አሰገደ መልአክ

አንዳንዷች ምህታታዊ በሆነ መንገድ ቤታቸው ፈረሶ፤ ትዳራቸ ተበትኖ፤ እንዳያገቡ ካገቡም በሰላም እንዳይኖሩ፤ ማህጸንን በመዝጋት እንዳይወልዱ፤ ገንዘባቸው ኪሳቸው*ሳይገባ አልቆ፤ ቤተሰቦቻቸውን አጥተው፤ እጂግ ግራ በሚገባ ሂወት መፍትሔ ጠፍቶቸው ሲዋትቱ እናያለን። ለዚህም ነው ክርስትያን ከሚታየው አለም ሳይሆን ከማይታዩ መናፍስት ጋር ነው ትግላችን የሚባለው፤ በዚህም ምክኒያት ነው ሰው ከጾም እና ከጸሎት ሂወት ውጭ መሆን እንደማይገባው ቤተክርስቲያን የምታስተምር። ይህ ምትሀታዊ አሰራር ላልደረሰበት የህልምና የቅዠት አለም ሊመስለው ይችላል። ለምን እንዴት እና በምን የሚሉ ጥያቄወችን ይጠይቃል።

መጽሀፈ ሄኖክ በምዕራፍ 2 እንደሚነግረን ከወረዱት ከመላክ ወገን ሁለት መቶዎቹ የስማዝያ ነገዶች ዛሬም ድረስ በአለማችን ላይ በሰፊው የሚተገበርን ክፉ ስራ ሁሉ ለሰው ልጆች የማይገባ የተለያዩ የረቀቁ ሚስጥርን ገልጠዋል አስተምረዋል፡፡ ከነዚህ መካከል አሚዛራክ የተባለው መንፈስ ለሰው ልጆች ያስተማራቸውን የጥንቆላ ምትሃት አለ። ይህ ምታት ነው እንግዲህ ዛሬም ድረስ በአንዳንድ የሀይማኖት ሰባኪያን ጭምር ዛሬ ላይ የምንመለከተው። ታዲያ ይህ ምትሀታዊ ተግባር የሚፈጸምበት ራሱን የቻለ መንገድ አለው በእርግጥ እንደ ሚስቡት መንፈስ ገቢሩም ይለያያል። ይህ የአሚዛራክ ምታት ለስጋቸው ያደሩ ከክፉ መናፍስት ጋር የሚተባበሩ ቃል እስከ መገባባት፣ ልጆቻቸው መስዋዕት እስከመስጠት የሚደረሱ በርካታ ግለሰቦች ዛሬም በሀገራችን አሉ። በእርግጥ መንፈስ ቅዱስ ሰለሞናዊ ጥበብን ገልጦላቸው ጥበባዊ በሆነ መንገድ አጋንትንን ሳይስቡ ከምታት በጸዳ መልኩ ጥበብን የሚራቀቁባት መላዕክትን እሰከ ማውገዝ የደረሱ ጠቢባን ነበሩን። ዛሬም በጥቂቱ አይጠፉም ለማገኘት ቢያዳግትም በርካታ ጤናማ የጥበብ መንገዶች ዛሬም ድረስ አሉ። ነገር ግን ይህን ክፉ ስራ ለመስራት ከሚጠቀሙበት እና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ሊቃውንት አባቶች አውግዘው ከለዩዋቸው መጽሀፍት መካከል አሰገደ መላእክ የተባለው መጽሀፍ ተጠቃሽ ነው፡፡ በዚህ የተካኑ ሰዎች ሰማያዊ መናፍስትን ወደነርሱ ለማቅረብ እና ለመዋረስ ይጠቀሙበት የነበረውን ጥብብን መሰረት ተደርጎ የተዘጋጀ የጥበብ መጽሀፍ ነው። ይህ መጽሀፉ ታዲያ የሚያዘውን ገቢር እየፈጸሙ መጽሀፉን ሲጠቀሙ የሚፈልጉት መንፈስ እንደሚጠሩ እንደሚቀርባቸው ይነገራል፡፡ ከስንዴ ውስጥ እንክርዳድ እንደማይጠፋ ሁሉ እኛም ሀገር ውስጥ ይህን
መጽሀፍ እና መጽሀፉ ውስጥ የሚገኙትን ጥበባት ተጠቅመው ምታታዊ በሆነ መንገድ ያልተገባ ነገር የሚያደርጉ ግለሰቦች በርካቶች ናቸው፡፡ ስለ እኒህ ከባባድ የሰለሞናዊ ሆነ በአንጻሩም የምታታዊ ጥበቦች በተወሰነ መልኩ በዶር አለማየሁ ዋሴ መፅሀፍ በመርበብት ላይ ተገልፁዋል፡፡ ነጮቹ ፍሪማስነሪዎች መናፍሱትን ከሰው ልጅ ጋር ለማዳቃል የመጀመርያው እርምጃ መናፍስቱን ማቅረብ በመሆኑ ይህን ለማድረግ ይህን አሰገደ መልአክ የተሰኘው መጽሀፍ ተጠቅመዋል፡፡ በዚህ መጽሀፍ ተጠቅመው ከሰው ልጅ ጋር ግኑኝነት እንዲፈጽሙ ከሚያቀርቧቸው መናፍስት መካከል: ራሄሎ፣ ዲና ፣ ወለተወርቅ ጁፋር ዛቢል....... የተሰኙ እና ሌሎቹም መናፍስት ይጠቀሳሉ፡፡ እነዚህ መናፍስት የሴት መናፍስት ሲሆኑ በሰው ልጆች ላይ የዝሙት ፈተናን ያሳድራሉ።

ለሰይጣናዊ ተግባር ራሳቸውን ያስገዙ ሰዎችም ዝሙትን ምክንያት በማድረግ የሰውን ትዳር ለማፍረስ እነዚህን መናፍስት ከላይ የተጠቀሰውን መጽሀፍ ላይ የሚገኘው ጥበብ ላልተገባ ነገር በማዋል መናፍስቱን በተለይም ራሄሎ እና ዲና የተባሉትን መናስፍስትን በማቅረብ ወደ ወንዱ ወይም ወደ ሴቷ ይህን መንፈስ ያሰርጻሉ፡፡ ታዲያ እነዚህ መናፍስት የሰረጹበት ግለሰብ የአመንዝራነት ሱሰኛ አድርገው ግልሰቡን/ግለሰቧን ከትዳራቸው ውጪ እንዲልከሰከሱ ያደርጓቸዋል በዚህም የተነሳ ትዳራቸው ለአደጋ ይጋለጣል፡፡ በዚህ ጎለም በተባለው አስማት አማካኝነት የሰው እና የሮሃንያ ወይንም የዛር መናፍስት ዝርያ ሆነው ከተፈጠሩት ፍሪማስነሪ ግለሰቦች አብዛኛዎቹ ታዋቂ ግለሰቦች እንደሆኑ ይነገራል። አንዳንድ የአሜሪካን ፕሬዝዳንቶች ቤተሰብ እና የእንግሊዝ ነገስታትን ቤተሰቦችን እንዲሁም የአንዳንድ የሃይማኖት ድርጅት መሪዎች የነዚህ የዛር መናፍስት ድቅያዎች ናቸው፡፡


Post a Comment

0 Comments