✍ ዮሐንስ አብነት አጉማስ
ይህ በውጫዊ ገጽታው "አካባቢን መጠበቅ" ቢመስልም፣ በጥልቅ ንቃተ-ሕሊና ሲመረመር የሚከተሉትን 4 አጀንዳዎች ይዟል ተከተለኝ ልስጥህ እኛ ጋ ምታመልጥ ነገር ስለለች፦
የቁሳቁስ ቁጥጥር ልምምድ ፦ ሥርዓቱ (Matrix) የሰውን ልጅ ለትላልቅ ትእዛዞች ለማዘጋጀት መጀመሪያ ጥቃቅንና በዕለት ተዕለት ሕይወት ውስጥ ያሉ ነገሮችን ይከለክላል። ይህ "ፔስታል" መከልከል፣ ነገ ለሚመጡት ጥብቅ የዲጂታልና የባዮሜትሪክ ቁጥጥሮች ሕዝቡ ትእዛዝን ያለ ጥያቄ የመቀበል ሥነ-ልቦናዊ ዝግጅት እንዲያደርግ ነው።
የመረጃ መከታተያ ፦ ስስ ፔስታሎች "Identity" የላቸውም። ሥርዓቱ ግን የሰው ልጅ የሚገዛቸውና የሚጠቀማቸው ቁሶች በሙሉ በባርኮድ (Barcode) የተመዘገቡና ተከታታይነት ያላቸው እንዲሆኑ ይፈልጋል። ይህ ወደፊት "Carbon Footprint" (የሰው ልጅ በምድር ላይ የሚያሳርፈው የፍጆታ መጠን) ለመለካትና በዚያው ልክ ግብር ለመጣል።
የኢኮኖሚ መጋረጃ፦ የብር ቅጣት መቀመጡ፣ በሕዝቡ ውስጥ "የፍርሃት ንዝረት" (Frequency of Fear) ለመፍጠር ነው። ፍርሃት ባለበት ቦታ ደግሞ ንቃት አይኖርም። የሰውን ልጅ ትኩረት በዕለት ተዕለት ሕልውና እና በቅጣት ስጋት ላይ በማሰር፣ ከመንፈሳዊ ንቃቱ እንዲዘናጋ ማድረግ ነው።
ማስረጃ ፦ ይህ አሠራር ዓለም አቀፋዊው "Sustainable Development Goals" (SDGs) አካል ሲሆን፣ ዓላማው የሰውን ልጅ የግል ምርጫና ነፃነት ደረጃ በደረጃ በማጥበብ ወደ ማዕከላዊ ቁጥጥር ማምጣት ነው።
መፍትሔ
የባሕርይ ቁስን መመለስ
በጥንት አባቶቻችንና እናቶቻችን ዘንድ የነበሩትን እንደ ዘነቢል (ከሸምበቆ የሚሠራ)፣ አቆማዳ (ከቆዳ የሚሠራ) ወይም ከጥጥ የሚሠሩ ዘላቂ ከረጢቶችን መጠቀም መጀመር።
ምስጢሩ፦ እነዚህ ተፈጥሮአዊ ቁሶች ከምድር ጋር ያላቸው ንዝረት ሕያው ነው። ምግብህን በእነዚህ ቁሶች ውስጥ ስታስቀምጥ፣ ምግቡ መለኮታዊ ኃይሉን አይሰርቅም። ፕላስቲክ ግን የምግብን ንዝረት ይገላል ያደርጋል።
የ"ፍርሃት ንዝረት" ማምከኛ
የብር ቅጣት አዋጅ ዋና ዓላማው ገንዘብ መሰብሰብ ብቻ ሳይሆን በሕዝቡ ልብ ውስጥ "ጭንቀትን" መዝራት ነው። ጭንቀት ደግሞ የሰው ልጅን የንቃት ድግግሞሽ ዝቅ ያደርጋል።
መፍትሔ፦ ሕጉን በአካላዊ ደረጃ አክብሮ (ፔስታል አለመያዝ)፣ ነገር ግን በውስጣዊ ማንነትህ "በዚህ ትእዛዝ አልሰበርም" የሚል የንቃት አቋም መያዝ።
ምስጢሩ፦ ሥርዓቱ የሚደሰተው ስትበሳጭና ስትፈራ ነው። አንተ ግን በዝግጅትና በፈገግታ ተፈጥሮአዊ አማራጮችን ስትጠቀም፣ የሥርዓቱን "የኃይል መጠጫ"ትዘጋዋለህ።
የጋራ ትብብርና የ "ባርተር" ንቃት
ይህ እስራት የሰው ልጅን ወደ ዲጂታል ግብይትና ወደ ማዕከላዊ ቁጥጥር ለመግፋት አንዱ መንገድ ነው።
መፍትሔ፦ በማኅበረሰብ ደረጃ መረዳዳትን ማጠናከር። ለምሳሌ፦ ግሮሰሪዎችና ሱቆች የራሳቸውን የወረቀት ወይም የጨርቅ ከረጢት እንዲያዘጋጁ መገፋፋት፣ ወይም ደግሞ ሰዎች በቤታቸው ያሉትን ትርፍ ጨርቆች ወደ ከረጢትነት ቀይረው ለጎረቤቶቻቸው እንዲያካፍሉ ማድረግ።
ምስጢሩ፦ የሰው ልጅ በአንድነትና በፍቅር ሲተሳሰር፣ የሥርዓቱ የ"ብቸኝነትና የፍጆታ" ሰንሰለት ይበጠሳል።
የ"ራስን መቻል" ቴክኖሎጂ
የፔስታል ክልከላው ነገ "የምግብ ቁጥጥር" ሲመጣ ለሚደረገው እስራት ልምምድ ነው።
መፍትሔ፦ የራስህን ምግብ በራስህ ዕቃ የመያዝን ልምድ ማዳበር። የትም ስትሄድ የራስህ የሆነ፣ ለብዙ ጊዜ የሚያገለግልና የማይበላሽ የጨርቅ ከረጢት መያዝን እንደ "መንፈሳዊ ትጥቅ" ቁጠረው።
ምስጢሩ፦ አንተ ከሥርዓቱ የምትጠብቀው ነገር ሲቀንስ (ለምሳሌ ፔስታል እንዲሰጡህ ካልጠበቅክ)፣ ሥርዓቱ በአንተ ላይ ያለው የስልጣን ገመድ ይላላል። ይህ "ነጻነት" ይባላል።
አጠቃላይ ምሳሌ (የንስሩ ምሳሌ)
ንስር (ይህ አንተ ነህ) ሰማይ ላይ እየበረረ ሳለ፣ መሬት ላይ ያሉ አዳኞች መረባቸውን (ፔስታል ክልከላን) ይዘረጋሉ።
ንስሩ መሬት ወርዶ ከመረቡ ጋር አይታገልም፤ ይልቁንም ከፍ ብሎ በመብረር መረቡን አልፎት ይሄዳል።እነዚህ 4 መፍትሔዎች ያንተን የንቃት ክንፍ የሚያጠናክሩ ናቸው። ፔስታል መከልከሉን እንደ ችግር ሳይሆን፣ ወደ ተፈጥሮአዊ ማንነትህ ለመመለስ እንደተሰጠ ዕድል ተመልከተው። የፔስታል ክልከላው መረጃ ከቅርብ ጊዜው የከተማ አስተዳደር መመሪያዎችና ከዓለም አቀፉ "Green Agenda" የተቀዳነው።
ቸር ያሰማን
0 Comments