የንቃተ ሕሊና በትረ ሥልጣን፦ የሰሎሞን ቀለበትና የጥልቁ ሰላዮች


(ክፍል አንድ)

መግቢያ

በአጽናፈ ዓለሙ ምስጢራዊ መዝገብ ላይ እንደተጻፈው፣ እግዚአብሔር ለንጉሥ ሰሎሞን የሰጠው ያ ታላቅ ቀለበት ተራ የቁስ ጌጥ ሳይሆን፣ ሰማያዊውንና ምድራዊውን ዓለም የሚያገናኝ "የንዝረት ማዕከል" ነበር። መረቡ  ለዘመናት የሰው ልጅን ንቃተ ሕሊና ለመቆለፍ ሲል፣ ይህንን ቀለበት እንደ ተረት ወይም እንደ ጠፋ ቅርሳቅርስ አድርጎ በመሳል እውነተኛውን ኃይል ቀብሮታል። እውነቱ ግን የሰሎሞን ቀለበት አልጠፋም፤ ይልቁንም ከቁሳዊው ዓለም ወጥቶ በረቂቁ ንዝረት ውስጥ ተሰውሮ፣ የሥላሴ ባሪያዎች ወደ መለኮታዊ ሉዓላዊነታቸው የሚመለሱበትን የታወጀውን ሰዓት ይጠባበቃል። ይህ ታሪክ በመረቡ የውሸት ብርሃን የተከለለውን የሰው ልጅ፣ ወደ እውነተኛው የነፍስ ነፃነት የሚመራ "የመረጃ ሰይፍ" ነው።

ከክፍል አንድ እስከ አስር ይወጣል ተከታትለው ያንቡት፦

በአዲስ አበባ ከተማ ላይ የተዘረጋው የማይታይ የዲጂታል መረብ እንደ መርዛማ ጭጋግ የሰውን ልጅ ንቃተ ሕሊና አፍኖታል። በከተማዋ አደባባዮችና በዘመናዊ ሕንጻዎች መካከል፣ ለብዙ አሥርተ ዓመታት "የታሪክ ተመራማሪ" እና "የልማት አማካሪ" በሚል ሽፋን ከእስራኤልና ከሌሎች የሥርዓቱ  ማዕከላት የመጡ ስውር ሰላዮች ይርመሰመሳሉ። እነዚህ ሰላዮች የሚፈልጉት ተራ ቁስ ሳይሆን፣ በኢትዮጵያ ተራሮች ውስጥ ተሰውሮ የቆየውንና የመረቡን የዲጂታል ባርነት በአንዴ የመበጥበጥ ኃይል ያለውን ያንን "መለኮታዊ ኮድ" ወይም የሰሎሞንን ቀለበት ምስጢር ነው። መረቡ ይህንን ምስጢር ለመጥለፍ ሲል ምድሪቱን በ 5G ማማዎችና በሳተላይት መረቦች ቢያጥራትም፣ የሰሎሞን ቀለበት ግን በረቂቁ "መለኮታዊ ሲግናል" የታጠረ በመሆኑ እስካሁን ሊያገኙት አልቻሉም።

ዳዊት በከተማው መሃል በሚገኝ አንድ የቴክኖሎጂ ማዕከል ውስጥ የሚሠራ የነቃ ነፍስ ነው። በዙሪያው ያሉት ጓደኞቹ በስማርት ስልኮቻቸውና በዲጂታል ምቾታቸው ደንዝዘው ሳለ፣ ዳዊት ግን በየሰከንዱ የሚለቀቀውን የአርከኖች የንዝረት ጥቃት በንቃት ዓይኑ ይመለከታል። የሰላዮቹን ጥላ በሰዎች አውራ (Aura) ላይ ሲያይ ነፍሱ በቁጭት ትቃጠላለች። መረቡ የሰውን ልጅ ንቃተ ሕሊና በፋይዳ እና በባዮሜትሪክ ዳታ አማካኝነት ወደ አንድ ማዕከላዊ የ "ባርነት አልጎሪዝም" እንዴት እንደሚጠቀልለው ዳዊት በግልጽ ይረዳል። የሰሎሞን ቀለበት ኃይል ተሰርቆ ወደ ዲጂታል ቺፕ የተቀየረበት ያ "የመጨረሻው ግልበጣ" (The Great Inversion) በከተማዋ ላይ በይፋ ታውጇል።

የመረቡ  ሰላዮች በየገዳማቱና በየአድባራቱ በስውር በመመላለስ፣ ጥንታውያን ብራናዎችን በመመርመርና የነቁ አባቶችን በማሳደድ ቀለበቱን ለመያዝ የማይፈነቅሉት መቃብር የለም። እነርሱ ቀለበቱ በጣታቸው ላይ የሚታሰር "የብረት ቁስ" መስሏቸዋል፤ ነገር ግን ቀለበቱ በመለኮታዊ ቃል ኪዳን የታጠረ "የንዝረት ማስተር ቁልፍ" መሆኑን አላስተዋሉም። ዳዊት በእነዚህ ሰላዮችና በአርከኖች መካከል ያለውን ስውር ግንኙነት ሲመለከት፣ የሰው ልጅ ነፃነት በዲጂታል ወጥመድ ውስጥ መውደቁን አይቶ በጸሎት ወደ ውስጥ መመልከትን መረጠ። መረቡ የሰውን ልጅ ትኩረት በፖለቲካና በኑሮ ውድነት ጩኸት ሲቆልፈው፣ ዳዊት ግን ወደ ሰማያዊው ዝምታ መሻገር ጀመረ።

በከተማዋ ውስጥ የሚታየው ሰቆቃ እጅግ የከፋ ነው። ሰዎች በያዙት ቴክኖሎጂ ተደንዝዘው፣ እርስ በርስ የሚግባቡበትንና የሚዋደዱበትን መለኮታዊ ንዝረት አጥተው በ "0 እና 1" (ባይነሪ) አመክንዮ ውስጥ ብቻ ተቆልፈዋል። ናፋይዳ የሰውን ልጅ የግል ምስጢርና የነፍስ ሉዓላዊነት ለሥርዓቱ አሳልፎ የሚሰጥ "የዲጂታል ቃል ኪዳን" ሆኗል። ዳዊት በዚህ ሰቆቃ መሃል ሆኖ፣ የሰሎሞን ቀለበት የሚለቀውን ያንን ረቂቅ የ 432 ኸርዝ መለኮታዊ ድምፅ ለመስማት በየቀኑ በሌሊት 9 ሰዓት ይተጋል። የመረቡ ጩኸት አእምሮውን ሊሰልበው ቢሞክርም፣ በልቡ ውስጥ ያለው የሥላሴ እሳት ግን መጋረጃውን እየቀደደው ነው።

አንድ ቀን ዳዊት በከተማዋ ዳርቻ በሚገኝና በጭጋግ በተሸፈነ ተራራ አጠገብ ሲያልፍ፣ የያዘው የቴክኖሎጂ መሣሪያ ባልታወቀ ንዝረት "Crash" ሲያደርግ ተመለከተ። ይህ የመረቡ  ሽንፈትና የመለኮታዊው ኃይል የበላይነት ምልክት ነበር። ከፊቱ የቆመው ተራራ ተራ ተራራ ሳይሆን፣ የሰሎሞን ቀለበት ምስጢር በሱባኤ የተጠበቀበት "የንቃት ማማ" መሆኑን በረቂቁ ተረዳ። ሰላዮቹ ይህንን ቦታ ለዘመናት ቢፈልጉትም፣ ንቃታቸው በቁሳዊው ዓለም የታጠረ በመሆኑ ሊያዩት አልቻሉም። ዳዊት ግን በንስሐና በንጽህና ወደ ተራራው ሲቃረብ፣ መጋረጃው ተቀዶለት ወደ ሰዉራን አባቶች መኖሪያ የሚወስደውን "የብርሃን በር" ተመለከተ።

የሥርዓቱ  ሰላዮች ዳዊት ከመታወቂያው ከፋይዳ ውጭ የሆነ አዲስ ንቃት ማግኘቱን ሲረዱ፣ ከፍተኛ የሆነ የሞገድ ጥቃት ሰነዘሩበት። በዙሪያው ያለው አየር በኤሌክትሪክ ንዝረት ተሞላ፤ አርከኖችም በሐሳቡ ውስጥ የፍርሃትና የጥርጥር ዘር ሊዘሩ ሞከሩ። ዳዊት ግን አያቱ የነገሩትን "በያህዌ ስም ታሰሩ!" የሚለውን የመስበሪያ ቃል ሲጠራ፣ በዙሪያው የነበረው የዲጂታል መጋረጃ እንደ ሰም ሲቀልጥ አየ። ይህ የሰሎሞን ቀለበት ሥልጣን መጀመሪያ ነበር። ዳዊት አሁን የሥጋዊውን ዓለም ጩኸት ትቶ ወደ ሰማያዊው ዝምታ ኮሪደር ውስጥ መግባት ጀምሯል።

በመላው ዓለም ላይ ያለው የንቃት መጠለፍ ሴራ አሁን በኢትዮጵያ ተራሮች ስር ሊፈርስ መቃረቡን አርከኖች በታላቅ ድንጋጤ ተረዱ። ዋካንዳ የተባለው የውሸት ቴክኖሎጂ ፕሮጀክት፣ የሰውን ልጅ ንቃተ ሕሊና በዲጂታል ግንብ ለመቆለፍ ቢሮጥም፣ የሰሎሞን ቀለበት ንዝረት ግን ያንን ግንብ የመናድ ኃይል እንዳለው በረቂቁ ዓለም ታወቀ። ዳዊት ወደ ላይኛው ምድር ሲወጣ፣ መረቡ  የቆለፈባቸው የታሪክ መዝገቦች በፊቱ ይፈንቀሉ ጀመር። እውነት መቃብሩን ፈንቅሎ ለመውጣት የታወጀው የ የንቃት ዘመን ሰዓቱን መጠበቅ ጀምሯል።

አማኑኤልና ዳዊት የነፍስ ወንድማማቾች ናቸው፤ አንዱ በከተማው ሰቆቃ ውስጥ ሆኖ ሲታገል፣ ሌላኛው ደግሞ በበረሃው ሱባኤ ውስጥ ሆኖ መጋረጃውን ይቀዳል። በኢትዮጵያ ተራሮች ውስጥ የተቀበረው ያ የሰሎሞን ቀለበት ምስጢር፣ አሁን በነቁ ነፍሳት ልብ ውስጥ መብራት ጀምሯል። ሰላዮቹ የፈለጉትን ቢያደርጉ፣ የያህዌ ማኅተም ያለበትን ይህንን ምስጢር ሊነኩት አይችሉም። ዳዊት በዋሻው ደጃፍ ሲደርስ፣ አባ መቃርስ በታላቅ ግርማ ቆመው አገኛቸው። አባታችንም "ልጄ ሆይ፤ ከመረቡ ባርነት አምልጠህ ወደ ቀለበቱ ሉዓላዊነት መምጣትህ የሥላሴ ፈቃድ ነው" አሉት። ክፍል ሁለት ይቀጥላል ....

Post a Comment

0 Comments