እዚች ምድር ላይ ብቻችንን አይደለንም!
የሮዝዌል ኒው ሜክሲኮ ምሥጢራዊ የዩፎ ፋይሎች!!
የሃርቫርድ ዩኒቨርስቲ ጥናት: ከሌላ ፕላኔት የመጡ ፍጡራን (Alien's) በሰዎች መሃል እየኖሩ ነዉ።
በቅርቡ የተደረገ የሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ ጥናት ከሌላ ፕላኔት የመጡ ፍጡራን በመካከላችን ሊኖሩ እንደሚችሉ ጠቁሟል፣ ምናልባትም እንደ ሰው መስለው በመሬት ላይ ወይም ከመሬት በታች ወይም በጨረቃ ላይ እየኖሩ ሊሆን እንደሚችል ጠቁሟል።
ከሃርቫርድ Human Flourishing ፕሮግራም ጥናት ዩኤፍኦዎች (UFO) የሌላ ፕላኔት ፍጡራን በመሬት ላይ ያሉ ጓደኞቻቸውን ለመጎብኘት ሲመጡ ይዘዋቸዉ የመጡ በራሪ አካላት ሊሆኑ እንደሚችሉም ገምቷል።
በአንዳንድ ሣይንሣዊ መስኮች የተቀዳጀናቸውን ምጡቅ ግኝቶች እኛ ብቻ ነን ያሣካናቸው ብለን ምስጋናውን ለመውሰድ አንችልም፣ በእርግጥ ከሌሎች የተደረገልን እገዛ ነበር፡፡
ይህን ያሉት የሮኬት ሣይንስና የጠፈር ጉዞ አባት እየተባሉ የሚጠሩት አሜሪካዊ የጠፈር ቴክኖሎጂ ሣይንቲስት ሔርማን ኦበርት ናቸው፡፡ ሣይንቲስቱ ይህን ሲሉ በትክክል የማንን እርዳታ አግኝተናል ለማለት እንደሆነ ማብራሪያ ሲጠየቁ ደግሞ መልሳቸው እቅጭ ያለ ነበር! ‹‹በሌላ ዓለማት ነዋሪዎች!››፡፡
“We cannot take the credit for our record advancement in certain scientific fields alone; we have been helped.” When asked by whom, he replied: “The people of other worlds.”
Hermann Oberth, Father of rocketry and space travel.
አሁን ማወራቹ የሰው አስተያየት አይደለም፡፡ ዝም ብሎ ያልተጨበጠ መላምትም አይደለም፡፡ ወይም በየዜና ማሰራጫው እንደ ‹ቀልድ› የሚወሩትን የሰውን ጉጉት የሚያጭሩ እንቶ ፈንቶ ወሬዎች አይደለም፡፡
ለወሬ ለወሬማ በተለያዩ ጊዜያት በየማህበራዊ ሚዲያዎቹ እንደዚሕ የሚሉ ዜናዎችን ሰምተን ይሆናል፡- ‹‹ሒላሪ ክሊንተን የኤልየን ልጅ በማደጎ ወሰደች››…፣ ‹‹ትልቁ ቡሽ ከዩፎ ጋር ሲጓዙ በድብቅ የተነሣ ፎቶ››…፣ ‹‹ሲ አይ ኤ የደበቀውን ምሥጢራዊ የዩፎ ሰነዶች ከ50 ዓመት በኋላ ለሕዝብ ይፋ አደረገ››…፣ ‹‹ካርል ሳጋን በዴንቨር.. በኮሎራዶ የዩፎዎችን ማረፍ ያረጋገጠበት እማኝነት››፣ ወዘተ ወዘተ ወዘተ እናገኝ ይሆናል፡፡ ይሄኛው ግን እንደዚያ አይደለም፡፡
ይህ በአንድ በእውነተኛ ህይወቱ በእውኑ ዓለም ህይወቱን ሙሉ ያገለገለውን የሚወደውን የሃገሩን መንግሥት ሽንጡን ገትሮ ባደባባይ የሞገተ ብዙዎችንም ማሳመን የቻለ እውነተኛ የተግባርና የመርህ ሰው እማኝነትን የያዘ መጽሐፍ ነው፡፡
የሕይወት ማስታወሻውን የጻፈው ሰው ኮሎኔል ፊሊፕ ጄ ቶርሶ ይሰኛል፡፡ መጽሐፉ ደግሞ፡- ‹‹ዘ ዴይ አፍተር ሮዝዌል››፡፡ ‹‹ዘ ዴይ አፍተ ሮዝዌል›› የሚል ርዕስ ያለው ይህ በኮሎኔል ጄ ቶርሶ የተጻፈ መጽሐፍ እጅጉን በዓለም የታወቀ መጽሐፍ ነው፡፡
ኮሎኔል ጄ ቶርሶ በዩ ኤስ ‹‹አርምድ ሰርቪስስ ኮሚቴ›› ውስጥ የሠራ ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንን ነው፡፡ ኮ/ል ቶርሶ የነበረው ሚና ጥቂቶች ብቻ የተሰማሩበት በቴክኖሎጂ ምርመራና ትግበራ ላይ በተሰማራው ከፍተኛው ምሥጢራዊ የልዩ ኤክስፐርቶች ቡድን ውስጥ የወታደራዊ ደህንነት ልዩ አዋቂነት ነው፡፡ ኮ/ል ጄ ቶርሶ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት እንዲሁም በኮሪያ ጦርነት በወታደራዊ ደህንነት ተንታኝነት እና በኃላፊነት ተሰማርቶ ታላቅ ውጤትን ያስመዘገበ የተግባር ሰው ነው፡፡ ኮሎኔል ጄ ቶርሶ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት እነ አሜሪካና ሸሪኮቻቸው ምዕራብ አውሮፓውያኑ ጥምር ጦራቸው ሮም ጣልያንን፣ ኖርማንዲን እና ባጠቃላይ ዲ-ዴይ ተብሎ የሚታወቀውን ታላቁን ወታደራዊ ኦፕሬሽን ሲያካሂዱ በሥፍራዎቹ ሰዎቹን አሰማርቶ በወታደራዊ ደህንነት መስክ ቁልፍ ታሪካዊ ሚናውን ድምፁን ሳያሰማ የተወጣው- ይኸው የወታደራዊ ደህንነት መኮንን የፊዚክስም ባለሙያ ኮ/ል ጄ ቶርሶ ነበር፡፡
ከዓመታት በኋላ ‹‹የብሔራዊ ደህንነት ኤጀንሲ›› ተብሎ በእነ አልጎርና ክሊንተን ዘመን በድጋሚ እንዳዲስ ተጠናክሮ ሲዋቀር እንደ አወዛጋቢው ኮንትራክተር እንደ ኤድዋርድ ስኖውደንን የመሣሠሉትን ሁሉ በሥሩ ቀጥሮ ሲያሰራ የነበረው የቀድሞው ‹‹ብሔራዊ የደህንነት ካውንስል›› በሚባለው ውስጥም ቁልፍ የሆነን ሙያዊ አገልግሎት አበርክቷል! ኮሎኔል ፊሊፕ ጄ ቶርሶ፡፡ በዚህ ሁሉ መሃል የቶርሶ መረጃዎችን ማነፍነፍና ልዩ አዋቂነት እጅጉን የሚፈለግበት ምሥጢራዊ ተግባር መጣ፡፡ ወቅቱ ዓለም በሁለት ጎራዎች ተከፍላ በቴክኖሎጂ አንዱ አንዱን ለመብለጥ የመጨረሻውን የሣይንስ ትንቅንቅ የሚያደርግበት የቀዝቃዛው ጦርነት ወቅት ነው፡፡ እና ከሚሊቴሪ ውስጥ ለከፍተኛ የደህንነት አገልግሎት ሥራ ይሁን ወይም በእውነተኛ ምክንያት ባይታወቅም በ1963 - ኮሎኔልፐፊሊፕ ጄ ቶርሶ ያለዕድሜው በመደበኛው መንገድ በጡረታ እንዲሰናበት ተደረገ፡፡
ነገር ግን ቶርሶ ከስንብቱ በኋላ ያመራው ወደ ቤቱ አልነበረም፡፡ ቶርሶ ከጡረታው በኋላ አገልግሎቱን ለሚወዳት ሃገሩ እነሆኝ የሚልበት ሌላ ግዳጅ ተሰጠው፡፡ ኃላፊነቱ እጅግ ከፍተኛ ኃላፊነት ነው፡፡ በአድሚራል አርሌይ በርክ እና በጄነራል አርተር ትሩዶ
ይመራ በነበረው የቻይናዎችንና የሶቭየቶችን የቴክኖሎጂ ብቃትና ምሥጢራት የሚበረብርና ሪፖርት የሚያደርገው... ብሎም ትንበያውን ሊሰጥ የተቋቋመው ልዩና ምሥጢራዊ ግብረ-ሃይል ውስጥ ነበር በቀጥታ የተወሰደው፡፡ ለተከበረው የወታደራዊ ደህንነት ተንታኝ ለአድሚራል አርሌይ በርክ እና በወታደራዊ ደህንነት ተግባሩ የፕሬዚደንቱ ልዩ አማካሪ እስከመሆን ለደረሰው ለጄነራል አርተር ትሩዶ በቀጥታ ሪፖርት እንዲያደርግ ልዩ ሥልጣንና ኃላፊነት የነበረው ከባድ ሰውም
ነበር፡፡
ብቻ ብዙ ነገሮች አለፉ፡፡ ብዙ በአንድ ጄነራልና ኮሎኔል ምናልባትም በፕሬዚደንቱና በሁለቱ የደህንነት ዳይሬክተሮች ብቻ ዓይኖች አልፈው ከብዙዎች የተሰወሩ ብዙ ብዙ ምሥጢራትንም ተመለከተ ኮ/ል ፊሊፕ ጄ ቶርሶ፡፡ ነገር ግን የኋላ ኋላ ኮሎኔል ፊሊፕ ጄ ቶርሶ በተለይ አንድ ነገር እረፍት ይነሳው ጀመር፡፡ ስለምን የሚሊቴሪ ደህንነቱ ስለ ዩፎዎች (ወይም ስለሌላ ዓለም ፍጡራን በእጁ ያሉትን መረጃዎች… ለሕዝቡ መደበቅ አስፈለገው??? ለምንስ በአይናቸው ያዩት… በሥፍራው የነበሩትን የነፃይቱን አሜሪካ ነዋሪዎች እንዳይናገሩ ማፈን.. በከፍተኛ ኃይል ማስፈራራትና… በማያቋርጥ ተፅዕኖና የደህንነት ክትትል ውስጥ መጣል አስፈለገ? መንግሥቱ እና የደህንነት ተቋማቱ የመጨረሻው ተጠሪነታቸው ለመረጣቸው ሕዝብ አይደለምን??? ታዲያ ለምንድነው እኒህ ሁሉ ምሥጢሮች ታፍነው የሚቀሩት?
ሃገርን ምን የሚጎዳ ነገር አለባቸው?
የሚል ለብዙዎች ባልደረቦቹ አስፈሪ የሆነባቸው ፅኑ አቋም አደረበት፡፡ እና በዚህ አቋሙ ሕይወቱን ከሠጠለት ሙያው በክብር ተሰናበተ፡፡ ከመሠናበቱ በፊት በሚሊቴሪ ችሎቶች ቃሉን እንዲሰጥና ጥልቅ ምርመራ እንዲደረግበት ተደርጎ ነበር፡፡ እና ውጤቱ የኮ/ል ጄ ቶርሶን ታማኝነት፣ ብቃት፣ አገልግሎትና መብት የሚያረጋግጥ ነበር፡፡ እና በሠላም ተሰናበተ፡፡
ታዲያ ኮሎኔሉ እስከ አሁን ዓለምን የሚያነጋግርበት ምን ትልቅ ምክንያት ቢኖረው ነው?? ኮ/ል ቶርሶ በጁላይ 5 ቀን 1947 በአሜሪካ፣ ሮዝዌል ከተማ፣ በኒው ሜክሲኮ በረሃማ ግዛት ውስጥ በድንገት የተከሰከሰውን እጅግ የተራቀቁ ልዩ ቴክኖሎጂዎችን የታጠቀውን የዩፎዎች (የማይታወቁ በራሪ አካላት) የበረራ መንኩራኩር (ፍላዪንግ ዲስክ) እንዲሁም ከእነዚያ የስፔስ እንግዶች መካከል ከነህይወታቸው ተርፈው በምሥጢራዊው 110ኛ የሚሊቴሪ ደህንነት ምድብተኞች የተወሰዱትን አንደኛው ከተቆረጠ እግሩ መሃል የኤሌክትሪክ ብርሃን የሚፈናጠር እንዲሁም አካላዊ ገጽታቸውን ኮ/ል ጄ ቶርሶ ካስቀራቸው እጅግ ምሥጢራዊ ወታደራዊ ዶክመንቶች መካከል በማቅረብ ጄ ቶርሶ ሽንጡን ገትሮ… በሃገሩ እየማለ.. በሁሉ ነገሩ ቃል-ኪዳኑን እያስረገጠ እልፍ አዕላፍ ሚስጥራዊ መረጃዎችንና በተለያዩ ጊዜያት ስለሮዝዌሉ ክስተት የዕምነት ቃላቸውን የሰጡ እማኞችን፣ የተለያዩ በላብራቶሪ ውስጥ ያገኛቸውን ፎቶዎች፣ ሰነዶችና ፋይሎች እያጣቀሰ በዚያን ጊዜ የተከሰቱትን ዩፎዎች መመልከቱን፣ መኖራቸውን፣ እና አሜሪካ ለደረሰችባቸው እጅግ የመጠቁ የሌዘር ጨረራ፣ የስፔስ፣ የጠፈርና በረራ፣ እንዲሁም የኤሌክትሮ ማግኔቲክና የተለያዩ ምጡቅ የስፔስ ሳይንስና የልዩ ልዩ ወታደራዊ መሣሪያዎችና ሣይንሶች ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማበርከቱን በማስረጃ አስረግጦ ያብራራል፡፡
እንዲያውም ከዚያ አልፎ ኮሎኔል ፊሊፕ ጄ ቶርሶ ከእርሱ መሰናበት በኋላ በጠፈር ሳይንስ መስክና በወታደራዊ ልሂቃን ዘንድ ያስተዋላቸው አንዳንድ ክስተቶች በእርግጥም የአሜሪካ መንግሥት ከጠፈሮቹ እንግዳ ፍጡራን ጋር ቀጣይ ግንኙነትና የቴክኖሎጂ ኩረጃና ልውውጥ እንደነበረ በትክክል ያረጋግጣሉ ሲል ነው የሚናገረው ኮሎኔል ጄ ቶርሶ በ‹‹ዘ ዴይ አፍተር ሮዝዌል›› መጽሐፉ፡፡ በእርግጥ ጄ. ቶርሶ እውነቱን ካወጣና ከሞገተ ከዓመታት በኋላ በዚያች የጁላይ 5/ 1947 በሮዝዌል የስፔስ ኤልየኖች ከነበራሪ ዲስካቸው ብቅ ያሉባትን ከስተት በዓይናችን አይተን አምቀን ቆይተን ነበር የሚሉ የዓይን እማኞች ከጊዜ ወደ ጊዜ ተበራክተዋል፡፡
የአሜሪካ መንግስት ራሱ ምን ቢያደርግ ጥሩ ነው???
በሮዝዌል፤ ኒው ሜክሲኮ ልዩ ዲዛይን ያለው ትልቅ ሕዝባዊ ተቋም ገነባ፡፡ ይህ የሮዝዌል ሥፍራ በየዓመቱ በብዙዎች ካለም ዙሪያ ይጎበኛል፡፡ መንግስት ያነፀው ተቋም ምን ቢሆን ጥሩ ነው???? ‹‹የሮዝዌል የማይታወቁ ባዕድ ፍጡራን ልዩ ቤተ- መዘክር››
(‹‹ሮዝዌል ዩፎስ ስፔስ ሙዝየም››!!!)፡፡፡
ጉድ በል!
ጎጃም! ጉድ በል ጎንደር!! ታዲያ ከዚህ በላይ የምን አውጫጭኝ… የምን የ‹‹ዕምነት-ክህደት›› ቃል አስፈለገን???!!! ምንም!!! ባለፈው ጁላይ 5 ቀን ላይ ቢቢሲ እና ሲ ኤን ኤን ላይ በቀጥታ ይተላለፍ የነበረ የመታሰቢያ የሕዝብ ፌስቲቫል ነበረ፡፡
የፌስቲቫሏ ከተማ ነዋሪዉ ሰው አንዳንዱ እየሳቀ፣ አንዳንዱ እየፈነጠዘ፣ አንዳንዱም እያፈረ… ለጋዜጠኞች ይናገር ነበር ሃሳቡን፡፡ በርካታ ቱሪስቶችም በሥፍራው ተገኝተው በዓሉን ያከብሩ ነበር፡፡ ከተማዋ ማነች??? ከተማዋ ያኔ ቶርሶ ዩፎዎች ከነበራሪ ዲስካቸው ወደቁባት ያላት የኒው ሜክሲኮዋ ሮዝዌል ከተማ ናት፡፡ በዓሉ ኃይለኛ የቱሪስት ምንጭ ሆኖላታልም፡፡ 70ኛ ዓመቷን መታሰቢያ እያከበረች ነበረ፡፡ ዩፎዎች በከተማዋ የተከሰቱበትን፡፡ ከዓለም ሁሉ በማይታወቁ የሌላ ዓለም ባዕድ ፍጡራን መኖር የሚያምኑ ወይም የሚጠረጥሩ ሰዎች ሁሉ በየዓመቱ በጁላይ 5 በዚህች ከተማ ክበርቻቻቸውን ይፈጽማሉ በሣቅ፣ በደስታ፣ በፈንጠዚያ!!!!
እስከዛሬ ግን እነዚያ ኤሊየኖች በከተማይቱ በምድሪቱም ላይ ስለምን እንደመጡ የሚያውቅ አልተገኘም፡፡ ለክፉም ለደጉም አመጣጣቸውን እንግዲህ ለበጎ ያድርግልን ማለት ነው!!! አበቃሁ፡፡
ማስታወሻ፡- ከዚህ ጽሑፍ ጋር በቀረበው ምስል ላይ የሚታየው ኮ/ል ፊሊፕ ጄ. ቶርሶ አይደለም፡፡ የእርሱን የራሱንና የያዛቸውን የኤሊየን ምስሎች ከመጽሐፉ (በፒ ዲ ኤፍ ይገኛል)፤ አሊያም ከድረ-ገጽ ፈልጎ በቀላሉ ማግኘት ይቻላል፡፡ ከዚህኛው ፎቶ ጋር
የተያያዘው ጽሑፍ ግን እንዲህ ይነበባል፡-
‹‹Alien shaking hands with I'm not sure who or about what. We're Not Alone people..››
(‹‹ባዕድ ፍጡር ማን እንደሆነ ወይም ለምን እንደሆነ ካላወቅሁት ሰው ጋር ሲጨባበጥ፡፡ ኧረ ተዉ ብቻችንን አይደለንም ሰዎች!!!!››)፡፡❗
0 Comments