በሥነ-ተዋልዶ ጤና ትምህርት ይለፉ፤ እንዲጠፉ!




ሔኖክ ኃይለገብርኤል | አባወራ | ኢትዮጵያ አውታር  

የሥነ-ተዋልዶ "የጤና ትምህርትና መብቱ" ለልጆች እንዲሰጥና በካሪኩለም እንዲካተት የሚመክሩት አካላት የትውልድን ጥፋት የሚያመጡና የሚያፋጥኑ ተውሳኮች ናቸው!

ዛሬ በ”ሳይንሳዊ እውቀት” እና “በመብት” ስም በትምህርት ቤቶቻችን ውስጥ ሊሰገሰግ የሚሞክረው የሥነ-ተዋልዶ ጤና (SRH) ትምህርት፣ የትውልዱን አእምሮ ለመበከልና ቤተሰባዊ እሴቶቻችንን ለማፍረስ የተዘረጋ የጥፋት መረብ ነው።

እንደ አሉላ ፓንክረስት ያሉ “ያንግ ላይቭስ” (Young Lives) ተሟጋቾች፣ ትምህርት ቤቶች በባዮሎጂ ትምህርት ብቻ ሳይወሰኑ የባህል እምነቶችን የሚገዳደሩና “የሥርዓተ-ጾታ ደንቦችን” የሚፈታተኑ ውይይቶችን እንዲያበረታቱ ይመክራሉ።

  • ■ Schools can play an important role in increasing adolescents’ understanding of SRH issues. Increasing the

    coverage of SRH in curriculums beyond basic biology lessons could help to ensure both girls and boys receive ageappropriate information. Promoting discussion of SRH through peer group support networks in schools (including

    girls’ clubs) and community groups (including youth clubs), could also provide a supportive environment to improve

    knowledge and help to shift cultural beliefs and challenge discriminatory gender norms.

ይህ “ባህልን መፈታተን” ማለት ልጆቻችንን ከማንነታቸውና ከሃይማኖታዊ ሥነ-ምግባራቸው ማላቀቅ ማለት መሆኑን አባወራው ሊረዳው ይገባል!

 

ከምንጩ ለማንበብ ይህ  አስፈንጣሪው ይጫኑ

እንዲህ ዓይነቱ የሥነ-ጾታ ትምህርት (Sex Education) ወይም የሥነ-ተዋልዶ ጤና ትምህርት ለታዳጊዎች እንዲሰጥ የሚገፋፋው ያለምክንያት አይደለም። ቀድሞ በፅንስ ማቋረጥ(ውርጃ) የሚታወቁ ክሊኒኮች እንደ “Planned Parenthood” ውስጥ ይሠሩ የነበሩ ግለሰቦች የጾታ ትምህርትን ለልጆች የሚገፉት “የውርጃ ገበያን ለመፍጠር” እንደኾነ በግልጽ ተናግረዋል።

ልጆቻችን ገና በለጋ ዕድሜያቸው ስለ ጾታዊ ግንኙነት እንዲያውቁ፣ እንዲያስቡና መረን እንዲለቁ በማድረግ የወሊድ መከላከያን በመጠቀም ለልቅ ወሲብ እንዲዳረጉ፣ ድንገት የሚፈጠረውን እርግዝናም እንዲያስወርዱ ለዚህም የሥነ-ተዋልዶ ንግድ “ደንበኛ” እንዲሆኑ እያዘጋጇቸው ነው።

የእነዚህ አካላት ዓላማ “አድሎአዊ የጾታ ደንቦችን መፈታተን” በሚል ስም፣ ወንድን ከወንድነቱ፣ ሴትን ከሴትነቷ የሚያወጣና የተፈጥሮን ሕግ የሚቃረን አስተሳሰብ በልጆች አእምሮ ውስጥ መዝራት ነው።

ትምህርት ቤቶችን ለዚህ አጀንዳ ማስፈጸሚያነት መጠቀማቸው፣ ወላጆች በልጆቻቸው ላይ ያላቸውን የሞራልና የሥነ-ምግባር አነጻጽ ሥልጣን ለመንጠቅ የታለመ ሴራ ነው።

አባወራው ልጆችህ በትምህርት ቤት ስም የባዕድ አጀንዳ መጠቀሚያ እንዲኾኑ አትፍቀድ። የሥነ-ተዋልዶ ጤና ትምህርት በሚል ሽፋን የሚቀርበው መርዝ፦

ትውልድን መረን ማውጣት፦ ልጆች ገና ሳይጎለምሱ ኃላፊነት ለጎደለው ልቅ ወሲብ መዳረግ፤

ማኅበረሰብን ማምከን፡- የወሊድ መቆጣጠሪያዎችን በለጋና ለምለም እድሜያቸው በመስጠት የመራቢያ እድገንጥራቸውን ማዛባት በዚያም የእርግዝና ጸጋቸውን ማሳጣትና ዘር አልባ ማድረግ፤

የሰውን ዘር ማጥፋት፡- ጽንስ ማቋረጥን (ውርጃን) በማለማመድ የሰውን ዘር ማጥፋት

ኢሰብዓዊነትን ማስተማር፡- በመብትና በነጻነት ስም ኢሰብዓዊ ጭካኔን ለትውልዱ ማስተማር

ቤተሰብን ማፍረስ በልጁና በወላጅ መካከል ያለውን የእሴት ግንኙነት በመበጠስ፣ ልጁ ለወላጁ ሳይኾን ለ”መብት ተሟጋቾች” ታማኝ ማድረግ፤

ከፈጣሪ መለየት፡- የነፍስ ፈጣሪውን፣ ባለቤቱን ሥራ በማፍረስ አመጸኛ በማድረግ በአጋንንት ሥራ መተባበር፤

ከተፈጥሯቸው መነጠል፡- ሴት ያደረገ ተፈጥሮአውዊ ጸጋቸውን እንዲጠሉት፣ እናት ያደረገ ሚናቸውንም እንዲጠየፉትና እንዲጥሉት ማድረግ፤

የገበያ ሸቀጥ ማድረግ፦ ልጆችን ውርጃና ለተለያዩ የወሊድ መቆጣጠሪያ መድኃኒቶች መደበኛ ደንበኛ ለማድረግ ታቅዶ የሚሠራ ነው።

የአባቶቻችንን እሴት የሚንድ፣ ትውልድን ለባዕድ ገበያ አሳልፎ የሚሰጥና የልጆቻችንን ንጽሕና የሚያረክስ ማንኛውም “ትምህርት” በኢትዮጵያ ምድር ቦታ ሊኖረው አይገባም።

እኛ አባወራዎች ልጆቻችንን የምናንጸው በራሳችን ባህልና እምነት እንጂ በእነዚህ ትውልድን አጥፊ ማኅበረሰብን አምካኝ ተቋማት እና እነርሱ በገንዘብ በሚደግፏቸው “ሊቃውንት ጥናትና ምክር” አይደለም!




Post a Comment

0 Comments