ስውሩ አለም! ከማን ጋር እየኖርን ነው?
ናሳ/NASA የደበቀው የዩፎዎች/UFO ከተማ
Anunaki Film ለምን ታገደ?
ጨረቃ ላይ የተሰራው የግንብ አጥር!
UFO ዩ.ኤፍ.ኦዎች ሆሎማን አየር ሀይል ጣቢያ ስለመገኘታቸው!
✍ ቲና በቀለ | ኢትዮጵያ አውታር
እ.ኤ.አ በ1964 ሶስት በራሪ አካላት ሆሎማን አየር ጣቢያ ሲያርፉ ራዳር ውስጥ ገብተው ነበር። ሰውን መሰል፣ ሰማያዊ ዓይን ያላቸው እና የበረራ ልብስ የለበሱት ኤሊያኖችም ከአየር ሀይሉ ኮማንደር እና ከአራት የጣቢያው ኦፊሰሮች ጋር እንደተገናኙ፤ እንዲሁም ለቀናት በቦታው እንደቆዩ ተገልጿል። በምን ዙሪያ ውይይት እንደተደረገ ግን አሁንም ድረስ ምስጢር ነው። ከአመታት በኋላ “UFOs: Past, Present,and Future,” እና “UFOS: It Has Begun,” በተባሉ ዶክመንታሪዎች ላይ አይዘንሐወር ከኤሊያኖች ጋር የነበራቸውን ግንኙነት በፎቶ እና በቪዲዮ በማቅረብ ጭምር ያስረዳል።
ቦይድ ቡሽማን የኤሮስፔስ ሳይንቲስት ነው፤ እ.ኤ.አ በ ነሀሴ 7 2014 ከመሞቱ በፊት ስለ ኤልያኖች ምስጢር የሰላሳ ደቂቃ ቪዲዮ ቀድቶ ነበር። ቡሽማን "Lockheed Martin Aeronautics Company" ለብዙ ዓመት አገልግሏል። ቪዲዮው ላይ በአሜሪካን አየር ሀይል የሚመራና በምስጢር የሚጠብቁት፥ ከሌላ ዓለም ፍጥረታት ቴክኖሎጅ ጋር የሚሰራ አካል እንደነበር በፎቶ በማስደገፍ ያብራራል። ኤልያኖች በኤሪያ 51 እና በተጨማሪም በድሪምላንድ ኔቫዳ በረሃ ከላስ ቬጋስ በስተሰሜን በኩል 85 ኬሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኝ ምስጢራዊ ቦታዎች እንደሚገኙ ያስረዳል...
...ናሳና ዩ.ኤፍ.ኦ❗
ናሳ ባወጣው ምስል መሰረት በጨረቃ በማይታየው ጎን በኩል አንፀባራቂ የኤልያን ከተማ ይገኛል። አሁን ላይ በከተማው ውስጥ ማንም እንደሌለ የገለፀው ናሳ ነገር ግን ኤልያኖች በጥንት ጊዜ ሳይኖሩበት እንዳልቀረ ተናግሯል። የጨረቃ የማይታየው ክፍል ከመሬት አቅጣጫ በተቃራኒው የሚገኝ ሲሆን፥ ምን እንዳለበት እስከ አፖሎ 8 ተልእኮ ድረስ አይታወቅም ነበር። ተመራማሪዎች ከመሬት በሌላ በኩል በሚገኘው የጨረቃ ክፍል የተለያዩ ማእድናት እንደሚገኙ ቢገልፁም ዊሊያም ኩፐር በአፖሎ 8 የተጓዙ ተመራማሪዎች በወቅቱ የሌላ ዓለም ፍጥረታትን አግኝተው እንደነበርና መረጃውን ለማንም እንዳይናገሩ ተነግሯቸው እንደነበር ይገልጻል። ለዚህም ጨረቃ ላይ የተሰራው የግንብ አጥር እንደ ምክንያትነት ይነሳል።
በናሳ ይሰራ የነበረ ቶማስ ካስቴሎ የተባለ ሰው ምድር ውስጥ ኤልያኖች ከሰው ልጆች ጋር እንደሚዳቀሉ ተናግሯል። በተጨማሪም በቦታው የኤልያኖችን ተመራማሪዎች እንደተመለከተ፤ እንዲሁም ባንድ ወቅት ኤልያኖችን ከሰው ልጆች ጋር የጦርነት ሙከራ ተዘጋጅቶ ነበር። ካስቴሎ ትእይቱን የመመልከት አጋጠሚ እንደነበረው ሲ.አይ.ኤ ባወጣው መረጃ ገልጿል። አሁን ላይ ካስቴሎ ምን እየሰራ እንደሆነ እና የት እንዳለ የሚያውቅ የለም።
የናሳው ቃል አቀባይ ትሪሽ ቻምበርሰን ስለ ሌላ ዓለም ፍጥረታት መኖር፦ "ምድርን ከብዙ ሺህ አመታት በፊት ጎብኝተዋታል። የጥንት ፒራሚዶችን እና ሃውልቶችን የገነቧቸው እነማን ይመስሏችኋል? በእኔ እይታ ሁሉም ነገር ግልጽ ነው።"
ቶም ኬለር የተባለ በናሳ ይሰራ የነበረ የኤሮስፔስ ኢንጂነር እና የቀድሞው ዳይሬክተር ቤን ሪች ዩ.ኤፍ.ኦዎችን በመጠቀም የተለያዩ የቴክኖሎጂ ውጤቶች እንደተሰሩ፥ ነገር ግን ማስረጃዎች በከፍተኛ ምስጢር እንደሚጠበቁ ፍንጭ ለመስጠት ሞክረዋል።
ተመራማሪዎች አኑናኪዎች ወደ ምድር ተመልሰው ሊመጡ እንደሚችሉ ናሳ እንደሚያምን ገልጸዋል። ለዚህ ምክንያታቸው ደግሞ ፕላኔት ኒብሩ ላይ የተለየ ክስተት ማየት በመጀመራቸው ነው ተብሏል። በዚህም ፕላኔት ኒብሩ ላይ ሳይኖሩ እንዳልቀረ እና በቅርቡ ወደ መሬት እንደሚመለሱ ናሳ እንደሚያምን አንዳንድ ተመራማሪዎች ተናግረዋል።
የተለያዩ የዓይን ምስክሮች ስለ ባእድ ፍጥረታት መኖር❗
ቲላ ቴኪላ ስለ ኢሉሚናቲ የተለያዩ መረጃዎችን በመልቀቅ ትታወቃለች። በተለይም ዝነኛ ሰዎች ለሰይጣን መስዋዕት እንደሚሆኑ፥ እንዲሁም ባንድ ወቅት ለሰይጣን ተገዢ እንደነበረችም ገልጻለች። ዝነኛ ሞዴሊስት፣ ተዋናይ እና ድምፃዊ የሆነችው ቲላ ቴኪላ እ.ኤ.አ 2012 "the others" ብላ ስለጠራቻቸው፥ ባእድ ፍጥረታት የሚከተለውን ብላለች፦ "የሰው ልጆች ላይ ስለሚፈፅሙት በደል ተሰላችቻለሁ፤ እኛን ልክ እንደ አሻንጉሊቶቻቸው ነው የሚያዩን። አብዛኛው ሰው ስለ ባእድ ፍጥረታት መኖርና ስለ ምርምር ቦታዎቻቸው አያውቅም። ባእድ ፍጥረታት ከመሬት ውስጥ በመውጣት የሰውን ልጅ ለማጥፋት የመጡ ሲሆኑ አንዳንዶቹ ደግሞ ጨረቃ ላይ ይገኛሉ።" ስትል ገልጻለች።
እ.ኤ.አ በ1947 በሜክሲኮ የተገኘው በራሪ ዲስክ በጊዜው ከነበሩት የሰው ጦር አውሮፕላኖች በላይ በከፍተኛ ፍጥነት ሲጓዝ ነበር። ቦብ ላዛር የተባለ በኤሪያ 51 ሲሰራ የነበረ ሰው እ.ኤ.አ በ1989 በአንድ የቴሌቪዥን ጣቢያ ቀርቦ ወደ ዘጠኝ አካባቢ የሚሆኑ በራሪ ዲስኮች እንደሚገኙ ተናግሯል።
እ.ኤ.አ ጥር 25.2019 ግዙፍ ዩ.ኤፍ.ኦ ከአሜሪካ ካሊፎርኒያ ሳን ክሌሜንቴ ወደብ ወደ ደቡብ ሲበር እንደነበር ታይቷል። በዚሁ ቀን ሜክሲኮ አካባቢ ተመሳሳይ ዩ.ኤፍ.ኦ ሲበር እይታ ውስጥ እንደገባ የምስል ማስረጃዎች ያሳያሉ።
እ.ኤ.አ በ1954 በፈረንሳይ አስደንጋጭ የዩ.ኤፍ.ኦ ታሪክ ተከስቶ ነበር። ማሪየስ ዴዊልድ የተባለ የዓይን ምስክር የሰጠውን ቃል መሠረት በማድረግ በተደረገው ምርምር በሰሜን ፈረንሳይ ኳረብል ቫለንሲንስ አካባቢ የኤልያኖች መንኮራኩር በወቅቱ ሲጓዝ የነበረውን ባቡር አቅጣጫ አስቀይሮ ነበር፤ በተጨማሪም በዚያን ወቅት ከባእድ ፍጥረታቱ በተለቀቀው ጨረር እንስሳት እንደሞቱ ተገልጿል።
እ.ኤ.አ በ 1935 ዊሊ ሌይ የተባለ የሮኬት ሳይንቲስት ከጀርመን ወደ አሜሪካን ተሰድዶ ነበር። ይህ ሰው ከሁለት ዓመት በኋላ በወጣ አንድ አምድ ላይ ጀርመን ውስጥ 'የእውነት ማህበረሰብ'(Wahrheitsgesellschaft) የሚባል ቡድን እንዳለ፥ ቡድኑ ስለ ቭሪል ማህበረሰቡ የሚያጠና እና ማህበረሰቡን በመጠቀም የተለያዩ የቴክኖሎጂ ስራዎችን ለማሳለጥ የተቋቋመ እንደነበር ተናግሯል። ከሌይ በኋላም የተለያዩ ተመራማሪዎች ከሁለተኛው ዓለም ጦርነት በፊትም ሆነ በኋላ የቭሪል ማህበረሰቡ በጀርመን እንደነበሩ ገልጸዋል።
ዩ.ኤፍ.ኦዎችን አንዳንድ የሴራ ተመራማሪዎች የቭሪ ተሳቢዎች ብለው ይጠሯቸዋል። እንደ ዴቪድ አይክ ከሆነ የቭሪል ተሳቢዎች ቁመታቸው ከሰው የማይተናነስ፣ አይናቸው እና ቆዳቸው የእባብ አይነት እነደሆነ ይገልጻል። በብሪታንያ የዩ.ኤፍ.ኦ ተመራማሪ የሆነው ቶኒ ዶድ እነዚህን ፍጥረታት "ሰባት እግር ያላቸው፥ ረጃጅም፣ ተናዳጅ የሆኑና የአእምሮ ልህቀት ያላቸው እንደሆኑ ይናገራል።
ባለስልጣናት ስለ ኤሪያ 51
ፕሬዚዳንት ጂሚ ካርተር በምርጫ ቅስቀሳ ወቅት "ፕሬዚዳንት ከሆንኩ ከዩ.ኤፍ.ኦ ጋር የተያያዙ ማንኛውንም መረጃዎች ለህዝብ አሳውቃለሁ" ብለው ነበር። ነገር ግን ፕሬዚዳንት ከሆኑ በኋላ ስለ ሌላ አለም ፍጥረታት አንስተው አያውቁም።
ፕሬዚዳንት ሮናልድ ሬገን - እ.ኤ.አ በ1985 የአሜሪካ ፕሬዚዳንት የነበረው ሮናልድ ሬገን ከሌሎች ሀገራት መሪዎች ጋር በጄኔቫ በነበራቸው ስብሰባ "ባእድ ፍጥረታት ምድርን የሚያጠቁ ከሆነ....ይህ ጊዜ ዓለም አንድ የምትሆንበት ሰዓት ነው" ብለው ለማስጠንቀቅ ሞክረው ነበር።
ፕሬዚዳንት ጆርጅ ቡሽ - ቡሽ የሲ.አይ.ኤ ዳይሬክተር በነበረ ጊዜና ለአሜሪካ ፕሬዚዳንትነት ምርጫ በሚወዳደርበት ወቅት ከአንድ ጋዜጠኛ ስለ ዩ.ኤፍ.ኦ እውነታውን ያወጣ እንደሆነ ተጠይቆ፥ መረጃዎችን የሚያገኝ ከሆነ እንደሚያወጣ ተናግሮ ነበር። ጋዜጠኛውም በድጋሚ ቡሽ የሲ.አይ.ኤ ዳይሬክተር እንደመሆኑ ሁሉንም ነገር ያውቅ እንደሆነ ሲጠይቀው "ጥቂት ነገር አውቃለሁ" በማለት መልሶ ነበር።
እ.ኤ.አ በ2021 የዩናይትድ ስቴትስ ዕጩ ፕሬዚዳንት ተወዳዳሪ በርኒ ሳንደርስ ህዝቡ ለፕሬዚዳንትነት ከመረጠው ስለ ኤሪያ 51 መረጃ እንደሚሰጥ ተናግሯል።
በተመሳሳይ ቢል ክሊንተን፣ ባራክ ኦባማ እና ሌሎችም የአሜሪካን ፕሬዚዳንት ከመሆናቸው በፊት ስለ ባእድ ፍጡራን ማስረጃዎችን ለህዝብ እንደሚያሳውቁ ቃል ቢገቡም ከሆኑ በኋላ ቃላቸውን መጠበቅ አልቻሉም።
የቀድሞው ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ በአንድ ወቅት በጂሚ ኪሜል ሾው ላይ ስለ ኤሪያ 51 ለተጠየቀው ጥያቄ “The aliens won’t let it happen. ...They exercise strict control over us.” በማለት መልሶ ነበር።
ዴቪድ አይክ የሰው ልጆች በሰው መሰል ተሳቢዎች ወይም የቭሪል ተሳቢዎች ተብለው በሚጠሩት ፍጥረታት እየተተኩ እንደሆነ የሚያምን የሴራ ተመራማሪ ነው። የቀድሞው የኒውዚላንድ ጠ/ሚኒስትር ጆን ኪ የዴቪድ አይክ ተሳቢዎች እውነት እንደሆኑ ተጠይቆ መረጃውን ውድቅ ለማድረግ እንደማይችል ተናግሮ ነበር...
...የሩሲያው አድሚራል ቭላድሚር ፕሪኮድኮ ያደጉት ሀገራት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ገንዘቦችን ፈሰስ በማድረግ የሌላ ዓለም ፍጥረታትን እና ሌሎች ዓለማትን ስፔስ ላይ የሚያደርጉትን ምርምር ገታ አድርገው መሬት ውስጥ ጥናታቸውን ቢያደርጉ የተሻለ ነገር እንደሚያገኙ ተናግሯል። ለዚህም ከሁለተኛው ዓለም ጦርነት በኋላ ሩሲያ ምድር ውስጥ ያገኘችውን ባእድ አካላት፣ የመሬት ውስጥ መገናኛዎችን እና የኤልያኖችን የጦር አውሮፕላን በመጥቀስ ገልጿል።
ባንድ ወቅት የቀድሞው የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ሮናልድ ሬገንም የሚከተለውን ብለው ነበር: "In our obsession with the antagonisms of the moment, we often forget how much unites all the members of humanity. Perhaps we need some outside, universal threat to make us recognize this common bond. I occasionally think how quickly our differences would vanish if we were facing an alien threat from outside of this world. And yet I ask: is not an alien force already among us? What could be more alien to the universal aspirations of our people then war and the threat of war?"
Black Triangle
Black triangle በ 20ኛው እና 21ኛው ክ/ዘመን የታዩትን ጥቁር ሶስት ማዕዘናት የሆኑ ተመሳሳይ በራሪ አካላት፥ ከከተማዎች በላይ ሲበሩ የታዩትን ዩ.ኤፍ.ኦዎች የሚመለከት ክፍል ነው።
- The Belgian UFO wave የተባለ ቡደን እ.ኤ.አ በ 1989 የታየውን ጠፍጣፋ፣ ሶስት ማዕዘን ቅርፅ ያለው እና የሚያበራ ግዙፍ በራሪ አካል በቤልጅየም መታየቱን በሰላሳ ሲቪል ሰዎች እና በሶስት የፖሊስ ቡድን አባላት ምስክርነት ማረጋገጥ ተችሏል።
- ሌላኛው "Phoenix Lights" የተሰኘው እና እኤአ በ 1997 በአሪዞና ግዛት ለ 106 ደቂቃ ተከስቶ የነበረው "V" ቅርፅ ያለው በራሪ አካል
በ "Google earth" የተለያዩ ምስጢራዊ ቦታዎች ስለመገኘታቸው❗
#በተለያዩ ጊዜያት የተሰወሩ እና በማን እንኳን እንደታሰሩ በወል የማይታወቁ ቦታዎች ይገኛሉ። ፒራሚዶች፣ ግንቦች፣ ቤተመንግስታት እና ሌሎች ምስጢራዊ ቦታዎች ውቂያኖስ ውስጥ በብዙ ኪሎሜትሮች ጥልቀት በየጊዜው እንደሚገኙ እንሰማለን።
- በሜክሲኮ የባህር ዳርቻ፥ Mexico-12 ° 8’1.5’N, 119 ° 35’26.4’W ላይ የተገኘው ፒራሚድ መሰል ሰርጓጅ መርከብ
- ከጥቂት ጊዜያት በፊት የተገኘው ግዙፍና ጥንታዊ የማያ የውሃ ውስጥ ከተማ
- እ.ኤ.አ በ 2012 በዩናይትድ ስቴትስ ተመራማሪ በሆነችው አንጄላ ሚኮል በሳተላይት አማካኝነት የታየው እና ከግብፁ ጊዛ ፒራሚድ ይገዝፋል የተባለው ፒራሚድ
- ሌላኛው በ "Google earth" የተገኘው፥ ምድርን ይከባታል የተባለው ግዙፍ ግንብ እና ሌሎችም ይገኙበታል።
- በአንታርክቲካ ማን እንደሰራቸው የማይታወቁ የተለያዩ ፒራሚዶች ተገኝተዋል። ታዲያ እነዚህን ሁሉ ምስጢራዊ ቦታዎች ማን ስራቸው? ለሚለው ጥያቄ ማስረጃዎች ሁሉ ወደ ባእድ ፍጥረታት ያመራሉ።
አኑናኪ ፊልም ለምን ተከለከለ❓
#በፈረንጆች አቆጣጠር 2006 ላይ ለእይታ ይቀርባል ተብሎ የነበረው እና የጥንት ሰመራውያንን ስልጣኔ ከባእድ ፍጥረታት ጋር በማገናኘት ይተርካል የተባለው አኑናኪ ፊልም ሳይታሰብ ሊቀር ችሏል። ከፊልሙ ጋር የሚያያዙ ማንኛቸውም ነገሮች እንዲጠፉ የተደረጉ ሲሆን፥ ምክንያቱ በግልጽ ባይታወቅም፥ በፊልሙ ውስጥ ህዝብ ማወቅ የሌለበት ነገር እንዳለ ተገልጿል።
አርኪኦሎጂያዊ ማስረጃዎች❗
በ'አል ኡቤድ አርኪኦሎጂ ጣቢያ ሰባት ሺህ ዓመት ያስቆጠሩ የእባብ መሰል ሰው እጅ ስራዎች ተገኝተዋል። የእጅ ስራዎቹ የጥንት ሰመራውያን እንደሆኑ ተነግሯል። በተጨማሪም የተለያዩ የዋሻ ላይ እና ብራና ላይ የተሳሉ የባእድ ፍጥረታት ይገኛሉ።
ቅዱሳት መፃህፍት ስለ ባእድ ፍጥረታት
ከመፅሐፈ ሄኖክ በተጨማሪ
በመፅሐፈ ዜና ምስጢር ሌሎች ዓለማት እንደሚገኙና በውስጣቸው የተለያዩ ፍጥረታት እንደሚገኙ ይገልጻል። ከእነዚህም መካከል አንድ ሺህ ዓመት ኖረው(ልክ ፊልሞች ላይ እንደምናየው እንደ ቫምፓየሮችና ፌኒክስ ባለሁለት ራስ ንስር) እጸ-ተሃድሶን በመጠቀም ለሌሎች ሺህ ዓመታት እንደሚኖሩ ያስረዳል።
በዩናይትድ ስቴትስ በተደረገው ጥናት ወደ 12 ሚሊዮን ሰዎች አካባቢ ሰው መሰል ተሳቢዎች ዓለምን እንደተቆጣጠሩ ያምናሉ፤ አብዛኞቹም ከእነዚህ ፍጥረታት ጋር በተለያዩ አጋጣሚዎች እንደተገናኙ እና መኖራቸውን በተለያዩ አጋጣሚዎች እንዳረጋገጡ ይታሰባል።
ባእድ ፍጥረታት በመካከለችን አሉን❓
#የሴራ ተመራማሪዎች ባእድ ፍጥረታት በኤሪያ 51 እና ሌሎች ምስጢራዊ ቦታዎች ከሰው ልጆች ጋር እንደሚዳቀሉ በየጊዜው ይናገራሉ።
ተዋናዩ ጋሪ በዚ 5 parts of my brain contain alien power on the intergalactic highway of existence
ቢሊየነሩ ሪቻርድ ብራንሰን “I've been to space 4 times, & impressed aliens by telling them I'd been to earth 5 times!”
ኒኮላስ ኬጅVየኦንላይን ንግድ አገናኝ የሆነው ጃክ ሞርድ ባንድ ወቅት ከ 140 ዓመት በፊት በሲቪል ጦርነት ተሳታፊ የነበረ ያንድ ወታደር ፎቶ ለቅቆ ነበር። የለቀቀው ፎቶ ከኒኮስ ኬጅ ጋር ተመሳሳይ ነው።"በየሰባ አምስት አመት ራሱን የሚያድስ እና ዘላለማዊ ቫምፓየር" በማለት ኬጅን ኒኮላስ ሞርድ ገልጾታል።
ኬኑ ሪቭስ የ'ማትሪክስ' ፊልም ተዋናዩ ኬኑ ሪቭስ ዘላለማዊ ወይም ቫምፓየር ሳይሆን እንዳልቀረ ብዙ ጊዜ ይነሳል። መልኩን፣ አላማውን እና ስራውን እየቀየረ በየዘመናቱ ሳንመለከተው እንዳልቀረም ይነሳል። ከዚህ ጋር በተያያዘ ለተጠየቀው ጥያቄ ባንድ ወቅት “We’re all star dust baby.” በማለት መልሶ ነበር።
All humans are susceptible to the illusion-of-truth effect; the more we hear something, the more likely we are to believe it's true. Google fact
"ውሸት ሲደጋገም እውነት ይመስላል።" ሀገርኛ አባባል
#ዓለምን አናውቃትም የሚባለው ያለምክንያት አይደለም። ዓለምን የሚመሯት ጥቂት ሰዎች ናቸው የሚባለውም እንዲሁ። አብዛኛው የዓለም ህዝብ የሚያውቀው ከልጅነቱ ጀምሮ በየሚዲያው የሚነገረውን የውሸት አጀንዳ እና ፕሮፓጋንዳ ነው። እውነታውን እንዲያውቅ አይፈለግም። እውነታውን እንዳያውቅ በተለያዩ በምስጢር ማህበረሰቡ በተፈጠሩ አጀንዳዎች ይጠመዳል። በዚህም ዋናውን ሴራ ከነመፈጠሩ ይረሳዋል። የአእምሮ አጠባ የሚባለውም ይህ ነው። አብዛኛው ሰው ተመሳሳይ ነው። መንቃት ለፈለገ ግን ጊዜው አሁንም ገና ነው።
0 Comments