(ክፍል-3)
አስማት በ3 ይከፈላል?
1. ጥቁር አስማት (Black Magic)
2. ነጭ አስማት (White Magic)
3. የተፈጥሮ አስማት (Natural Magic) ይባላሉ!
1. ጥቁር አስማት (black magic) ማለት ሰውን የሚጎዱ/ጎጂ ናቸው ከሚባሉት ለምሳሌ እንደ ርቢ፣ መስታአብድ፣ መስታሓምም፣ መስታጸልይ፣ መድፈነ ፀር፣ ሕይወት ማጥፋት፣ የንግድና የተለያዩ የስራ ቦታዎች ማዘጋት፣ ትዳር ሕይወት እንዳይሳካ ማድረግ ወዘተ ናቸው... ከዚህ ውስጥም መድፈነ-ፀር ትልቁን ቦታ ይይዛል ለዚህ ከምያገለግሉ አስማት ውስጥም #መልክአ_ሳጥናኤል ተጠቃሽ ነው።
2.ነጭ አስማት (white magic) ማለት ሌላ ሰዉን ሳይጎዱ የሰዎችን/የራስን ኑሮና ሕይወት ማስተካከል እንዲሁም በክፉ በመናፍስት የሚመጣን ጥቃት መከላከያ ማለት ነው!
ለምሳሌ መፍትሔ (ስራይ ሀብት ) ዐቃቤ ርዕሰ፣ ለማስታረቅ፣ ለፍቅር፣ ለትዳር፣ ዐይነ ጥላና ከለይ የተጠቀሱትን ጥቁር አስማት ለመከላከል የሚጠቅሙ ናቸው።
3. የተፈጥሮ አስማት (natural magic) የምባል ደግሞ ልክ እንደ ነጭ አስማት ሆኖ ግን ትንሽ ለየት ያሉ ተግባራት ማድረግ ዝናብ ማዝነብ፣ መሰወር፣ በደመና መሄድ በሰው ተቀባይነት እንድናገኝ ለማድረግ የመሳሰሉት ናቸው። የአስማት ነገር ከተነሳ እጅግ ጥልቅና ሰፊ ጊዜ ስለሚወስድ ለግንዛቤ ያህል ይሄ በቂ ይመስለኛል በመሀል በመሀል እየገባሁ አንዳንድ ነገሮችን እንደዚሁ እንማማራለን!
0 Comments