FHI 360 የተባለው ድርጅት ግብረሰዶማዊነት በሕግም፣ በሃይማኖትም፣ በዕሴትም ክልክል በሆነበት ሀገር ውስጥ እንዴት ሊሠራ ቻለ?

✍ ሚካኤል ዘኢትዮጵ

FHI 360 እ.ኤ.አ. በ1971 በሰሜን ካሮላይና ዩኒቨርሲቲ አማካኝነት "Family Health International (FHI)" በሚል ስም ሲመሠረት ዋነኛ ትኩረቱ በታዳጊ ሀገራት የቤተሰብ ምጣኔ እና የወሊድ መቆጣጠሪያ ዘዴዎች ላይ ምርምር ማድረግ ነበር። ሆኖም በሂደት በ2011 አካባቢ የAcademy for Educational Development (AED) ንብረቶችን በመጠቅለል ስሙን ወደ FHI 360 በመቀየር የሥራ መስኩን አስፋፋ። 
ይህም በጤና ሽፋን ስም የተለያዩ ማኅበራዊና ባሕላዊ ለውጦችን በዓለም ዙሪያ እንዲያራምድ በር ከፈተለት። ይህ ሥራው በጤና ድጋፍ ስም የገቡ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች የረዥም ጊዜ የቆየውን የኢትዮጵያ ሃይማኖታዊ ዕሴትና የሕዝብን ማንነት የሚገዳደሩ "አካታች" የተባሉ የባዕድ ርዕዮተ ዓለሞችንና የPride Month ንቅናቄዎችን በስውርም ሆነ በግልጽ እንዲያራምዱ ዕድል ሰጥቷቸዋል። እንዲህ ዓይነቱ በጤና አገልግሎት ሽፋን ሕግን ያላከበረ አካሄድ፣ በሀገር ውስጥ የሚሠሩ ተራድዖ ድርጅቶች ሊኖራቸው የሚገባውን ገለልተኝነት የጣሰ ጉዳይ ነው።

በኢትዮጵያ ውስጥ ግልጽ የሆነ የፀረ-ግብረሰዶማውያን ሕግ ቢኖርም መንግሥት እንደ FHI 360 ያሉ ድርጅቶች ርኩ*ሰትን በጤና ሽፋን እንዲያራምዱ መፍቀዱ እንደ ሥውር ድጋፍ ይቆጠራል። ይህ የሚሆነው መንግሥት ከምዕራባውያን ለጋሾች የሚገኘውን ከፍተኛ የጤና እና የልማት በጀት ላለማጣት ሲል ድርጅቶቹ "አካታችነት" በሚል ስያሜ ለሚያከናውኗቸው አጀንዳዎች ቸልተኝነትን ስለሚመርጥ ነው። በዲፕሎማሲያዊ ጫና እና በገንዘብ ጥገኝነት ምክንያት የሚደረገው ይህ ዓይነቱ ዝምታ ድርጅቶቹ የሀገሪቱን ሉዓላዊ ሕግ እና የሕዝቡን የሞራል ዕሴት እየጣሱ ሥራቸውን እንዲቀጥሉ ምቹ ሁኔታን ፈጥሯልና ራሱ ሥርዓቱም ተጠያቂ ነው።


Post a Comment

0 Comments