው አዲሱ የዓለም አገዛዝን (New world Order ) ተግባራዊ ለማድረግ Illuminati የተሰኘ ስርአት የፈጠሩት:: በዚህ ስርአት ቁጥጥር ስር አልወደቅንም ነበር:: ምክንያቱም እነኝህን አካላት ልንገዛ እንጂ ሊገዙን አልተመረጥንም:: ስንመረጥ ጥበብ ነበር የተሰጠን:: እሱን አስጣሉን:: ይኀው ዛሬ ማንነታችንን ክብራችንን ፀጋችንን አስጥለው ያባሉናን:: ዛሮች የሰውን ልጅ አእምሮ ለመቆጣጠር ከሚጠቀምቧቸው መንገዶች ዋንኞቹ ሶስት ነገሮች ናቸው፦
1, ገንዘብ
2, ወሲብ
3, ስልጣን ናቸው::
በነገራችን ላይ ሐተታ መናፍስት በተሰኘው ጥንታዊ መፅሐፍ ላይ ስለዛር ብዙ መረጃ ሰፍሯል:: ዛሬ ላይ ከእነዚህ መናፍስት የተዳቀሉ ሰዎች ዓለምን እንደሚያምሷት አምናለሁ:: በእኛም ዘንድ ሳናውቀው በባህላችን ውስጥ በሰረፀው ባእድ አምልኮት ራሳችንን ለነዚህ አካላት አስገዝተናል:: ከስር በኮመንት መስጫ ስር ፎቶው የምትመለከቷት ከዛር ነገስታቶች አንዷ እንደሆነች የሚነገርላት #ራሄሎ የተሰኘች ዛር ናት:: እሷና ነገዶቿ ውበታቸውን ገልጠው ለወንዶች በማሳየት የብዙ ወንዶች ህይወትን አበላሽተዋል:: ብዙ የክፍለአገር ሾፌሮች ብዙ ገጠመኞች አሏቸው ከነርሱ ጋር በተጎዳኘ::
ዛር እንዴት ይመጣል❓
የዛር አጋንንትና ወይም ሰይጣን አስቀድሞ በቤተሰብ ሃረግ ውስጥ በነበሩ እናት አባት፣ አያት ቅድመ አያት ወዘተ.. በተለያየ መልኩ ሲገብርና ሲመለክ ከኖረ በኃላ ከነርሱ የሚወለዱ ልጆችን ከማኅጸን ጀምሮ አብሮ እየተወለደ <የኔ ዘር> ናቸው እያለ አብሮ ይኖራል ማለት ነው፡፡
ዛሮች የሰውን ልጅ አእምሮ ሲቆጣጠሩ ከሚታዩ ምልእክቶች መካከል የሚከተሉት ይጠቀሳሉ፦
~ ከፍተኛ ራስ ምታት
~ የጀርባ ህመም
~ ድብርት
~ ሱስ ( የወሲብ, የመጠጥ የሲጋራ ወዘተ )
~ ተስፋ መቁረጥ
~ የመንፈሳዊ ህይወት ዝለት ወዘተ ናቸው
ሰዎች በገዛ ፍቃዳቸው ዛሮችን የሚዋረሱበት አጋጣሚም አለ:: ይህን የሚያደርጉት ማእድናትን ለማግኘት፣ ለሀብት፣ ለዝና፣ ለወሲብ፣ ለስልጣን ወዘተ ናቸው:: ይህ አይነቱ ስርአት የሰውን ልጅ ባህሪ እና መንፈሳዊ ህይወት የሚፃረር ተገቢ ያልሆነ ነገር ነው:: ብዙዎችም ህይወታቸውን አጥተውበታል:: ዓለምም አሁን ያለችበትን ያልተገባ የቀውስ ስርአት ውስጥ ልትዘፈቅ ችላለች::
በዛር መናፍስት በሰዎች ላይ የሚደርስ ጥቃት! ሰዎች ከፈቃዳቸው ውጪ በዛር ነገዶች የሚደርስባቸው ወሲባዊ ጥቃት!
" ይህ ፅሁፍ ከመንፈሳዊ ህክምና ሊቃውንትና ጥቃቱ ደርሶባቸው መፍትሔ ካገኙ ሰዎች ጋር በቃለ መጠይቅ ካገኘሁት መረጃ መነሻነት የፃፍኩት ነው!!!
1. ወሲባዊጥቃት
ሰዎች ከፈቃዳቸው ውጭ በዛር ነገዶች ወሲባዊ ጥቃት ይፈፀምባቸዋል!
ይህን ጥቃት ባለመረዳት የብዙዎች ጤና ተናግቷል የብዙዎች ትዳርም ፈርሷል። ከላይ እንዳልኳቹ የዛር መናፍስት የዘር ግንድ እጅግ በጣም ውብ ከሆኑት ከአስራ አምስቱ የአዳምና የሔዋን ልጆች የሚመዘዝ ነው።
በባህርና በወንዝ ስር ተሰውረው እንዲኖሩ ፈጣሪ ከረገማቸው በኋላ እነዚህ ረቂቃን ዛሮች ከዛን ጊዜ አንስቶ እንደ ሰው ልጆች ሁሉ ከባህርና ከወንዞች ስር በብዙ ቢሊየን መጠን ተራብተዋል። #ዛሮች የሰዎችን አካልና አእምሮ በመዋረስ ወይንም በመቆጣጠር የተለያዩ ጥቃቶችን ይፈፀሙ የነበረ ሲሆን አሁንም በፈፀም ላይ ይገኛሉ። ከጥቃቶቻቸው መካከል አንዱ ወሲብ ነው። ሴቶቹም ወንዶቹም ዛሮች ብዙዉን ጊዜ ለሊት ከስድስት እስከ ዘጠኝ ባለው ሰአት የሰውን አእምሮና አካል በመዋረስ የወሲብ ጥቃት ይፈፅማሉ። በዚህ ሰአት ሰዎች በእንቅልፋቸው እየደረሰባቸው ያለውን ጥቃት በህልማቸው በእውን እያሉ ከሚመኙት ወይንም ከሚያውቁት ሰው ጋር አስደሳች ወሲብ ሲፈፅሙ ይታያቸዋል። አሳዛኙ ነገር ይህ የሚሆነው የዛር መናፍስት ወሲባዊ ጥቃት ሲያደርሱ መሆኑ ነው። ይህ ጥቃት በዛሮች የደረሰበት ሰው ጠዋት ሲነቃ ብዙውን ጊዜ የሚከተሉትን ውጤቶች ያስተውላል፦
√ የጀርባ ህመም
√ የሰውነት መድከም
√ ድብርት
√ ቀላል የራስ ህመም
√ የመነጫነጭ ስሜት ናቸው።
የዛር መናፍስት ሙሉ በሙሉ አእምሮውን ተቆጣጥረው በተደጋጋሚ የወሲብ ጥቃት የሚፈፀምበት ሰው የሚከተሉት ምልክቶች ይኖሩታል👇
√ የትዳር ወይንም የፍቅር አጋር ጋር የነበረው/ራት ስሜት ያለምንም በቂ ምክንያት መቀነስና የመጥላት ስሜት ማጎልበት!
√ ደስታ የሌለው ከተለያዩ ከማይታወቁ ሰዎች ጋር ግንኙነት እንዲፈፀም የሚገፋፋ የወሲብ ሱስ!
√ ከፍተኛ የራስና የወገብ ህመም
√ በሴቶች ዘንድ የወሊድ ችግር
√ የስራና የትምህርት ፋላጎት መቀነስ
√ የስሜት መረበሽ
√ ለፀሎትና ለቤተክርስትያን ያለን ፋላጎት መቀነስ!
√ ከፍተኛ የፍርሃትና የመደናገጥ ስሜት በዋነኝነት ተጠቃሽ ናቸው።
መፍትሔ❗
በዛር መናፍስት በለሊት የወሲብ ጥቃቶች ተፈፅሞ ከላይ የተዘረዘሩትን ምልክቶች ጠዋት ሲነሱ ካስተዋሉ ወይንም ጥቃቱ ቀድሚ እንዳይደርስብዎ የሚከተሉት ነጥቦች እንደመፍትሔ ይቀርባሉ።
1.ማታ ከመተኛትዎ በፊት ለሊቱ የሰላም እንዲሆን ከማንኛውም የመናፍስት ጥቃት አምላክ እንዲጠብቅዎ ፀልየው መተኛት (በተለይ መዝሙረ ዳዊት ደግሞ(ፀልዮ) መተኛት)
2.ምልክቶቹን ሲያስተውሉ የግል የፀሎት ጊዜ በማቀድ መፆም መፀለይ እንዲሁም ፀበል መጠመቅ
3. አእምሮን የሚቆጣጠሩ መናፍስትን ለማራቅና ተያይዘው የሚመጡ የአእምሮ ህመሞችን ለመፈወስ ለኖህ የተሰጠውን (መፅሐፈ ኩፋሌን ያንብቡ) የህክምና ጥበብ አድርገው ሰዎችን የሚረዱ የመንፈሳዊ ህክምና ሊቃውንት አባቶችን በማማከር ህክምና መጀመር ናቸው። የትኛውም ክፉ መንፈስ ካለው ሀይል የቅዱሳን መላእክት ሀይል ይልቃልና የእነርሱን እርዳታ በፀሎት በመጠየቅና መንፈሳዊ ህይወታችንን በማሰደግ ከእግዚአብሔር ጋር ያለንን ግንኙነት በማጠንከር በማንኛውም ክፉ መንፈስ የሚመጣን ጥቃት መቋቋምና ማሸነፍ እንችላለን።
ሌላው ደሞ የዛር መተላለፍ እና መወራረስን ለማስቆም የመጀመሪያው ትልቁ መፍትሔ #ቅዱስ_ቁርባን ነው፡፡ ሰይጣን ከኛው እየተወለደ የኔው ዘር ናቸው እያለ ቢፎክርም ፍፁም ምስጋና ይግባውና መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከኛው እናት ድንግል ማርያም ተወልዶ አይደለም የኔ ዘር ናችሁ ብሎናል፡፡ ቅዱስ ሥጋና ደሙን ስንወስድ ዲያቢሎስ እየተወራረሰ የመጣበት አቅጣጫና ጉዞ ከመሠረቱ ጀምሮ ይከሽፋል፡፡
በተለይ ነፍሰጡር ሴቶች፤ እባካችሁ፥ ከዛር የተላቀቀና ገና ከሕፃንነቱ በጠላት ያልተያዘ ልጅ እንዲኖር ከተፈለገ ከአምልኮት ጋር በተደጋጋሚ ማቁረብ አለባችሁ፡፡ ከእናቲቱ ወይም ከአባቱ በኩል እየተወራረሰ የመጣው መንፈስ ካለም ልክ ቁርባኑ ሲወሰድበት፤ መንገዱ ይዘጋበታል፡፡ የመንፈስ ቅዱስ የመሆንን ዕድል ጽንሱ ያገኛል፡፡ ቁርባንና ጠበል ለነፍሰ ጡር ሴት አይመከርም የሚባል ወሬ ከቤተ-እግዚአብሔር ሰዎች ሳይቀር ይናፈሳል፡፡ ይሄ የዲያቢሎስን የዘር ጥቃት ያልተረዱ፣ ስለ ክፋት መናፍስት ግንዛቤው የሌላቸውና በማወቅም ባለማወቅም በጠላት የተከበበ ትውልድ የሚያፈሩ ሰዎች ቋንቋ መሆኑን ተገንዝባችሁ ተጠበቁ!
0 Comments