ያሳትኋቸው ሰዎች ከኔ ጋራ ወደ ገሃነም ይወርዱ ዘንድ ከፈጠረኝ ከእግዚአብሔር መሐላ አለኝ። የአዳምን ልጆች እንደ ወፍ ጫጩት ጨብጬ እይዛቸዋልሁ።
ከቀናች ከሕገ እግዚአብሔር አርቃቸዋለሁ። ወደ ገሃነም ሊሄዱ ጐጣጉጥ ወደ ሆነ ጐዳናም እመልሳቸው ዘንድ ምክንያት እሆናለሁ። ከጌታቸው ሕግ ወጥተው የሳቱ ሰዎች ግን ወደኔ ይመጣሉ። እኔንም ይወዳሉ መሐላዬንም ይጠብቃሉ እኔ ልቡናቸውን እከፋለሁና ወደ ፈጣሪያቸው ወደ እግዚአብሔር እንዳይመለሱ አሳባቸውንም እለውጣለሁና...።
እኔ እንዳዘዝኳቸው ትእዛዜን ያደርጋሉ። የዚህን ዓለም ገንዘብ ባሳየኋቸውም ጊዜ ከቀናች ሕግ ልቡናቸውን አስታለሁ።
ቆንጆችንና መልከ መልካም ሴቶችንም ባሳየኋቸው ጊዜ በነዚህ ከቀናች ሕግ አርቃቸዋለሁ። የሚያበሩ የህንደኬ ዕንቈችንም ብርና ወርቅንም ባሳየኋቸው ጊዜ ወደኔ ሥራ ይመለሳሉ።
ቀጭን ልብስን ቀይ ሐርንና ነጭ ሐርንም ግምጃንና ነጭ ሐርንም ባሳየኋቸው ጊዜ በዚህም ከቀናች ሕግ አርቃቸዋለሁ።
ገንዘብን ከብቶችንም እንደ አሸዋ አብዝቼ ባሳየኋቸው ጊዜ በዚህም ወደኔ ሥራ እመልሳቸዋለሁ። በትዕቢት ስለ ሴቶችም ስለ ቁጣና ስለ ጠብም የሚደረግ ቀናትን ባሳየኋቸው ጊዜ በዚህ ሁሉ ወደኔ ሥራ እመልሳቸዋለሁ።
ማደሪያዬንም ላደረኳቸው ሰዎች ምልክትን አሳያቸዋለሁ በከዋክብት አካሄድም ቢሆን በደመና መውጣትም በእሳት ማናፋትም ቢሆን በአውሬዎችና በወፎችም ጩኸት ቢሆን እነሳቸው ማደሪያዎቼ ናቸውና በዚህ ሁሉ በልቡናቸው ምልክቶችን አሳድርባቸዋለሁ።
መጽሐፈ መቃብያን ፫ ምዕራፍ ፩ ከ፩-፮/
0 Comments