ታቦት እና መሠዊያ ምን አገናኛቸው?


ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ታቦቱ መሠዊያ ነው ብላ ስታሰተምር ፤ በብሉይ ኪዳን የነበረው የቃልኪዳኑ ታቦትና መሠዊያ ይለያያል አሁን ይዛቹ የምትወጡት ታቦት ብላቹ የምትጠሩት መሠዊያ ነው ካላቹ ታቦት ማለቱን አቁሙና መሠዊያ በሉት ለሚል ልብ አልፉ ክርክር በፕሮቴስታንት ይነሳል ለዚህ ጥያቄያቸው #ከ1700 አመታት በፊት ተመልሷል።  ቅዱስ አምብሮስ የአዲስ ኪዳኑን መሠዊያ ቀጥታ የቃል ኪዳኑ ታቦት ሀምሳል ሚስጢራዊ ውክልና እንዳለው እንዲህ በግልጽ አሰቀምጦታል።

የቅዱስ አምብሮስ ንባብ (ከ 339 — 397 ዓ.ም) የነበረ አባት ነው ።የቃል ኪዳኑ ታቦት ለአዲስ ኪዳኑ መሠዊያ ቀጥተኛ ሚስጤር ሲያብራራ ከዛሬ 1ሺህ 7መቶ አመት በፊት እንዲህ ብሏል

​"ጥንታዊው ታቦት ምን እንደነበረ ተመልከት፤ በውስጡም መና ነበረበት። ነገር ግን ያ ታቦት የዚህ (የሐዲስ ኪዳን) መሠዊያ ምሳሌ (Figure) ነበረ። ታቦቱ በውስጡ የእግዚአብሔርን ሕግ ይዞ ነበር፤ ይህ መሠዊያ ግን የሕጉን ራስ የሆነውን የክርስቶስን ሥጋ ይዟል። በታቦቱ ላይ ደም ይረጭ ነበር፤ በዚህ መሠዊያ ላይ ግን የክርስቶስ ደም ይፈስሳል።

​በዚያ ድንኳን ውስጥ የነበረው ታቦት 'የስርየት መክደኛ' (Propitiatory) ነበረው፤ ይህም መሠዊያ (Altar) የስርየት ስፍራ ነው። ያ ታቦት በእግዚአብሔር ኃይል የተሠራ ነበረ፤ ይህ መሠዊያ ግን በመለኮታዊ ጸጋ የተሞላ ነው። ስለዚህም ያ ታቦት የዚህ መሠዊያ ጥላ ነበር።"

​"Consider what the Ark of the Covenant was, in which was the manna. But that Ark was a figure (type) of this Altar. In the Ark was the Law, on the Altar is Christ. In the Ark was the tablet of the testimony, on the Altar is the body and blood of the Lord... The Ark was the shadow, the Altar is the truth."

ለምን መሠዊያ አለው?

​ቅዱስ አምብሮስ በመቀጠል እንዲህ ይላል፦
​"ታቦቱ መሠዊያ ተብሎ መጠራት ያለበት፣ በላዩ ላይ የሚቀርበው መሥዋዕት (ደም) የእግዚአብሔርን ቁጣ የሚያበርድና ለሕዝቡ ስርየትን የሚያመጣ በመሆኑ ነው። ዛሬም በቤተክርስቲያን መሠዊያ ላይ የምንሰዋው መሥዋዕት ያንን እውነት ይገልጻል። "ቅዱስ አምብሮስ ታቦቱን "የመሠዊያ ጥላ" (Shadow/Figure of the Altar) በማለት ይገልጸዋል። በአይሁድ ሥርዓት ታቦቱ ላይ ደም መረጨቱ፣ ታቦቱን እንደ "ውስጣዊ መሠዊያ" (Inner Altar) እንዲቆጠር እንዳደረገው በሰፊው ይተነትናል።

​ይህ የቅዱስ አምብሮስ ትምህርት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን "ታቦት" እና "መሠዊያ" ለአንድ አገልግሎት (ለቅዱስ ቁርባን) እንደሚውሉ ከሚገልጸው ትምህርት ጋር ፍጹም ይስማማል።

​ይህ ትምህርት የት ይገኛል? (Sources) ይህንን ንባብ በሚከተሉት የታወቁ የእንግሊዘኛ ጥራዞች ውስጥ ማግኘት ትችላለህ፦

​The Nicene and Post-Nicene Fathers (NPNF): Series II, Volume 10 (St. Ambrose: Select Works and Letters).

​CUA Press (The Fathers of the Church series): Volume 44, "Saint Ambrose: Theological and Dogmatic Works".

​Online Sources: እንደ New Advent ወይም CCEL ባሉ ድረ-ገጾች ላይ "St. Ambrose On the Sacraments" ብለህ ብትፈልግ ሙሉውን ንባብ ታገኘዋለህ።

Post a Comment

0 Comments