ከአሸባሪነት የተፈረጀው "አባወራነት"




✍ ሔኖክ ኃይለገብርኤል 

ከመጋረጃው ጀርባ የኢቬት ኩፐርና የአሉላ ፓንክረስት ምክክር

በብሪታንያ ፖለቲካ ውስጥ አባወራነትን፦ የወንድነትን ተፈጥሮ “የሴት ጥላቻ” (Misogyny) በሚል ስም ከጽንፈኝነትና ከአሸባሪነት ጋር እኩል ለመፈረጅ የምትሠራው ኢቬት ኩፐር፣ አዲስ አበባ ድረስ መጥታ ከYoung Lives ዳይሬክተር ጋር መምከሯ ለአባወራው፣ ለቤተሰቡና ለትውልድ “መልዕክት”አለው!

ኢቬት ኩፐር በሀገሯ የወንዶችን ሚና እና የአባወራውን ሥርዓት (Patriarchy ) መደገፍን “እንደ ጽንፈኝነት” ነው የምታየው። ይህንን አመለካከቷን ይዛ ከአሉላ ፓንክረስት ጋር ምን መከሩ?


በኢትዮጵያ ያለውን ነባር፣ ባህላዊና ሃይማኖታዊ የአባወራነት እሴት “ጎጂና ጽንፈኛ” ብሎ ለሚፈርጀው የእነ አሉላ ፓንክረስት Young Lives ፦”አጥኚና የፖሊሲ ምክረ ሃሳብ አቅራቢ” “ግብረሰናይ” ድርጅት ዓለም አቀፍ እውቅና ለመስጠት፣ መንግሥትንም በዚሁ የፖሊሲ ምክረሃሳብም ኢትዮጵያውያንን ምን ለማድረግ ታቅዶ ይኾን?

ኩፐር በብሪታንያ የፀረ-ሽብር ሕግን ተጠቅማ የወንዶችን ንግግርና ማኅበራዊ ተጽዕኖ ለመገደብ እንደምትፈልገው ሁሉ፣ በኢትዮጵያም “ጥናቶችን” መሠረት በማድረግ አባወራነትን በሕግ የሚያስጠይቅ ወይም እንደ ወንጀል የሚያስቆጥር አሠራር እንዲዘረጋ ግፊት ሊደረግ ይችላል።

ድርጅቱ (Young Lives) “ጥናት አደረግኩ” በሚል ሰበብ፣ የአባወራውን ሚና የሚያንኳስሱ መረጃዎችን አቀናብሮ ለኩፐርና መሰል ባለሥልጣናት ያቀርባል።

እነዚህ “ምሁራዊ” የተባሉ መረጃዎች ደግሞ የኢትዮጵያን ቤተሰብ መዋቅር ለማፍረስ እንደ ፖሊሲ ግብዓት ያገለግላሉ፤ የነገ ትውልዳችንንም ዕጣ ፋንታ ይወስናሉ!

የአባወራነትን ሥርዓት ከጽንፈኝነት ጋር ማገናኘት ማለት፣ አባት በቤቱ ላይ ያለውን የመሪነት ሚና “የጭቆናና የሽብር” አካል አድርጎ መሳል ማለት ነው።

ይህ ደግሞ በቤተሰብ ውስጥ አመጽን፣ መከፋፈልን፣ ሥርዓት አልበኝነትን፣ እሴት አልባነትን በመዝራት፣ አልጫና ቀላጭም ትውልድ በመፍጠር ሀገርን የሚሸከም ጠንካራ ትውልድ እንዳይኖር ያደርጋል።

አባወራነት የቤተሰብ ሕልውና እንጂ “ጽንፈኝነት” አይደለም! በብሪታንያ የራሳቸውን ማኅበረሰብ፣ ቤተሰብ የናዱ፣ ትውልድን ያጠፉ፣ የታሪክ ተወቃሽ፣ ተነቃሽ፣ ተከሳሽ የኾኑ ባለሥልጣናት፣ በእኛ ሀገር ባለ ግቢያቸውም ቢኾን የቡና ሥነ-ሥርዓት እየተጋበዙ የቤተሰባችንን ምሰሶ እንዲነቀንቁ አንፈቅድም!

“ኢትዮጵያዊ ነኝ” ባዩ አሉላ ፓንከረስት “በግበረሰናይ” ድርጅቱ በኩል
🚨 የሚሠራው ጥናት ምንድን ነው?
🚨 ከውጭ ጉዳይ ፀሐፊዋ ጋርስ ምን ተማከሩ?
🚨 ማንስ ይደጉመዋል?
🚨 በገንዘብ የሚረዱትስ ምን ላይና የት ያተኩራሉ?
🚨 ምን ዓይነት ጉዳዮችንስ ያስቀድማሉ?

የብሪታንያ ከፍተኛ ባለሥልጣናት በኢትዮጵያ ማኅበራዊና ቤተሰባዊ መዋቅር ላይ ተጽዕኖ ሊፈጥሩ የሚችሉ የፖሊሲ አቅጣጫዎችን ለመቅረጽ የሚያስችላቸውን “የመረጃ አቅርቦት” (Briefing) ለማግኘት ይኾን?

ከሮሚና ስትራቲ በተጨማሪ ሌላ ከኢትዮጵያውያን በላይ ለኢትዮጵያውን አሳቢና ተቆርቋሪ አገኘን! ደግሞ ሁለቱም እንግሊዛዊ ቢኾኑስ? አጋጣሚ ወይንስ...

አሉላ ፓንክረስት?

ይህ የዛሬ አስር ቀን አካባቢ የኾነ ነው! እመለሳለሁ!


Post a Comment

0 Comments