ኢራን ዘመናዊ መሳሪያዎች ብትታጠቅም #የእስራኤልን የደህንነት ተቋም መቆጣጠር አልቻለችም!
"መፍትሄ ማምጣት ካልቻልክ የችግሩ አካል ነህ" ይላሉ የሞሳዱ ዳይሬክተር ኤሚት....
- ሞሳድ መንፈስ ነው። የማይገኝበት የምድራችን ቦታ የለም።
- በዘመቻ አልማዝ፦ አዲሱን የራሽያ ሚግ- 21 ከራዳር ቁጥጥር ውጭ በመብረር ከኢራቅ መንግስት ሰርቀውታል።
- ከፈረንሳይ ሸርቡር ወደብ ዘመናዊ ሚሳየል የተገጠመላቸውን የጦር መርከቦች ያለምንም ኮሽታ ሰርቀውታል።
- በዘመቻ ፕላምበት፦ 200 ቶን የሚመዝን ውድ ዩራኒየም ማንም ሳይነቃ ከአውሮፓ ሰርቀዋል። ይሞታል እንዴ?
ሞሳዶች እንዲህ ይላሉ " አንድ የመሥክ ሰላይ ከሙሉ ባላቲዎን ሠራዊት ይበልጣል " በትክክልም በተግባር አሳይተውታል።
የኤሊ ኮኸን ገድል በሶሪያ ምድር ድንቅ ነበር። እስራኤል የጎላን ተራራዎች ከሶሪያ ላይ በቁጥጥር ስር ታውል ዘንድ ኤሊ ኮኸን በደማስቆ ሰይጣን መሆን ነበረበት።
ኤሊ ኮኸን በጠላት ቀጠና (በሶሪያ) ምክትል የመከላከያ ሚኒስቴር ለመሆን ተቃርቦ ነበር። እስራኤላውያን ኤሊ ኮኸንን "የኛ ሰው በደማስቆ " እያሉ ዝንት ዓለሞ ሲያደንቁት ይኖራሉ።
ወልፍጋንግ ደግሞ ወደ ግብጽ የተላከ የእስራኤል ሰይጣን ነበር። የቤተ-መንግስት ባለሟል ለመሆን ጊዜ አልወሰደበትም ነበር። ለማንም የማይፈቀደውን የግብጽን ወታደራዊ ምስጢር እንዲጎበኝ ተፈቅዶለታል። እስራኤላውያን "በካይሮ የቴላቪቭ አይን" ይሉታል።
-በ6ቱ ቀን የእስራኤልና የአረቦች ጦርነት የግብጽን የጦር ጀቶች (ሚጎች) በራሳቸው አዘዋቸዋል። የግብጽም የጦር መኮንኖች በመምሰል የግብጽን የምድር ጦር በመምራት ትእዛዝ ሰጥተዋል።
በሲናይ በርሃ ከሂሊኮፍተር ላይ የሚወረወሩት የእስራኤል ኮማንዶዎች የዓለምን ሕዝብ ቆሞ እንዲያጨበጭብ አስገድደውታል ... የዚህ የአርያን ሻሮን የጦር ንድፍ በአሜሪካንና በአውሮፓ በሚሊታሪ አካዳሚዎች እንደ አንድ ትምህርት ይሰጣል።
የያሲር አረፋትን ምክትል "አቡ ጀሀድን " በቱኒዚያ ለመግደል የውጭውን በር ሰብረው፣ ሹፌሩን ገድለው ፣ ሁለቱን ጠባቂዎቹን ገድለው፣ ሳሎኑን አልፈው ማንበቢያ ክፍሉ ገብተው ለመግደል ያቀዱት 22 ሰከንድ ሲሆን እነሱ ግን በ13 ሰከንድ ኦኘሬሽኑን ጨርሰውታል። መንፈስ ነገር ናቸው።
90 ደቂቃ በኢንተቤ
በመካከለኛው ሌሊት አራት የጦር ጀቶች፣ ሁለት ቦይንግ የህዝብ አውሮኘላን ፣100 ኮማንዶዎች የአረቡን የአየር ክልል እየሰነጠቁ ፤ ከራዳር ክልል ውጭ እየተወነጨፋ ዩጋንዳ ኢንቴቤ ከተማን ወረሯት... በ30 ደቂቃ አስደናቂ ጦርነት የዪጋንዳ ሚጎችን ወደ አፈርነት ቀየሩት... ሁለተኛው ግሩኘ በዮናታን ናታኒያሁ የአሁኑ ጠቅላይ ሚኒስቴር የቢኒያሚን ናታኒያሁ ታላቅ ወንድም የሚመራው ቡድን የታገቱትን ይሁዲዎች ካስለቀቀ በኋላ... አጠቃላይ በ90 ደቂቃ ውስጥ የጽዮናዊቷን ሀገር ተልእኮ በድል አጠናቀው ወደ ቴላቪቭ በጀግንነት ሲመለሱ ላዬ የጽዮንን ልጆች አለማድነቅ ክፋት ይሆናል።
ቴክኖሎጂ
ከ2006 እ.ኤ.አ በፊት ሞሳድ በከፍተኛ ጥበቃ የተቆለፉ ኮምፒተሮችን በመሥበር ዳታውን የሚገለብጥ "ቴምፐስት" የተባለ ረቂቅ መሣሪያ ፈጥረዋል።
ስማርት ዳስት..የጉንዳን መጠን ያላቸው መሳሪያዎች ሲሆኑ በጠላት ቀጠና ያለውን ማንኛውንም ድምጽ ቀርጸው ለሞሳድ ቢሮ ይልካሉ። ከአንድ ወር በኋላ እራሳቸውን ያጠፋሉ።
ሀገርን ለመሥራትና ለማጠናከር የደህንነቱን እና የስለላ ተቋማትን ማጠናከር የህልውና ጉዳይ ቢሆንም #የኢትዮጵያው ግን የተቋቋመው ዜጎቹን ለማዳን ሳይሆን ለማሰቃየት ነው።
0 Comments