የሰውን ልጅ ፈጥረዋል የሚባልላቸው "ዩፎዎች"UFO



✍ ቲና በቀለ | ኢትዮጵያ አውታር 

ዩፎ ማለት ከስሙ ትርጉም ስንነሳ ባእድ በራሪ አካል ማለት ነው። እነዚ ለየት ያሉ ፍጥረታት #ኤሊዬን የሚል መጠሪያ የተሰጣቸው ሲሆን ሁለት እጅና እግር ያላቸው ጭንቅላታቸው ከሁሉም አካላቸው ገዘፍ ያለ ሲሆን በአስተሳሰብ ከሰው ልጅ እጅግ ይልቃሉ። እነዚህ ፍጥረታት በአሁን ሰአት በአጥኚዎች ዘንድ እንደ አምላክ እየታዩና በተጨማሪም እነኝ ኤልያኖች ባለምጡቅ አእምሮ ናቸው ምናአልባትም አለምን የፈጠሯት እነሱ ናቸው ወደሚል ድምዳሜ እየሄዱ ነው። እነዚህ ፍጥረታት በጥንት ጊዜ ወደዚሁ ምድር ይመጡ እንደነበረና #ከፈርኦናዊያንም ጋር ይግባቡ እንደነበር የሰው ልጅንም #በጉዲፎቻ ይወስዱ እንደነበር ጥንታዊ የግብፅ መፀሀፍት ያወሳሉ። አጥኝዎችም በአሁን ወቅት Dead theory ተብሎ የሚጠራውን ሰው ከዝንጀሮ ነው የመጣው የሚለውን ገሸሽ አድርገው የሰው ልጅ የዩፎ ልዩ ፍጥረት ነው ማለት ጀምረዋል።
ዓለማችን እስካሁን በሰው ልጆች ሊመለሱ ያልቻሉ እጅግ በጣም ብዙ ሚስጥራትን ይዛላች። የምንኖርበትን ምድር እንኳን ብናይ የጦር መርከቦች አውሮፕላኖች እና እንዲሁም ሰዎች  ምንም አሻራ ሳይጥሉ ሚስጥራዊ በሆነ ሁኔታ በሰሜን አትላንቲክ ውቅያኖስ በሚገኘውና ቤርሙዳ በሚባለው ቦታ ላይ መሠወር እስካሁን መላ ያልተገኘለት ክስተት ነው።

ከመሬት ሆነን በማናየው የጨረቃ ጀርባ ላይ በኤልያንስ ተሠርተው ሊሆን ይችላል ተብለው የተገመቱ ሐውልቶችና የግብጽን ፒራሚድ መሳይ ቅርጾች በሩሲያና አሜሪካ ጠፈርተኞች ታይተዋል መባላቸው ሌላ ሚስጥራዊ ነገር ነው። በተለይም በሁለቱ ሀገራት ግልፅ ማብራሪያ አልተሰጠም። የጨረቃ ጀርባ የኤልያንስ መነሻ ጣቢያ ነው ብለው የሚከራከሩም አልጠፉም። ማርስ ላይም የሰው ፊት የሚመስል ገፅታ የማርስ ውጫዊ ገጽታዋ ላይም ቫይኪንግ በተባለችው የናሳ መንኮራኩር ፎቶ ተነስቷል መባሉ በናሳም ሆነ በሌላ አካል ይህ ነው የሚባል ማብራሪያ አልተሰጠም። በአሜሪካ ግዛት ላይም "ክልል51"(Aria 51) የሚባል ኔቫዳ በተባለ የገጠር መንደር ለይ ባለ ቦታ በሰው ልጆች የተያዙ ፍጡራን ምርምር የሚደረግበት ቦታ ነው ተብሎ ይወራል።
ሳይንስ ኤልያን የሚለውን ቃል ሲተረጉመው መነሻቸው ከምንኖርባት ምድር ያልሆነ ኤልያን ሊባል ይችላል ይላል። በሳይንሱ አተረጓጎም የኤልያን ፍጥረታት ባለ አንድ ህዋስ ከሆኑ ፕሮካርዮስ ከሚባሉት ጀምሮ ከሰው ልጆች የበለጠው እጅግ በተራቀቀ ቴክኖሎጂ ላይ የደረሱትን ፍጡራን ሁሉ የሚያጠቃልል ነው። 
በተደረጉ ጥናቶች እና ፍጥረታቱን አይተናል ካሉ ሰዎች በተሰበሰበ መረጃ ኤልያንስ የተለያየ መልክና ቁመና አላቸው ጥናቶቹ እንደሚያሳዩት ከሆነ የሰው ልጅ በደረሰበት ሳይንስ እነዚህን ፍጡራን ለመግለፅ በቂ አነዳልሆነ ነው።

በአንድ መልኩ እነዚህ ፍጡራን አንድሮጂኖስ የሚባለውን የከፊል ወንድ እና በከፊል ሴት እንዳስፈላጊነቱ ፆታቸውን ይወስናሉ አጭር ቁመትና ከሰው ልጆች ተለቅ ያለ ጭንቅላት ተለቅ ያለ አይን ከሰዎች ልዩ የሚያረጋቸው ነገር ሁሉም የጋራ የሆነ ንቃተ ህሊና አላቸው የቆዳቸው ቀለም ከግራጫ እስከ ቢጫ ድብልቅ ቡኒ ከሰዎች ያነሱ አፍና ጥርሶች ትንንሽ ቀዳዳ ያላቸው አፍንጮች ጆሮ አራት ጣቶች አሏቸው። ብዙ ሰአት የማይተኙ ሲሆን እድሜያቸው እስከ 700አመት ይደርሳል ቀጭን እግር ያላቸው ሲሆን ብዙ አይራመዱም ነገር ግን በፀረ-ስበት ቴክኖሎጂ ይንሳፈፋሉ።

የጠፍር አጥኚዎች area 51 የሚል ስያሜ በሰጡት ቦታ እነዚህ ፍጥረታት ሲበሩ መታየታቸውንም ይገልፃሉ  እንደ ኤሮፕያን አቆጣጠርም 1974 ዓ.ም may 4  የናይጄርያ ክልል ውስጥ ከራዳር ውጪ የገባ ምንነቱ ያልታወቀ አካል ግንኙነት ማድረግ ባለመቻሉ #ናይጄርያ በሚሳኤል መትታ ጥላዋለች ይህም አካል ዮፎ የተባለ ከታች በፎቶ እንደሚታየው ክብ ቅርፅ ያለው ሲሆን በውስጡም ኤልያኖች የሚል ስያሜ የተሰጣቸው ልዩ ፍጡሮች እንደተገኙ ተገልጿል።

#ሳይንቲስቶች dead theory ተብሎ የሚጠራውን ሰው ከዝንጀሮ ነው የመጣው የሚለውን ገሸሽ ካደረጉ በኋላ አሁን ላይ የሰው ልጅ በራሱ የዩፎ ልዩ ፍጥረታት ዝርያ ነው ወደ ማለት ተጉዘዋል ይህም ብቻ አደለም የሰውን ልጅ ወደ #universe ያመጡት እነዚህ ልዩ ፍጡራን ናቸው በፊት ከልዩ ፍጡራን ከዮፎያውያን ጋር ነበር የሚኖረው ታድያ በአንድ ወቅት ላይ የሰው ልጅ አእምሮው ማሰብ እየቀነሰ መጣ ሀሜት ጀመረ ልዩነት መፍጠር ጀመረ ከዩፎውችም ጋር መስማማት ሲያቅተው አለምን ፈጥረው እዚህ ከእንስሳት ጋር ጥለውት ሄዱ የሰው ልጅም በዚህ ምድር ላይ ከእንስሳ የተሻለ የሚያስበው ከዮፎች አለም ስለመጣ ነው የሚል አዲስ ፍልስፍና ብቅ ብሏል ታድያ ይሄን ስስማ ትዝ የሚለኝ ሰው ዝንጀሮ ነበር ሉሲ የሞተችው አፕል ልትበላ ልትቆርጥ ዛፍ ላይ ወታነው እያለ የተቀለደብን ዘመን ነው ነገ ደግሞ ሌላ ነገር ይመጣና ይህም ይተውና ሌላ ደግሞ ይሰበክልናል። ዩፎ አምላክ ናቸው ሁሉን የፈጠሩ እነሱ ናቸው ብሎ ሳይንስ ካመነ እንዴት በፈጠሩት ፍጡር በሰው ልጅ በሚሳኤል ተመተው ይወድቃሉ?? ለማንኛውም ወደ ቀድሞው ነገር ስንመለስ እነዚ #ዩፎዎች በጣም ጨካኝና አደገኛ ተደርገው ለዘመናት ይፈሩ የነበሩ ቢሆኑም አሁን በግብፅ ጥንታዊ መፅሀፍት ላይ በተፃፈው መሠረት ደግሞ የዋህ እና አዛኝ ናቸው ወደሚል ድምዳሜ ተደርሷል እናም #የሰውን ልጅ ከላይ ሆነው የሚጠብቁት እነሱ ናቸው ወደሚልም ተደርሷል በቀጣይ ዮፎ እነማን ናቸው የሚለውን በቅዱሳት መፃህፍት እይታ በደንብ የምንዳስሰው ይሆናል።


Post a Comment

0 Comments