(ክፍል-ሶስት)
ጥቁር አስማት (black magic) ተብሎ የሚጠራው አስማት እርኩሳን መናፍስትን በመሳብ የሚሰራ በሰው ልጅ አካላዊ እና የሞራላዊ ከፍተኛ ጉዳት የሚያደርስ የአስማት አይነት ነው። አንዳንዷች ምህታታዊ በሆነ መንገድ ቤታቸው ፈረሶ፤ ትዳራቸ ተበትኖ፤ እንዳያገቡ ካገቡም በሰላም እንዳይኖሩ፤ ማህጸንን በመዝጋት እንዳይወልዱ፤ ገንዘባቸው ኪሳቸው ሳይገባ አልቆ፤ ቤተሰቦቻቸውን አጥተው፤ እጂግ ግራ በሚገባ ሂወት መፍትሔ ጠፍቶቸው ሲዋትቱ እናያለን። ለዚህም ነው ክርስትያን ከሚታየው አለም ሳይሆን ከማይታዩ
መናፍስት ጋር ነው ትግላችን የሚባለው፤ በዚህም ምክኒያት ነው ሰው ከጾም እና ከጸሎት ሂወት ውጭ መሆን እንደማይገባው ቤተክርስቲያን የምታስተምር። ይህ ምትሀታዊ አሰራር ላልደረሰበት የህልምና የቅዠት አለም ሊመስለው ይችላል ለምን እንዴት እና በምን የሚሉ ጥያቄወችን ይጠይቃል።
መጽሀፈ ሄኖክ በምዕራፍ 2 እንደሚነግረን ከወረዱት ከመላክ ወገን ሁለት መቶዎቹ የስማዝያ ነገዶች ዛሬም ድረስ በአለማችን ላይ በሰፊው የሚተገበርን ክፉ ስራ ሁሉ ለሰው ልጆች የማይገባ የተለያዩ የረቀቁ ሚስጥርን ገልጠዋል አስተምረዋል፡፡ ከነዚህ መካከል አሚዛራክ የተባለው መንፈስ ለሰው ልጆች ያስተማራቸውን የጥንቆላ ምትሃትና ጥቁር አስማት አለ። ይህ አስማት ነው እንግዲህ ዛሬም ድረስ በአንዳንድ የሀይማኖት ሰባኪያን ጭምር ዛሬ ላይ የምንመለከተው። ታዲያ ይህ ምትሀታዊ ተግባር የሚፈጸምበት ራሱን የቻለ መንገድ አለው በእርግጥ እንደ ሚስቡት መንፈስ ገቢሩም ይለያያል። ይህ የአሚዛራክ አስማት ለስጋቸው ያደሩ ከክፉ መናፍስት ጋር የሚተባበሩ ቃል እስከ መገባባት፣ ልጆቻቸው መስዋዕት እስከመስጠት የሚደረሱ በርካታ ግለሰቦች ዛሬም በሀገራችን አሉ። በእርግጥ መንፈስ ቅዱስ ሰለሞናዊ ጥበብን ገልጦላቸው ጥበባዊ በሆነ መንገድ አጋንትንን ሳይስቡ ከምታት በጸዳ መልኩ ጥበብን የሚራቀቁባት መላዕክትን እሰከ ማውገዝ የደረሱ ጠቢባን ነበሩን። ዛሬም በጥቂቱ አይጠፉም ለማገኘት ቢያዳግትም በርካታ ጤናማ የጥበብ መንገዶች ዛሬም ድረስ አሉ። ነገር ግን ይህን ክፉ ስራ ለመስራት ከሚጠቀሙበት እና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ሊቃውንት አባቶች አውግዘው ከለዩዋቸው መጽሀፍት መካከል አሰገደ መላእክ፣ ሰይፈስላሴ፣ መልክአ ሳጥናኤል ወዘተ የተባሉት መጽሀፍት ተጠቃሽ ናቸው፡፡ በዚህ የተካኑ ሰዎች ሰማያዊ መናፍስትን ወደነርሱ ለማቅረብ እና ለመዋረስ ይጠቀሙበት የነበረውን ጥብብን መሰረት ተደርጎ የተዘጋጀ የጥበብ መጽሀፍ ነው። ይህ መጽሀፉ ታዲያ የሚያዘውን ገቢር እየፈጸሙ መጽሀፉን ሲጠቀሙ የሚፈልጉት መንፈስ እንደሚጠሩ እንደሚቀርባቸው ይነገራል፡፡ ከስንዴ ውስጥ እንክርዳድ እንደማይጠፋ ሁሉ እኛም ሀገር ውስጥ እኚህን መጽሀፍ እና መጽሀፉ ውስጥ የሚገኙትን ጥበባት ተጠቅመው አስማታዊ በሆነ መንገድ ያልተገባ ነገር የሚያደርጉ ግለሰቦች በርካቶች ናቸው፡፡ #ነጮቹ_ፍሪማስነሪዎች መናፍሱትን ከሰው ልጅ ጋር ለማዳቃል የመጀመርያው እርምጃ መናፍስቱን ማቅረብ በመሆኑ ይህን ለማድረግ እነኝህን አሰገደ መልአክ.... የተሰኙትን መጽሀፍ ተጠቅመዋል፡፡ በነዚህ መጽሀፍ ተጠቅመው ከሰው ልጅ ጋር ግኑኝነት እንዲፈጽሙ ከሚያቀርቧቸው መናፍስት መካከል: ራሄሎ፣ ዲና ፣ ወለተወርቅ ጁፋር ዛቢል.......
የተሰኙ እና ሌሎቹም መናፍስት ይጠቀሳሉ፡፡ እነዚህ መናፍስት የሴት መናፍስት ሲሆኑ በሰው ልጆች ላይ የዝሙት ፈተናን ያሳድራሉ።
ለሰይጣናዊ ተግባር ራሳቸውን ያስገዙ ሰዎችም ዝሙትን ምክንያት በማድረግ የሰውን ትዳር ለማፍረስ እነዚህን መናፍስት ከላይ የተጠቀሰውን መጽሀፍ ላይ የሚገኘው ጥበብ ላልተገባ ነገር በማዋል መናፍስቱን በተለይም #ራሄሎ እና #ዲና የተባሉትን መናስፍስትን በማቅረብ ወደ ወንዱ ወይም ወደ ሴቷ ይህን መንፈስ ያሰርጻሉ፡፡ ታዲያ እነዚህ መናፍስት የሰረጹበት ግለሰብ የአመንዝራነት ሱሰኛ አድርገው ግልሰቡን/ግለሰቧን ከትዳራቸው ውጪ እንዲልከሰከሱ ያደርጓቸዋል በዚህም የተነሳ ትዳራቸው ለአደጋ ይጋለጣል፡፡ በዚህ #ጎለም በተባለው አስማት አማካኝነት የሰው እና #የሮሃንያ ወይንም የዛር መናፍስት ዝርያ ሆነው ከተፈጠሩት ፍሪማስነሪ ግለሰቦች አብዛኛዎቹ ታዋቂ ግለሰቦች እንደሆኑ ይነገራል። አንዳንድ የአሜሪካን ፕሬዝዳንቶች ቤተሰብ እና የእንግሊዝ ነገስታትን ቤተሰቦችን እንዲሁም የአንዳንድ የሃይማኖት ድርጅት መሪዎች የነዚህ የዛር መናፍስት ድቅያዎች ናቸው፡፡ እስቲ እነዚህ የአስማት አይነቶች ከፋፍለን ሰዎችን እንዴት ለመጉዳት እንደሚጠቀሙበት ለማየት እንሞክር።
1. መቅትል(ገዳይ አስማት) ምንድነው?
መቅትል የሚለው ቃል፥ቀተለ፥ገደለ፥ነፍስ አሳለፈ ከሚለው የግዕዝ ቃል የተወሰደ ነው። ይህ አስማት ሰውን ለመግደል ጠንቋዮች የሚጠቀሙበት አስማት ነው ተብሎ በመናፍስቱ አለም ይነገራል።
እግዚአብሔር አምላኩን ክዶ፥ ሰይጣንን አምኖ፥ የተዋረሰ ጠንቋይ፥ የዲያብሎስን ስም ደጋግሞ በመጥራት፥ ህንፃ ስላሴን ለማፍረስ ይጠቀምበታል።
አንዳንድ ጠንቋዮች እንዲሞት የሚፈልጉትን ሰው ስም በየቀኑ 49ጊዜ ደጋግመው ችፍርግ በተባለችው የእጽዋት ሥር ላይ ይጠራሉ። ከዛም ያቺ የተደገመባትን የችፍርግ ቁጥቋጦ ሥሯን ወደ ግራ በመጠምዘዝ፥ለ 7ቀናት ሲደግሙባት ከቆዩ በኋላ ሰውዬው እንዲሞት ከፈለጉ ሥሩን ይቆርጣሉ። እንዲታመም ከፈለጉ ደግሞ ሥሩን ወደ ግራ በመጠምዘዝ ድንጋይ ጭነው ይተውበታል።
ሌሎች ጠንቋዮች ደግሞ የሰይጣን ስም ደጋግመው በመጥራት የደገሙበትን ገዳይ ድግምት ከምግብ እና ከመጠጥ ጋር ለሰዋች በመስጠት ሰዎችን ይገሉበታል።
በዚህ ሁኔታ የተጠቃው ሰው ወደ ሆስፒታልም ሆነ ወደ ባህላዊ ህክምና ሔዶ መዳን አይችልም። ምክንያቱም የመናፍስት አሠራር ስለሆነ። ይህ ተጠቂ ሊድን የሚችለው ከስም ሁሉ በላይ በሆነው በአምላካችን ኢየሱስ በክርስቶስ ስም ብቻ ነው።
ጥላ ወጊ፦ ሌላው ደሞ በጥቁር አስማት ሥር ከሚጠቀሱት ነገሮች አንዱ ጥላ ወጊ የሚባለው የመናፍስት አሠራር ነው። ይህ ድግምት ከድግምቶች ሁሉ እጅግ የከፋ እና ፋታ የማይሰጥ ወይንም ወድያውኑ በመግደል የሚታወቅ ነው።
እግዚአብሔርን ክደው ለሰይጣን የተገዙ ስዎች በቀጥታ ከመናፍስት ጋር በመገናኘት የሚሰሩት ስራ ነው። ጠንቋዮቹ ሊገድሉት የሚፈልጉትን ሰው 15 ቀን ባልሞላው ጊዜ ውስጥ እንዲሞት ለማድረግ ሲፈልጉ የጥቁር ድመት ኩስ፣ የጥቁር አሞራ ራስ፣ የቄብ ዶሮ እንቁላል፣ 40ቀን ያልሞላው የሕፃን ልጅ የመቃብር አፈር፣ የተደቆሰ የሽኮኮ ጥርስ... ወዘተ አንድ ላይ በማዋሀድ ቢያንስ አምስት አንጓ ያለውን ሸምበቆ በማዘጋጀት የሚሰራ ሲሆን ሸንበቆውን ሲቆርጡት እንዲሞት የሚደገምበት ሰው ስም እየጠሩ "ቆረጥኩህ፥ ቆረጥኩህ" እያሉ ይቆርጡታል። የሚቆረጥበት ጊዜም የተወሰነ ነው ከሰዓቱ ውጪ ቢቆርጡት አይሰራም። የተደገመበት ሰው ወንዝ ተሻግሮ ቢሔድም ድግምቱ አይሰራም ብለው ያምናሉ።
ያሰቡት ተሳክቶ ድግምቱ ከሠራላቸው የተደገመበት ሰው በ15 ቀን ውስጥ ይሞታል ማለት ነው።
ይህን ድግምት የደገመው ሰው ሀሳቡን ቀይሮ ድግምቱን ልሻረው ሲል እንኳን ፈጽሞ የማይታሰብ ነው ብለው ያምናሉ።
ይህ ሰው መዳን የሚችለው የዲያብሎስን የነፍሰ ገዳይነት ሥራ ያፈርስ ዘንድ በተገለጠው የድንግል ማርያም ልጅ በሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው።
አንደርቢ፦ ምትሀት ማለት በጨለማ የሚወረወር ደንጊያ፣ ወርዋሪው የማይታወቅ በማዕድ ላይ የሚወድቅ ፋንድያ፣ አይነምድር፣ ጉድፍ ወዘተ ማለት ነው።
ይህንን የአንደርቢ ድግምት ከሌሎች የሚለየው ጠንቋዩ በቀጥታ ከዲያብሎስ ጋር ፊት ለፊት በመተያየት ልዩ ቃልኪዳን በመግባት የሚደገመው ድግምት በመሆኑ ነው።
የሚደገመው ድግምት መልክዓ ሳጥናኤል ሲሆን ይህንን ለመስራት የግድ ሰይጣንን መዋረስ ያስፈልጋል።
የአንደርቢ ድግምት/አስማት ድንበር ዘላይ የመናፍስት አሠራር በመባል ይታወቃል። ምክንያቱም አዲስ አበባ ሆኖ በአሜሪካ ሆነ በደቡብ አፍሪካ ድንበር ሳይከለክለው በየትኛውም የአለም ዳርቻ ከገጠር እስከ ከተማ ያለውን ሰው ማጥቃት በመቻሉ ነው። ተብሎ በጠንቋዮች ዘንድ ይታመናል።
የአንደርቢ ደጋሚዋች ቃልኪዳን ከሰይጣን ጋር!
ቅዱሳን ሰዎች የምሕረት የይቅርታ የማማለድ ቃል ኪዳን ከእግዚአብሔር ተቀብለው ትውልድ ሲጠቅሙ ጠንቋዮች ደግሞ የሞት የሲኦል የገሃነም እሳት የክፉ ስራና የአመጽ የእርኩሰት ቃልኪዳን ከሉሲፈር ይቀበላሉ። አንደርቢ ምትሃት ለማድረግ የሚያስችለውን ሰይጣናዊ ሃይል ለማግኘት የወሰነ ሰው የሚከተለውን ያደርጋል
1. አራት አይነት ዶሮዎችን ይዞ በመቅረብ ነጩን ዶሮ በምስራቅ ጥቁሩን በምዕራብ ቀዩን በሰሜን ዝንጉርጉሩን በደቡብ በኩል በማድረግ በ4ቱ ማዕዘን ታስረው እንዲቆዩ ይደረጋል
2.የሱዳን ሽቶ በክንፋቸው ላይ ይርከፈከፋል
3. ሰይጣን ከባህር ሲወጣ እንዳይመታው ተብሎ ከዶሮዎቹ ጋር ነጭ አረቄ ሰንደል ወይም ከርቤና ዕጣን ከእጅ ጋር ይያዛል።
4. መልክዓ ሳጥናኤል ይደገማል!
ከዚያ በኋላ ቃልኪዳን አግቢው መልክዓ ሳጥናኤል 49 ጊዜ የሚደገመውን ክፍል አንብቦ ሲጨርስ ወድያውኑ ሰይጣን በሰው መልክ ከባህር ይወጣል። ከዚያም ሰይጣን እንዲዋሃደው የፈለገው ሰው ማነጋገር ይጀምራል ማድረግ ያለበትን ሰይጣናዊ መመሪያዎችን ይነግረዋል። መመሪያውም 1ኛ ወደፊት ሰይጣን በሚገለጥለት ሰዓት ወይንም ሰይጣንን ናልኝ ብሎ በጠራው ሰዓት ምን አይነት ልብስ መልበስ የሚመስል ነገር እንጂ መልካም ነገር የለውምና።
በዚሁ መንገድ ሰውየው እና ሰይጣን ተስማምተው ተዋደው ይለያያሉ። ሰውየው እግዚአብሔርን ቅዱሳንን እየሰደበ እና ሰይጣንን ደግሞ እያሞገሰ መልክዓ ሳጥናኤልን እየደገመ ጠላቴ በሚለው ሰው ላይ የአንደርቢ መአትን ያመጣል ማለት ነው።
ጠንቋዮች/አስማተኞቹ በሰይጣን ቁጥጥር ሥር ውለው ቃልኪዳን ከፈፀሙ በኋላ በሰዎች ላይ የሚያደርሱት አደጋ!
በሰይጣን ቅኝ ግዛት ስር የወደቀቁ ሰዎች ሙሉ በሙሉ ራሳቸውን ለሰይጣን ሰጥተው ስለተዋረሱት ሰይጣን ለወዳጁ ቅርብ ነው እንዲሉ ቅርባቸው ብቻ ሳይሆን ውስጣቸው የሆነው ሰይጣን እግዚአብሔርንና ቅዱሳንን እየሰደቡ ሰይጣንን የሚያወድሰውን መልክዓ ሳጥናኤልን እየደገሙ በሚጠሉት ላይ የድንጋይ ናዳ ያዘንባሉ፤ በእሳት ቤቱን እና ሰውዬውን ያቃጥላሉ፤ ጉንዳን እና ዓይጥ እንዲወረው ያደርጋሉ፤ ቤቱን በትላትል በመሙላትና ሰውየው ምንም አይነት ምግብ እንዳይበላ እና በረሃብ እንዲሞት ለማድረግ ወጡና እንጀራውን ወደ ቆሻሻ ነገር ይለውጣሉ። በማንኛውም ቦታ ላይ ላይ ቀና ብሎ እንዳይሔድ ገፍትሮ የሚጥል መንፈስን ይመድባሉ ዓይንን ያሳውራሉ ሽባ ያደርጋሉ ያጎብጣሉ ያሳብዳሉ።
ይህንን ሁሉ መዓት በሰው እና በንብረት ላይ ለማድረስ 40 ቀን ያልሞላው የህፃን ልጅ የመቃብር አፈር የጥቁር ዶሮ ደም የጥቁር ድመት ዓይን በጥቁር ላም ቀንድ ውስጥ አድርገው ከ40 ክንድ በላይ ሳይርቁ ሊያጠቁት በፈለጉበት ሰው ቤት በመቅረብ ድግምቱን በመድገም ጠንቋዮች በሰው ላይ አደጋ ማድረስ እንችላለን ብለው ያምናሉ።
እመኑኝ ሰይጣን እግዚአብሔር በፍጹም ልባቸው ያመኑት ክርስቲያኖች ላይ ምንም አይነት ስልጣን የለውም።
ይቀጥላል
0 Comments