አስማት ምንድነው ነው? አይነኬውና፣ አይደፈሬው አስማት!



የሚከተለውን ፅሁፍ በማስተዋል አንብቡት ስለ አስማት እንዲህ የተብራራና የተሰባጠረ መረጃ ሲወጣ የመጀመሪያው ነው። ታዲያ እኔ በመሆኔ ነው።

✍ ቲና በቀለ | ኢትዮጵያ አውታር 

ሁሉንም መርምሩ መልካሙንም ያዙ!

የሚከተለው ፅሁፉ ሀይማኖት ከመሰላችሁ በጣም ተሳስታችኋል ጥበብም ከመሰላችሁ በጣም ተሳስታችኋል ጥበብ ከዚህ እጅግ ትልቃለች። እና ምንድን ነው? አላችሁ በአንድ ቃል ርዕስ ማውጣት በጣም ከባድ ነው እንዲያው ቢቸግረኝ #አስማት አልኩት እንጂ ጉዳዩ ከዛም በላይ ነው።

እንመልከተው፦

አስማት ማለት ስሞች ማለት ነው በግዕዙ አንበሳ ብሎ አናብስት እንደሚለው ስም ብሎ አስማት ይላል በክርስትያን ቲዎሎጂ ውስጥ በላቲን ከሃይማኖት ተፃራሪ የሆነ ትርጓሜ ከተሰጠው በኋላ ከሰይጣን ጋር በማያያዝ አያሌ የአስማት መፃህፍት ይቃጠሉ ጀመር። ከእሳት የተረፉት የአስማት መፃህፍትም በጥቂት ሰዎች እጆች ስለገቡ በተለይ በምዕራቡ ዓለም ሰዎችን ማስፈራርያና መበዝበዣ ሆኑ። አዋቂዎቹ ተሳደው ስለተገደሉ ሌሎቹ የአስማት ጥቅሎቹን (መፅሀፎችን) መጫዎቻ አደረጓቸው።

ከቅኝ ግዛት በፊት በአፍሪካ አያሌ አዋቂዎች እንደነበሩ ጥናቶች ያሳያሉ። ዘመናዊ ህክምና ከመስፋፋቱ በፊት #አፍሪካውያን ይታከሙ የነበሩት በእነዚህ አዋቂዎች የቅጠላቅጠልና የሥራሥር ጥበብ ነበር። ከተፈጥሮ ጋር ጥብቅ ቁርኝት የነበራቸው አዋቂዎች ቅጠላቅጠልን ብቻ ሳይሆን መንፈሳዊ ኃይልንም ይጠቀሙ ነበር። ነገር ግን ለሀብት ቅርምት በሃይማኖት ስም የገቡ ወራሪዎች አዋቂዎችን በህዝብ ፊት እስከ ጥቅሎቻቸው በእሳት አቃጠሏቸው ግን ይህን ብቻ አላደረጉም በእኛ ዘንድ እንዲወገዙ እንዲጠሉ አውጥተን እንድንጥላቸው ካደረጉ በኋላ እነሱ ግን ከፍተኛ ጥናት ያደርጉባቸዋል።

#ለአብነት ያኽል በአክሱም አየኸዳ የሚባል ምንጭ ላይ ያስቸገረ ጋኔን ነበረ እናም እንግሊዞች በአንድ ደብተራ ምክንያት ያንን ጋኔን ይዘውት አገራቸው መሄድ ችለዋል በአባይ ወንዝም እንዲሁ ያስቸገረ አንድ ዛር ነበረ እሱንም በተመሳሳይ መልኩ እንግሊዞች ሊወስዱት ችለዋል እውነቱን ልንገራችሁ እንደ ውጭ መንግስታት በተለይ እንደ #እንግሊዝ ያለ መናፍስት አዳኝ አስማተኛና ጠንቋይ ሰብሳቢ በምድር ላይ የለም።

ይኸው እስከ ዛሬ በዓለም ላይ እየዞሩ የሰበሰቧቸውን መናፍስት መስዋዕት እያቀረቡላቸው አገራቸውን ማበልጸግ ችለዋል ሌሎች አገሮችን ለማጥቃት ተጠቅመውባቸዋል። እናም ከውጭ ወራሪዎች ያመለጠው በየዋሻው ተቀብረው የተገኙት ጥቂት ጥቅሎች ብቻ ናቸው ለጥናት ናሙና የተረፉት።
 በሀገራችን ከጥንት ዘመን ጀምሮ አንቱ የተባሉ አዋቂዎች እንደነበሩ ይታወቃል። ህዝቡን በቅጠላቅጠልና በሥራሥር ከመፈወስ አልፈው የውስጥ ደዌን በመስታዎት ቁልጭ አድርገው የሚያዩ ከእይታ ውጭ የሚሆኑ (ሚሰወሩ) በውሃ ላይ የሚራመዱና በደመና የሚጫኑ የአስማት ሊቃናት እንደነበሩ ይነገራል። ሆኖም ከሀይማኖት ምሁራን ጋር ባለመስማማታቸው ብቻ ሳይሆን ተወግዘው ከህዝቡ በመለየታቸው ቀስ በቀስ እንዲጠፉ ተደርገዋል።

በሃይማኖት መፃህፍት ውስጥም እነዚህ የአስማት ሊቃውንት መኖራቸው ተመዝግቧል። በጥንታዊቷ ግብፅ ፈርዖኖች ፊት ልዩ ልዩ ጥበቦችን ያሳዩ እንደነበርም በመፅሀፍ ቅዱስ ሳይቀር ተጠቅሷል።

ከምድያም ምድር ጥበብን ተክኖ፣ ፈርዖን ህዝቦቹን እንዲለቅ ተአምር ያሳይ የነበረውን ሙሴን በአስማት ጥበባቸው ተገዳድረውታል። የፈርዖን ጥበበኞችም በትራቸውን ወደ እባብ በመለወጥ እባብ አሳይተዋል። በዘፀአት መፅሀፍ እንደተጠቀሰው ሙሴና አሮን ፈርኦንን በተአምራት ለማስፈራራት ወደ ንጉሡ ይገባሉ። አሮንም በትሩን በፈርኦንና በባሮቹ ፊት ይጥላል። እባብ ትሆናለች። ፈርኦንም የግብፅን ጠቢባን ፈጥኖ ይጠራል። በአስማታቸው በትሮቻቸውን ወደ እባብነት ይለውጣሉ። በዚህ ጊዜ ግን ወደ እባብ የተለወጠችው የአሮን በትር የግብፆቹን በትር ትውጣለች።

በትንቢተ ዳንኤል ላይ ስለ ባቢሎን ጠቢባን እያሉ ጊዜ ተጠቅሷል። የባቢሎኑ ንጉሥ ምስጢር አዋቂዎች ህልም ፈቺዎችና ቃላተኞች እንደነበሩት በስፋት ተጠቅሷል።
በሄኖክ ምዕ 2 ላይ መጽሀፍ ላይ እንደተጠቀሰው ልዩ ልዩ ጥበቦችን ያደርጉ የነበሩት ኔፍሊም የመላእክትና የሰው ድቅያዎች አንዱ ያስተማሩት ነገር አስማት ነው።
#ፍልስጥኤማውያን እስራኤልን ሊወጉ ይመጣሉ። በወቅቱ ሳሙኤል ሞቶ ነበር። በዚህ ጦርነት የሚፈጠረውን ነገርና ምን ማድረግ እንዳለበት (የጦርነት ትንበያ) ሳሙኤል ሞቶ ስለነበር የሚነገር ይጠፋል። ቀደም ብሎ ሳኦል መናፍስት ጠሪዎችንና ጠንቋዮችን ከምድር አጥፍቶ ነበር ያለው ብቸኛ አማራጭ ሳሙኤልን በአስማት ከሙታን ጠሪዎች ዘንድ አስጠርቶ ማነጋገር ነበር። በዚህ ጊዜ ባርያዎቹ አይንዶር በተባለ ምድር አንዲት መናፍስትን የምትጠራ ሴት እንዳለች ለሳኦል ይነግሩታል። ሊገድላት የሄደ መስሏት እንዳትሸሽ ሳኦል እንደተራ ሰው ተሸፋፍኖና መልኩን ለውጦ ወደ አይንዶሯ አስማተኛ ይሄዳል። ይለምናታል። እርሷ ግን በሳኦል ታስገድለኛለህ ብላ ለሳኦል እንደማይናገር በእግዚአብሔር ይምልላትና አስማተኛዋ በድግምቷ ሳሙኤልን ከተፍ አደረገችለት። "የምትፈልገውን ጠይቀው!"

በነጳውሎስ ጊዜም መንፈስ ቅዱስን በገንዘብ ልግዛ ካለው ሲሞን ጊዜ 50ሺ ዲናር ሚገመቱ የአስማት መጻህፍት ተቃጥለዋል።

አስማት፣ መተት፣ ድግምት፣ ምትሐት፣ የሳይኪክ ጥበብና ቴሌፓቲ የነዚህ ጥበባት ባለቤት የሆኑ ግለሰቦች ፈጣሪ ሰጠኝ ተስጥኦዬ ነው በሳይንስ በላብራቶሪ በሜዲቴሽን እንዳገኙት ይዘባርቃሉ ወይም ይተውናሉ ምክንያቱም ትክክለኛው ምንጭና መንገድ በሰዎች ዘንድ እንዲታወቅ አይፈለግም።

#እውነታው ግን አመናችሁም አላመናችሁም የመንፈስ ጣልቃ ገብነት ያለው ወይም ከመንፈስ ጋር አብሮ የመስራት ጉዳይ ነው። መንፈስ ከምታስቡት በላይ ረቂቅ ነው አካል አለው ግን አታዩትም። ልክ እረኞች በእንስሶቻቸው ላይ ሰልጥነው ሲፈልጉ እርስበርስ ማጣላት ሲፈልጉ ወደ ቤት ሲፈልጉ ወደ ግብርና እንደሚነዷቸው መናፍስትም በሰው ልጆች ላይ እንዲሁ ናቸው። መናፍስት ከሰው ልጅ በጣም ቀድመው የተፈጠሩ ፍጥረት ናቸውና ስለሆነም የሰው ልጅ ሊሰለጥኑበት ችለዋል። ምንም ጥርጥር የለውም የኮምፒዩተር ቴክኖሎጂ የመጣው ከነሱ ነው። ሳይንስ ከሚሸውደን ንድፈ ሀሳብ አንዱ (emotion ) ስሜት የሚባል ነገር አለ ይላሉ።

እውነቱን ልንገራችሁ❗

ሰው ሚፈርድበት ህሊና አለው ሚያገናዝብበትና የሚመረምርበት አእምሮና ልብ አለው እውነት ነው። ሰው ሥጋ ነፍስና መንፈስ አለው ሥጋው ሲታይ ነፍስና መንፈሱ አይታዩም። የሰው ልጅ በሥጋው የእሳት፣ የውሃ፣ የመሬትና የንፋስ ባህሪ አለው። በነፍሱ ህያውነት፣ እስትንፋስን(መንቀሳቀስን)፣ ልባዊነት(አዋቂነት)፣ ነባቢነት (መናገርን) በመንፈሱ ደግሞ ማስተዋልን፣ መመርመርን፣ እምነትን፣ ተስፋ ማድረግን ከዚህ በተረፈ ስሜት የሚባል ሌላ አካል የለም።

#ሳይንስ ስሜት ቅብርጥሶ ብሎ የሚያጃጅለን በመናፍስት ተፅዕኖ ስር መውደቅን ነው። የሰው ልጅ በመናፍስት ተፅእኖ በሚወድቅበት ጊዜ የሚያሳያቸው ምልክቶች ሳይንስ ተፈጥሯዊ ስሜት የሆርሞን መመንጨት መቀየር መዛባት ብሎ ካባ ሚያለብሳቸው ናቸው። እነርሱም ንዴት በዘፈን መጦዝ፣ ራስን መሳት፣ ራስን መጥላት፣ ራስን ከአማልክት እንደ አንዱ መቁጠር፣ ሱሰኛ መሆን፣ ጣርያ የነካ ደስታ ውስጥ መግባት፣ መደበር፣ ሴሰኝነት፣ መቃዠት፣ አረመኔነት፣ ዝም ብሎ ማዛጋት፣ በማያስፈራ ጉዳይ ላይ ዝም ብሎ መፍራት፣ በማያስጨንቅ ጉዳይ ላይ ዝም ብሎ መጨነቅ፣ በተደጋጋሚ መዘንጋት፣ ዝም ብሎ ቁጣ ቁጣ ማለት፣ መደንፋት፣ ዝም ብሎ መተኛት፣ በትንሹም በትልቁም ዝም ብሎ መገልፈጥ፣ ዝም ብሎ ዕንባ ዕንባ ማለት፣ መፍዘዝ፣ መታመም ወዘተ ናቸው።

#እንዳትታዘቡን እንዳትስቁብን የመናፍስት ጥቃት እጅጉን የረቀቀና የተወሳሰበ ነው። የአስማት ሊቃናት ወይም ጠቢባን እንደሚናገሩት ከሆነ አንድ ሰው በፈጣሪ እቅፍ ውስጥ ካልሆነ ወይም ጥበብ ካልተዋሀደችው በቀር ማንም ከነዚህ የመናፍስት ጥቃት የሚያመልጥ የለም። መናፍስት ቁጥር የላቸውም ቁጥራቸው በምሳሌ ነው። አስደንጋጭ የሚገለፀው።

ምድር ከተፈጠረች ጀምሮ እስከምትጠፋ የሚንጠባጠቡት የዝናብ ጠብታዎችን አያክሉም። በዛ ላይ ረቂቅነታቸው አለ።

#የሰው ልጅ ድክመት የሆነ እውነታ ልንገራችሁ የሰው ልጅ በራሱ መልካምም ሆነ መጥፎ ሀሳብ ማፍለቅ አይችልም አለቀ። ግን ይጠይቃል ሀሳብን የሚያቀብሉት መናፍስት ከመንፈሳችን ጋር በሚፈጥሩት ኮኔክሽን አማካኝነት ነው። ይህ ብቻ አይደለም ያቀረቡለትን ሀሳብ እንዲያደርግም ያበረታቱታል ያግዙታልም። የሰው ልጅ ነፃነትና ድል የሚያገኘው ጥበብ ከእርሱ ስትዋሀደው ብቻ ነው። ከመናፍስት ጥቃት ቀላሎቹን አነሳን እንጂ መናፍስት በሰው ልጆች ላይ የሚያደርሱት ረቂቅና ውስብስብ ተፅእኖ እንዲህ በቀላሉ የሚዘረዘር አይደለም። አውሎ ነፋስ፣ ጎርፍ፣ ወረርሽኝ ሁሉ የነሱ ጥቃቶች ናቸው። የሰው ልጆችም እነሱን በመጠቀም በወገኖቻቸው የሚያደርሱት ጥፋትና ሴራ ሊናቅ የሚችል አይደለም። ከመስተፋቅር እስከ ጦርነት በጥቅሉ ይህን ጥበብ ለማግኘት መናፍስትን በቁጥጥር ስር አውሎ ወይም ከመናፍስት ጋር ስምምነትና ግንኙነት ፈጥሮ የሚከወን ነው። ይህ ጥበብ ገቢሮች (ሪቹዋልስ)፣ ጠልሰሞች (ሲምቦልስ) እና ኅቡዕ ስሞች (ስፔል) ይገኙበታል።


Post a Comment

0 Comments