ቡዳ ማለት በዓይኑ በማየት ብቻ ሰዎች ላይ ጉዳት ሊያደርስ ይችላል ተብሎ የሚታመንበት መንፈስ ወይንም ሰው ነው። ይሄ አይነት እምነት በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኝ ሲሆን ለአነሳሱም ከዛር መንፈስ ጋር ተመሳሳይ አፈ-ታሪክ አለው።
ቡዳ የዛር ጋኔን ምሪት፣ እጀ ሰብ፣ አይነ ወርቅ፣ አይነ ወግ ሰውን የሚይዝ የሚያሳብድ እንደ ጅብ የሚያስጎነብ የሚያስነክስ የዛር መንፈስ ነው። የቡዳ መንፈስ እንደ ቆሌ ዛር አድርጎ የያዘውን ሰው ወደ ጅብነት እንዲቀየር ማድረግ ይችላል። ይህውም በአስማት ሀይል ጅቡን ይጠራና የተደገመበት #የከብት_ወተት ይሰጠዋል ከጅቡ የተረፈውን ወተት ሰውየውን ያጠጣዋል ሰውዬም ወደ ጅብነት ይቀየራል። ብዙን ጊዜ ቡዳ ሰውን ሚበላው በደም ግባትና፣በአይን ከለር ነው። አንዳንዴ ደሞ የተባላው ሰው በዛው ቀን ወይም ከአመታት በሁዋላ ሊያውቅ ይችላል በቡዳ መንፈስ መጠቃቱን። ቡዳ ሰዎችን ብቻ ሳይሆን እንስሳትን በማክሳት፣አውድማን በማውደም ይታወቃ። በቡዳ ተበልቶ ሞቶ የተነሳ ሰው ምንም የማያውቅ ሲሆን እጁ ላይ እፀ መሰውር ይቀብሩበትና ከሰዎች እንዲሰወር ያረጉታልም ይባላል።
"የቡዳ አፈ-ታሪክ"!
የቡዳን አመጣጥ የሰውን ልጅ አጥኝው (አንትሮፖሎጅስት) ሬምኒክ መዝግቦት ይገኛል። እንደ አፈ ታሪኩ አገላለጽ፣ አዳም እና ሔዋን ከገነት ከተባረሩ በኋላ 30 ልጆች የነበሯቸው ሲሆን አንድ ቀን እግዚአብሔር ሔዋን ልጆቿን እንድታሳየው ጠየቃት። እርሷ ግን በመፍራት 15ቶቹን እና ቆንጆ የሆኑትን ልጆቿን በዋሻ ደብቃ 15ቱን ብቻ ለእግዚአብሔር አሳዩ። እግዚአብሔርም በውሸቷና በአለመታዘዟ በማዘን ዋሻው ውስጥ ያሉት 15ቹ ልጆች የተረገሙና መጥፎ እንዲሆኑ ተራገመ። አንድ አንዶቹ ልጆች ግን እግዚአብሔርን ይቅርታ ጠየቁ። አምላክም በመራራት ገሚሶቹን ቀበሮ፣ ጥንቸል ወዘተ አደረጋቸው። ገሚሶቹን ደግሞ ሰው እንደሆኑ ትቶ ግን የሰይጣን መልዕክተኛ እንደሆኑ እንዲቀጥሉ አደረገ። እኒህ እንግዲህ የቡዳ ሰዎች የቀደሙ ወላጆች ናቸው። ሬምኒክ የመዘገበው አፈ ታሪክ ሰፊ እምነት አይደለምና አብዛኞቹ ሰምተውት አያውቁም። በአንዳንድ ሥፍራ ብቻ የሚታመን ሊሆን ይችላል።
በመጽሐፍ ቅዱስ አስተያየት ስለዚህ ትምህርት አንዳችም አይገኝም። እንኳን «ዛር» ወይም «ቡዳ» የሚሉት ቃላት በመጽሐፍ ቅዱስ በፍጹም አይገኙም። ሆኖም የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ይህን ትንሽ ይመስላል። በመጽሐፈ ኩፋሌና ሌሎች መጻሕፍት መሠረት፣ የአዳምና የሔዋን ልጅ ቃየል ወንድሙን አቤልን ከገደለው በኋለ ከእኅቱ ጋራ ተባረረ። የቃየል ልጆች በዘመናት ላይ እጅግ በደለኞች ሆኑ። የአዳምና ሔዋን ሌላ ልጅ ሴት ግን ጻድቃን ልጆች ወለደ፤ የእግዚአብሔርም ልጆች ተባሉ። ሴት እራሱ ከሞተ በኋላ ልጆቹ አመጸኞች ሆኑ፣ የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ ንቀው ወደ ቃየል ልጆች ወረዱና ከነርሱ ጋር ተደባለቁ፤ አብረው ክፉ ልጆች (ኔፍሊም) ወለዱ። እግዚአብሔር ማየ አይኅ ያመጣው ስለዚህ ነው ይባላል። ከሰው ልጆች ኖህና ቤተሠቡ ብቻ አመለጡ፤ ዳሩ ግን በጥፋት ውኃው የጠፉት ክፉ ሰዎች አስማተኞች ስለ ነበሩ፣ የኖህን ልጆች በፈተና ለማታለል እስከ ፍርድ ቀን ድረስ አጋንንት ሆነው እንዲቆዩ እግዚአብሔርን ለመኑት። እግዚአብሔርም በምኅረቱ እንግዲህ 10 ከመቶ (አንድ አሥረኛ) ያለ ሰውነቶች ክፉ መናፍስት ብቻ ሆነው የሚሰሙዋቸውን ሰነፎች ለማታለል እስከ ዕለተ ደይን ድረስ እንዲቆዩ ፈቀዳቸው። (ኩፋሌ 10፡3-7)
በቡዳ መበላት እና ለዚህ በሽታ መድሃኒት ነው ተብሎ የሚሰራበት ዘዴ!
አንድ ሰው በፈራ ጊዜ፣ በደነገጠ ጊዜ በቡዳ የመበላት ዕድሉ ከፍተኛ ሆነ ተብሎ በዚሁ ነገር በሚያምኑ ሰዎች ይገለጻል። ቡዳ በሶስት አይነት መንገድ ሰውን ይበላል ተብሎ ይታመናል፣ ይሄውም ወደ ጅብነት በመቀየር፣ የአትክል ስር በመጠመዘዝ እና በቡዳ ዓይን በመመልከት ናቸው።
በዚሁ ባህል መሰረት አንድ ሰው በቡዳ ሲበላ በ4 አይነት መንገድ መድሃኒት ይፈለግለታል። አንደኛው ደብተራዎች ሲጸልዩለትና በጸበል ውሃ ሲረጩት ነው። ሁለተኛው ወደ ቃልቻ ቤት በመሄድ የቡዳውን መንፈስ በዛር መንፈስ በመተካት ነው። ሦስተኛው የኩበት ጭስ በማጨስ ሲሆን። አራተኛው ደግሞ በይውን ቡዳ ይዞ በማምጣት የጋለ መጥረቢያ ላይ ምራቁን እንዲተፋ በማድረግ ናቸው።
0 Comments