ሳይቃጠል በቅጠል በቅጠል



✍ ሔኖክ ኃይለገብርኤል | አባወራ | ኢትዮጵያ አውታር  

የጥፋት እሳት መጀመሪያው ቅንጣት ትንታግ ናት፤ ካልጠፋች ግን ሀገር ታነዳለች። "መብትና ነፃነት" እየተባለ የሚረጨው መርዝም እንዲሁ ነው—ጥቂት ፈቅጄ ቀምሼም እተወዋለሁ አይባልም፤ አንዴ ከፈቀዱለት እስከ ጥፋቱ አዘቅት ድረስ ይነዳል እንጂ!

አሁን በእኩልነት፣ መብትና ነፃነት እንዲሁም ጾታዊ ጥቃት ዘመቻ ተደርጎ የተጀመረው ትውልዱን በአባታዊ ሥርዓትና በአባቱም ላይ የማሳመጹ መንገድ ላይ ነው።

ይህ እሳት ሳይዛመትና ሀገር ሳይበላ "ሳይቃጠል በቅጠል" ሊመታ ይገባል፤ ሳያጠፋን አይቆምምና።

ይህ ሰደድ እየኾነ ሀገራትን እያጠፋ፣ ሕዝብን እያመከነ ያለው እሳት፤ ትናንት ሩቅ ነበር፤ ዛሬ ግን ጎረቤት ሀገራት መድረሱ እኛንም መጎብኘቱ እንደማይቀር ማሳያ ነው።

ኬንያ ትውልዷን እያጠፋ፣ ማኅበረሰቧን እያመከነ ላለው አውዳሚ "የሰደድ እሳት" ንፋስና ማገዶ ኾናለታለች፣ ኧረ ቤንዝንም ታርከፈክፋለች፤ እንደ ኢትዮጵያ ላሉ ጎረቤት ሀገራትም ይህንኑ ተውሳክ ለማዛመት ደምበኛ መሿለኪያ እየኾነች ነው።

እኛም በንቃት እየተከታተልናት!

ኢትዮጵያ ሆይ ተይ ስሚ!

👉 "የሴቶች ጭቆና" ሲሉ ሴቶችን የሚጠብቅን ሥርዓት ይቃወማሉ፣
👉 "ሥርዓተ ጾታ"(Gender) ሲሉ ጾታዊ ጸጋንና ሚናውን ያጠፋሉ፤
👉 "የሥነ-ተዋልዶ መብት" ሲሉ ጾታን ያሴመርጣሉ፣
👉 "የጾታ እኩልነት" ሲሉ "በመረጡት" ጾታ ያቆማሉ፣
👉 "ሴቷ ከወንዱ እኩል ትኹን" ሲሉ ሴትነቷን ያስጠላሉ፣
👉 "የሥነ-ተዋልዶ ጤና" ሲሉ ልቅ ወሲብና ውርጃን ያስተምራሉ
.
.
. ጫፉ ይጨበጥ እንጂ ቀስ በቀስ እየጎተተን የሚሄድ ከአዘቅቱም ሳይጥለን ማቆሚያና መመለሻ የሌለው የጥፋት መንገድ ነው።

እነዚህን አጀንዳዎች "ለበጎ ነው" ብሎ በጥቂቱ መቀበልና መፍቀድ አይቻልም። አንዴ ከፈቀድንላቸው፣ ማቆሚያና መመለሻ ወደሌለው ምዕራባውያን ወደ ወደ ጠፉበት(ተቃጠሉበት) "ሰደድ እሳት" መቀጣጠሉ አይቀርም።

በሴቶች እኩልነት፣ መብትና ነፃነት እንዲሁም በጸረ-ጾታዊ ጥቃት የተከፈቱብን ዘመቻዎች መመለሻቸው ሳይቸግር ማጣፊያቸውም ሳያጥር ሊቀለበሱ ይገባል።

በእርግጥ ብዙ ብር ይገኝበታልና ብዙዎች በ"ግብረሰናይ" ድርጅት ስም "ግብር የማይከፍል ሱቅ" ከፍተው ይነግዱበታል፤ ትውልድ ግን ይይጠፋበታል፣ ማኅበረሰብም ይመክንበታል።

አንድም ደግሞ ልሂቁና ሊቃውንቱ ሆዳደርም ቢሉ አልጫ ኾነዋልና ማንም ስለ እርሱ ማውራት አይፈልግም፤ የሚናገሩትንም እድል ከመንፈግ ጀምሮ ያፍናሉ እንጂ!

እነርሱ በሆዳቸው ሲታሰሩ፣ በፍልሃት ሲሸበቡ ትውልዱ ያለ እረኛ ይቀራል፤ የበግ ለምድ በለበሱ ተኩላዎችም ይበላል፤ ልቡ ጠፍቶም ይጠፋል።

በሴቶች እኩልነት፣ መብትና ነፃነት እንዲሁም በጸረ-ጾታዊ ጥቃት ስም የተከፈቱብን ዘመቻዎች መመለሻቸው ሳይቸግርና ማጣፊያቸው ሳይጥር አሁኑኑ ሊቀለበሱ ይገባል።

በጎረቤት ሀገር ኬንያ ወላጆች ከፍተኛ ችግር ውስጥ ገብተዋል! ሀገሪቷ የዚህ ከፉ ተውሳክ መራቢያ ስትኾን፤ እንዲህ እንድትኾን ያደረጓት የምዕራባውያን ተቋማት ደግሞ እርሷን መነሻ አድርገው የሀገሬን(ኢትዮጵያ) ባለ ማስትሬትና ዶክትሬት፣ ሊቅና ሊቃውንት ፈረስና በቅሎ አድርገው እየጋለቡ ይገኛሉ!

ይህ በጾታ እኩልነት፣ መብትና ነፃነት በተለይም ደግሞ በጸረ-ጾታዊ ጥቃት ዘመቻዎች ተሳቦ የተቀጣጠለው ትውልድን አጥፊ ማኅበረሰብን አምካኝ ሰደድ "ሳይቃጠል በቅጠል" ብለን ይጠፋ ዘንድ ፈጥነን ልንረባረብ ይገባል።

አለበለዚያ ግን ምዕራባውያን የጠፉበት መንገድ ላይ ወጥታ፣ ትውልዷን ባክኖባት፣ ልጆቿ እየጠፉባት፣ የምትይዘው የምትጨብጠውን ያጣችውን ኬንያን መከተላችን አይቀርም።

የተደገሰልን ብዙ ነው! ጥቂት ባፍጢም የተደፉ ሆዳደር ሊቃውን ሳይበላ፣ ሳይጠግ፣ ሳይለብስ ላስተማራቸውን ሕዝብ ውለታ የሚመልሱት እርሱንና ልጆቹን እንዲህ ላለው አጥፊ አሳልፎ በመስጠት መኾኑ እጅግ ያስቆጫል።

ቤታችን፣ ቤተሰባችን፣ ሀገራችን በራሳችን ልጆች፣ "እናት" "አንጀቷን አስራ" ባስተማረቻቸው "ምሁሮች" ልጆቿ እየተቃጠለች፣ ትውልዷን እያጣች፣ ማኅበረሰቧም እየመከነባት ነው!

አንተ ደግሞ "በምን ልሳተፍ?" አትልም፤ ዛሬም ታነባለህ!

አልሰማንም እንዳትሉ! አልጫ ስለኾናችሁ ስለዚህ ጉዳይ ማንሳት፣ ማውራትም አትፈልጉም እንጂ!

Post a Comment

0 Comments