ብዙ ሰዎች የሚያውቁት ስለ ቢትኮይን የተነገረን ነገር፣ "Satoshi Nakamura" የተባለ ጂኒየስ ሰው ቢትኮይንን እንደሰራው፣ ነገር ግን ስለሱ ምንም መረጃ ያለው ሰው እንደሌለ ነበር። ስለ ማንነቱ፣ ስለ ኑሮው፣ ስለ አድራሻው ምንም መረጃ የለም ነበር። አንድ ያለው መረጃ የቢትኮይን ዋሌት አለው፣ እዛ ውስጥም የተወሰነ ያህል ቢትኮይን አለው፣ ያ ቁጥርም ተቀይሮ አያውቅም።
ታድያ ይህ ነገር ለኛ እውነትን ለምናስሳት ሰዎች አጠራጣሪ ነው። ከርሱ ጀርባ የሆነ የተሰወረ ነገር አለ እኛ ያልገባን የሚያስብል ነበር። እናም እንዴት ምንም አይነት መረጃ ስለሱ አይወጣም? እንዴት ሃክ ተደርጎ የሆነ መረጃ አይወጣም? እንዴት አንዲት ፍንጭ እንኳ ይጠፋል፣ በዚህ ዲጂታል ዘመን? ስለ ሮዝቻልይዶች እንኳ መረጃ በሚታወቅበት ዘመን ስለ ሳቶሺ እንዴት አይታወቅም? የሚለው ትልቅ ጥያቄን የሚያጭር ነበር።
ምናልባትም ሳቶሺ የሚባለው ሰው እውነተኛ ሰው አይደለም ይሆን? ሳቶሺ የሚባል ሰው በገሃዱ ዓለም የለም ይሆን? ለከቨር የተፈጠረ ማንነት ይሆን? ምናልባትም ልክ እንድ ዊሊያም ሼክስፒር አይነት ሰው ይሆን?
ዊሊያም ሼክስፒር፣ የኢንግሊዝና ምዕራብ ዓለምን የለወጡ እና እጅግ ትልቅ ተጽዕኖ የፈጠሩ ድርሰቶች ነበሩት። እናም ለዘመናት ሰዎች ተገርመው፣ እንዴት ይህን ያህል ነገር ሊሰራ ቻለ? የሚለው ጥያቄ ይፈጥር ነበር። በኋላ ላይ ግን አንዳንድ መረጃዎች ወጡ። ሼክስፒር የሚባለው የፈጠራ ገጸ-ባሕሪ እንጂ እውነተኛ ሰው እንዳልሆነ ታወቀ። እንዲሁም፣ የሱ ስራዎች እና ድርሰቶች ቲያትሮች የተባሉት፣ እነ ሮሚዮ እና ጂሊየት፣ ሌሎችም፣ በሱ የተፈጠሩ ሳይሆነ የሆኑ ሰዎች በቡድን ሆነው የሰሩት፣ ያንንም ስራ በአንድ ምናባዊ ሰው ስም አድርገው እንደጻፉት መረጃዎች ተገኙ።
ታዲያ የቢትኮይን ፈጣሪው ሳቶሺም ያንኑ አይነት ምናባዊ ሰው ይሆን? የሚል ጥያቄ ብንጠይቅም ለጊዜው ምንም አይነት ያንን የሚመልስ መረጃ አልነበረንም።
አሁን ግን የ Epstein Files ሲለቀቁ እዚያ ላይ የሚያስገርም መረጃ ተገኘ። ሰውየው በ MIT ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ካሉ ሳይንቲስቶች ጋ ይሰራ እንደነበር እና በገንዘብም ይደግፋቸው እንደነበር ተገለጠ። ነገሩ እንዲህ ነው።
ፋይሎቹ ላይ Epstein ከተለያዩ ሰዎች ጋር በጉዳዩ ላይ ኢሜይሎች ሲላላክ እንደነበር ታውቋል። እነዚያ ኢሜይሎችም እጅግ የሚያስደንቅ መረጃዎችን ይዘዋል።
በመጀመርያ፣ ቢትኮይን ላይ ሲሰሩ የነበሩ የኮምፒውተር ፕሮግራመሮች ቁጥራቸው፣ ዋናዎቹ 5 ሲሆነ ከዚያም ከመቶ በላይ የሚሆኑም በተለያየ መልኩ ፕሮጀክቱ ላይ የሚሰሩ ፕሮግራመሮች እንዳሉ ይናገራል። የፕሮጀክቱ ዋና መሪዎች ግን ሶስት ሰዎች እንደሆኑ በስም ይጠቅስና፣ እነሱም Bitcoin foundation ከሚባል ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት ዘንድ ይከፈላቸው እንደነበር ይጠቅሳል። በኋላ ላይ ግን ይህ ድርጅት ኪሳራ ስለደረሰበት ሶስቱ ሰዎች ክፍያቸውን ከሌላ ቦታ ማግኘት ነበረባቸው።
በዚህ ጊዜ ታዲያ ጄፍሪ ኢፕስቲን ለነዚህ ሰዎች ፈንድ መስጠት እንደጀመረ እና ፕሮጀክቱም በሱ እና ጓደኞቹ ስር እንደገባ ይናገራል። ይህም ለነሱ ትልቅ ስኬት እንደሆነ ጠቅሶ ለጓደኞዱ በኢሜይል ጽፎ ተገኝቷል። ታድያ ይህ ሁለት ወሳኝ ነገሮችን ያሳየናል።
1ኛ፣ ቢትኮይንን የሰራው አንድ ሳቶሺ የሚባል ማንም የማያውቀው የተሰወረ ጂኒየስ ሰው ሳይሆን፣ በመንግስት እና በሚስጥር ማህበራት እውቅና፣ የነሱ አንዱ ተቋም በሆነው MIT ዩኒቨርሲቲ፣ ከአንድ በላይ በሆኑ ሰዎች ቡድን የተሰራ መሆኑን ነው። ይህም ልክ ሼክስፒርን እንዳልነው ማለት ነው።
2ኛ፣ ፕሮጀክቱ ሲሰራ ትልቅ በጀት ተመድቦለት እና ፈንድ ተይዞለት፣ ፈንዱም የመጣው የዓለም ሃጢአት እና ክፋት፣ አጋንንታዊነት፣ ማዕከል፣ ከሰዶም እና ገሞራ የከፋ ኃጢአት የሚሰራበት ስፍራ ላይ አለቃ በሆነው ሰው መሆኑን ነው።
ታዲያ ይህ በክፉ እና አሰቃቂ፣ ከሰዶም ኃጢአት በከፋ ኃጢአት የተጨማለቀ ገንዘብ፣ እጃችን ቢገባ ለኛ መጥፊያ ከመሆነ ውጪ፣ የአጋንንት ተገዢ እንድንሆነ፣ ወደ ሲዖል እንድናምዘገዝግ ከማድረግ ውጪ ሌላ ምን ጥሩ ወይም ጠቃሚ ነገርን ይዞልን ይመጣል?
ስለዚህ አስቡበት። ገንዘብ ሲመጣ፣ ከየት መጣ? የሚለውን መጠየቅ በጣም ጥሩ ነገር ነው። የኃጢአት እና የግፍ ገንዘብ፣ በነዚህ ሰዎች ኬዝ ደግሞ የአምልኮ ሰይጣን ገንዘብ፣ በእጃችን እንዳይገባ ለመከላከል ይጠቅመናል።
0 Comments