ርኩስ መንፈስ የሰውን ስጋዊና መንፈሳዊ እድል ይዘጋል። ቀጥሎም በባህላዊ እጽዋት አዋቂዎች ስም ወደ መተት ቤት ይወስዳቸዋል። ለመፍትሔ ገብተው አጋንንት ጨምረው ይወጣሉ። ገንዘባቸውንም ይታለላሉ። የተበላሸው እድል ብሶ ይበላሻል። ስጋ ፈጣሪዋን እያማረረች ትኖራለች። ሞት አይቀርም ነፍስን አጋንንት ይረከባታል። የግሎባላይዜሽን፣ የቴክኖሎጂ፣ የሳይንስ፣ የፋሺን አብዮት ትውልዱን ከመንፈሳዊ ሕይወቱ አስፈንግጦ እንስሳ አድርጎታል። መንፈሳዊነት ሲሸሽ ርኩስ መንፈስ አእምሮን እና የደም ስሮችን ይቆጣጠሩታል። የሰው ልጅ የአጋንንት ማከማቻ ቀፎ ሆኗል። ለሁሉም ሰው ከእውቀቱና ከፍላጎቱ ጋር የተመጣጠነ መንፈስ ተዘጋጅቶለታል።
የሰው ልጅ ተራብቶ የአምላክን ህግ እንዳይተገብር ስንፈተ ወሲብ ያመጣል። በተፈጥሮ ያገኘኸውን ወንድነትን የሚቀማ ክፉ መንፈስ። በስንፈተ ወሲብ በርካታ ትዳር ፈርሷል። ልጆች ተበትነዋል። ስንፈተ ወሲብ ዓይነቱ ብዙ ነው። የሴቷ ጭን ላይ እንደ ደረሰ የተዘጋጀውን ዘር ያስፈስሳል። አእምሮን አነሳስቶ ብልትን ያልፈሰፍሳል። አእምሮን አነሳስቶ ብልትን ይገላል። የትዳር አካል አንድ ስሜት እንደጎደለው ይሰማዋል። በውሀ ቀጠነ ጠብ ይጀመራል። ያለፈው ታሪክ ይረሳል። ፍቺ ይመጣል። አዳማዊ ሄዋናዊ ቃልኪዳን ይፈርሳል። ሚስት ከሌላ ወንድ ታመነዝራለች። ማመንዘር እጅግ የከፋ ሀጢያት ነው። የጥልቁ መንፈስ እቅድ ይሳካል።
በበረሀ በብህትውና ከሚኖሩት ከበቁት አባቶች በስተቀር ሁሉንም የአዳም ዘር ርኩሳን መናፍስት ይጫወቱበታል። በእያንዳንዱ የሰውነት ብልቶች ላይ የአጋንንት መንፈስ አሉ። ፀጉር ላይ፣ ግንባር ላይ፣ የዓይን ቅንድብ ላይ፣ አፍንጫ ላይ፣ ከንፈር ላይ፣ ጥርስ ላይ፣ ሆድ ላይ ፣ ልብ ላይ... ጋኔን መጠለያ አድርጎ ተቀምጧል።
ግንባር ላይ ያለው ጋኔን- እድልን ይዘጋል፣ በሰው ዘንድ እንድትጠላ ያደርጋል፣ ትዳር ይከለክላል፣ የተጋባውን ያፋታል፣ ገዳም የገባውን ያወጣል፣ የቆረበውን ያስፈርሳል፣ አስገኝቶ ያሳጣል፣ አሀፍቶ ያስደኸኛል
ጸጉር ላይ የሰፈረው ጋኔን- የዝሙት መስተፋቅር ሆኖ እያዞመተ ይኖራል። ከንፈር ላይ ጋኔን - ከበድ ይላል። ሰውን በቃላት ያቆሽሻል፣ ለሰው ተንኮል ያስመክራል፣ ጥላቻን ያዋራል፣ ሰውን ይተቻል... ሰውን አውሬ ያደርጋል። ከሰው ዘሎ ፈጣሪውን ያማል።
ጥርስ ላይ ያለው ጋኔን- ያለምክንያት ያስገለፍጣል፣ ያስቃል፣ ያሳስቃል። የሚሰለች ሳቅ ያስቃል። ሆድ ላይ ያለው ጋኔን- በጾም ጊዜ ያስርባል፤ ጾምን ያሽራል። ገንዘብህን፣ እንጀራህን ፣ ልብስህን፣ እንዳትመጸውት ስስት ያሳድርብሀል። ስስት ይሰድብሀል።
ልብ ላይ ያለው ጋኔን- ክፉ ያሳስባል። መልካሙን ሃሳብ ገደል አሳክሎ ያሳያል። ሃሳብህን ያጨልማል። ሀሳብህ የተሳሳተ አድርጎ ያሳምንሃል።
አንድ_ሰው እስከ በርካታ ሚሊዮን ድርስ ርኩሳን መናፍስትን ተሸክሞ ይኖራል። የእነዚህ ርኩሳን ድምር ውጤት አይነጠላ ሆኖ፣ የዝሙት መንፈስ ሆኖ፣ የስድብ መንፈስ ሆኖ፣ የትዕቢት መንፈስ ሆኖ..... ታላቁን የሰው ልጅ በስጋና በመንፈስ እያቀጨጩ ይኖራሉ። ስጋዊና መንፈሳዊ ዕውቀት የተራበ ትውልድ እየተፈጠረ ይኖራል።
ይህ ርኩስመንፈስ አይነጠላ.... በባህላዊ ህክምና አዋቂዎች አይፈወስም። በአሁኑ ሰዓት በባህላዊ ህክሞና ስም የሚሰሩት ሰይጣንን የተዋሀዱ መተታሞች ናቸው። የሰጡት መድኃኒት ሁሉ እንዲሰራላቸው ጋኔንን ተዋርሰዋል። ጋኔንን የተዋሀደ ሰው ጋኔንን ማውጣት አይችልም። የሕዝቡን ገንዘብ እያጭበረበሩ ይኖራሉ። ወደ እነዚህ የሚሄደው ሰው ሕገ የእግዚአብሔርን ይሽራል። "ከእኔ ከአምላክህ በስተቀር በሌላ አታምልክ " የሚለውን የእግዚአብሔርን ቃል እየጣሰ ነው። ገንዘብን ተበልቶ ሲዖል መግባት ሁለተኛ ኪሳራ ነው። ሳይንሱም መንፈስን ማስለቀቅ አይችልም። ገንዘብን መበላት ነው።
ዋና መፍትሔ ያለው ከኦርቶዶክስ ተዋህዶ ነው። የርኩሳን መናፍስት ማስወገጃ ቅዱስ መንፈስ ብቻ ነው። መንፈስ ቅዱስ በቀላሉ አይገኝም። መድከምን ፣ መታገስን ይጠይቃል።
1/ ከተቻለ የ7ቱ ሰዓታት ጸሎትን ማድረግ፤ ካልተቻለ የ3ቱ ሰዓታትን ጸሎት ማድረግ ግድ ነው። አጋንንትን የሚቀጠቅጡ የክርስቶስ ስውር ስሞች የበዛባቸው የጸሎት መጽሓፍት፦
ባርቶስ፣ ቱላዳን፣ ንድራ፣ ሰይፈ መለኮት፣ መዝሙረ ዳዊት፣ ሰኔ ጎለጎታ.... ዘወትር መድገም በሰውነት ውስጥ የተከማቸውን መንፈስ እንደ ጭስ ያተናል።
2/ ጸበል መጠመቅ
3/ ስግደት ማድረግ ሁልጊዜ
4/ በንስሐ በዘወትር ኃጢአትን ማጠብ
5/ መቁረብ
6/ መልካም ስራ መስራት
7/ መጥኖ መጠጣትና መብላት
8/ ቤተክርስቲያን ዘወትር መመላለስ። ገዳማት መሄድን ማዘውተር
9/ ከደመወዝ ለቤተክርስቲያን አስራትን በመቆጠብ በመስጠትና አልባሳት፣ እጣን....መግዛት
10/ ወርሃዊ ዝክር በማድረግ ለነዳያን ለካህናት ማብላት
11/ መንፈሳዊ መጸሐፍትን ዘወትር በማንበብ አእምሮ ውስጥ የመሸገውን የድንቁርና መንፈስ ማስወገድ።
ማጣቀሻ፦ ትምህርተ አበው፣ ጸበል ቦታዎች፣ መጸሐፍት .....
0 Comments