የክርስትያናዊ ጽዮናዊነት መሰረት እና የዘመናዊቱ እስራኤል አፈጣጠር (ክፍል 1)

ተስፋዬ ገቢሳ ( ክንፈ ሚካኤል)

ብዙ ሰዎች አሁን ስላለችው እስራኤል ተብለው ስለሚጠሩት ሕዝቦች ያለን ዕውቀት በቀድሞ ቀኝ ገዚዎች በትላልቅ የመገናኛ ብዙሃን የተቀነቀነውን የሐሰት ትርክት ነው። 

እ/ኤ/አ ከ1900 በፊት አሁን እስራኤል ተብሎ የሚጠራው፡ የፍልስጤማውያን መኖሪያ ሲሆን ለ400 አመት ገደማ በኦቶማን ቱርክ ቀኝ የሚገዛ ስፍራ ነው። በ1900 እ/ኤ/አ እንግሊዞች የአረብ ሐገራትን ኦቶማን ቱርክን በመዋጋት ከተባበራችሁን፡ ነጻ ሕዝቦች ትሆናላችሁ፡ በማለት፡ በአረቦች ከፍተኛ ድጋፍ፡ የኦቶማን ቱርክን አገዛዝ አስወገዱ። የፍልስጤም ምድር የእንግሊዝ ቀኝ ተገዢ ሆነች።
 
በታሪክ እንደሚታወቀው፡ በ1ኛው የአለም ጦርነት ወቅት፡ አሁን እስራኤል በምትባለው ሐገር 90% ነዋሪ ፍልስጤማውያን ሲሆኑ፡ አብዛኛው ሙስሊም፡ ሲሆኑ፡ ክርስቲያኖች እና 5% የሚሆኑ አይሁዶች  እንደነበሩበት ይታወቃል።    
  
የፍልስጤምን ምድር ፡ የጽዮናውያን እስራኤል ሐገር ለማድረግ ሐሳቡ የተጸነሰሰው፡ William Hechler  በተባለ የአንግሊካን ቄስ፡ ሲሆን፡የመጽሐፍ ቅዱስ የትንቢት መጽሐፍ፡ አይሁድ ወደ፡ ተቀደሰ ምድራቸው፡ እንዲመለሱ፡ ይተንብያል የሚል እምነት ነበረው።  

የኦስትሪያ ተወላጅ በሆነው፡Theoder Herzl በሚባል ሰው በስዊዘርላንድ በቤዝል ከተማ በ1896 እ/ኤ/አ የአንግሊካን ቄስ ከነበረው፡ William Hechler፡ ጋር በመገናኘት፡ የጽዮናውያን እንቅስቃሴን መሰረቱ።

የጽዮናውያን ጽንሰሐሳብ የተጀመረው፣ ወድ ጽዮን እንመለስ እና ስለ ጽዮን ዝም አልልም ከሚለው አስተሳሰብ ነው። ለዚህም ከመጽሐፍ ቅዱስ መዝሙረኛው ዳዊት እና ነቢዩ ኢሳያስ ለጽዮን ወይም ለኢየሩሳሌም የተዘመረውን መዝሙር፣ እና የተነገረውን ትንቢታዊ ቃል አብነት በማድረግ ነው። እነዚህም ጥቅሶች በመዝ=137:5-7 እና  ኢሳ=62:1 ይገኛሉ ።  
 
ይህ የጽዮናውያን እንቅስቃሴ የፖለቲካ ግብን፡  ከፍጻሜ ለማድረስ፡ የመጀመሪያው የጽዮናውያን ኮንፈረንስ፡ በስዊዘርላንድ ተደረገ። የጽዮናውያን እንቅስቃሴ መሥራች የሆነው፡ Theoder Herzl በእግዚአብሔር የመኖር ህልውና የማያምን ( Atheist): ሰው ነበር።
 
በ1896 እ/ኤ/አ Theoder Hertz በደች ቋንቋ " Judenstaat" " State of Jewish" ወይም " የአይሁድ መንግስት"፡ " ሐገረ አይሁድ" የሚል መጽሐፍ ጻፈ። እርሱም በአምስት አመት ሀገር ስትሆን፡ አያታለሁ፡ በሀምሳ አመት ደግሞ ሌሎች ሀገር ስትሆን ያያሉ ይል ነበር። ከሃምሳ አንድ አመት በኋላ ግን እስራኤል ሀገር ሆነች።   
 
Theoder Herzl፡ በ1904 እ/ኤ/አ በአርባ አራት አመቱ ከዚህ አመት በሞት ተለየ፡ የኬሚስትሪ ፕሮፌሰር የነበረው፡ Chaim Weizmann፡ የጽዮናውያን እንቅስቃሴን፡ ከግብ ለማድረስ፡ በ1906 እ/ኤ/አ ከእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስቴር፡ Arthur Balfour ፡ጋር፡ ውይይት አደረጉ።  
                                   
Chaim Weizmann፡ ከ Arthur Balfour፡ ጋር ባደረገው፡ ውይይት፡ የእንግሊዝ ኤቫንጄሊካል አማኞች፡ የእስራኤል ወደ ፍልስጤም፡ ምድር መመለስ፡ የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢት ፍጻሜ፡ አካል መሆኑን አሳመኑ።              
ከ1896 እ/ኤ/አ ጀምሮ፡ በዋናነት በአውሮፓ የሚገኙትን  አይሁዶችን፡ ተበታትነው፡ ከሚኖሩ የራሳቸው ሀገር ማዘጋጀት አለብን በማለት፡ የተወሰኑ ሀገራት ለአይሁድ መኖሪያነት፣ ታጩ፡ እነዚህም፡  ኡጋንዳ፡ በኢትዮጲያ ሐረር፡ አርጀንቲና፡ እና፡ የፍልስጤም ምድር ነበሩ። 

እንግሊዝ የፍልስጤም ምድርን በቀኝ መቆጣጠር በጀመሩ፡ ጊዜ የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስቴር Arthur Balfoure ለጽዮናውያን እንቅስቃሴ ፡ ፍልስጤምን ሐገር አድርጎ፡ እንደሚሰጣቸው በ Nov 2, 1917 እ/ኤ/አ ቃል ገባላቸው፡ The Balfoure Declaration" " የባልፎር ድንጋጌ " የሚል ሰነድ ተዘጋጅቶ፡ የፍልስጤም ምድርን የእስራኤል ሀገር ለማድረግ ምቹ ሁኔታን አዘጋጀ። በወቅቱ ከአለም እጅግ ሀብታም፡ የነበረው፡ የጀርመን አሽከናዚ ይሁዲ፡የሮሽፊልድ ቤተሰብ፡ የጽዮናዊነት ግብ የሆነውን ፍልስጤምን፡የአይሁድ ሀገር የማድረግ ሥራን፡ የተፋጠነ እንዲሆን፡ እጅግ ብዙ ገንዘብ፡ ለእንግሊዝ ሰጠ።                                         
በ1939  እ/ኤ/አ መጀመሪያ እንግሊዝ  " Two state solution" በሚል ሐሳብ ፍልስጤም ራሱን የቻለ ሉዓላዊ፡ ሀገር፡ እስራኤልም ራሱን የቻለ ሉዓላዊ ሀገር፡ እንዲሆኑ በማለት፡ የፍልስጤም ምድርን ከሁለት ቦታ ከለለ ( Demarcate)።    
             
በ1945: 2ኛው አለም ጦርነት ወቅት፡ አይሁድ እልቂት፡ ተፈጸመብን ብለው፡ የአለምን መገናኛ ብዙሃን በሰበር ዜና አናወጡት።
          
ያልተፈጸመባቸውን ግፍ ሁሉ በፈጠራ፡ በማውራት፡ አዲሲቱ ልዕለ ኃያል ሀገር የሆነችውን አሜሪካን እና በወቅቱ፡ የ League of Nation " የአለም መንግሥታት ኅብረት" ድርጅትን በማሳመን፡ እስራኤል ሉዓላዊ ሀገር እንድትሆን ተመከረ።                              
እስራኤል ሉዓላዊ ሀገር እንድትሆን በሚለው ሐሳብ ላይ 33ኛው፡ የአሜሪካ ፕሬዚደንት እና ባለ 33ኛ ድግሪ የሚስጥራዊ ወንድማማቾች ሕብረት ( Freemason )፣ አባል እና ከፍተኛ ሥልጣን፣ የነበረው፣ Harry Truman አልተስማማም ነበር። 

በሁዋላ የልጅነት አብሮ አደጉ እና የቅርብ ወዳጁ የነበረው አይሁዳዊው፡ Eddie Jacobson፡ የማግባባት እና የማሳመን ( Lobbying)፡ ሥራ በመስራቱ፡ እ/ኤ/አ በ April 14, 1948 የጽዮናውያን ስለላ ኃላፊ የነበረው፡ Abraham Feinberg እና የእስራኤል የመጀመሪያው ጠቅላይ ሚኒስቴርና፡ ሀገናህ (IDF ) የሚባሉት፡ የሽምቅ ተዋጊ፡ ቡድን መሪ፡ የነበረው፡ David Ben Gurion፡ ለአሜሪካ ፕሬዚደንት Harry Truman ሁለት ሚሊዮን ዶላር ጉቦ በመስጠት፡ ሀገረ እስራኤል እንድትመሰረት፡ ውሳኔ ተሰጠ።   
                        
በ May 15: 1948 እ/ኤ/አ የአለም መንግሥታት ማኅበር " ድርጅት፣ "  League of Nation" በመባል የሚታወቀው ድርጅት፡ በ15 ሀገራት፡ የድጋፍ ድምጽ፡ እና በ9 ድምጸ ተቃውሞ፣ በፍልስጤም ምድር የእስራኤልን ሉዓላዊ ሀገርነት በአዋጅ አጸደቀ።
 
በአውሮፓ በሚኖሩ፣ አሽከናዚ አይሁዶች፣ ጽዮናውያን፣ አቀንቃኝነት፣ እስራኤል እንደ ሉዓላዊ ሐገር ስትመሰረት፣ የኢትዮጲያ ንጉሠ ነገሥት የነበሩት፣ አጼ ኃይለ ሥላሴ፣ በአለም መንግሥታት ማኅበር፣ ስምምነት ላይ አልፈረሙም ነበር። 

ከአውሮጳ የመጡት፡ አሽከናዚ አይሁዶች በፍልስጤም ምድር ከመስፈራቸው በፊት " ሀገናህ" የተባሉ፡ አሸባሪና፡የሽምቅ ተዋጊ፡ ቡድኖች፡ በDavid Ben Gurion ሰልጥነው  ተዘጋጁ። እነዚህ በአሁን ጊዜ IDF " Israel Defense Force" በመባል ይታወቃሉ። እስራኤል እንደ ሀገር በተመሰረቱ፡ በሰላሳ አመታት ውስጥ 70% ፍልስጤማውያን፡ ገድለውና፡ አፈናቅለው አጠፏቸው።   
              
የእንግሊዞች ጠቅላይ ሚኒስቴር እና የአሜሪካ ፕሬዚደንት ለምን እስራኤል በፍልስጤም ምድር ሉዓላዊ ሀገር እንድትሆን ፈለጉ? 
                                        
ከ 1916 እስከ 1922 ዓም፣ የእንግሊዙ ጠቅላይ ሚኒስቴር LLoyd George እና  ከ1945 እስከ 1953 ዓም፣ 33ኛው የአሜሪካ ፕሬዚደንት የነበረው፡ Harry Truman ክርስቲያን ደጋፊ ጽዮናውያን፣ ( Christian Zionist): የንጥቀት ትምህርትን፣ አጥብቆ፣ አማኝ፣ ስለነበሩ፡ በእነርሱ እምነት፡ አይሁዶችን ወደ ፍልስጤም መልሰን ሉዓላዊ ሀገር ካደረግናቸው ክርስቶስ ዳግም ወደ ምድር ይመጣል፣ እኛም በደመና ተነጥቀን እንወሰዳለን፣ ብለው ያምኑ ነበር።

ይህ እምነታቸው ተፈጻሚ ሊሆን፣ የሚችለው፣ እስራኤል ራሷን የቻለች ሐገር ሆና፣ ስትገኝ ነው በማለት ብዙ፣ የኤቫንጄሊካን ፓስተሮች የሚያስተምሩት ሐቅ ነው። ይህ በሐሰት የፈጠሩት ትንቢት፣ ተፈጻሚ እንዲሆን በማለት፣ በአሜሪካ የሚገኙ፣ የፕሮቴስታንት ቤተ እምነቶች፣እጅግ ብዙ ገንዘብ መድበው ይንቀሳቀሳሉ። በእስራኤል ሶስተኛው ቤተ መቅደስ እንዲገነባ፣ ብዙ ገንዘብ ከሚያዋጡት መካከል፣ እንደ ፓስተር ጆን ሄግ፣ ያሉ፣ " Christian United for Israel " በሚል መፈክር የሚንቀሳቀሱ ናቸው። 

ዛሬ በታላላቅ መገናኛ ብዙኅን፣ የሚደረጉት፣ ፕርፓጋንዳዎች፣ ጥንተ መሰረታቸው፣ በውሸት ላይ የተገነባ ሲሆን፣ ምዕራቡ አለም ግን፣ "Collusion ( በሚስጥራዊ ስምምነት እውነትን መደበቅ ) ፣ በሚለው፣ብሒላቸው፣ የተቀረው አለምን ግራ በማጋባት፣ የራሳቸውን ድብቅ አጀንዳ ይፈጽማሉ።

አሁን ሐገረ እስራኤል በሚባለው ምድር፣ የሚኖሩት፣ አይሁዳውያን፣ ከመላው አለም የተሰባሰቡ፣ ሲሆን፣ እነዚህም አብዛኛዎች አይሁድ በእምነት እንጂ  አይሁድ፣ በዘር፣ የያዕቆብ ልጆች አይደሉም። እነዚህ ስብስቦች በሶስት የተለያዩ መጠሪያ የሚታወቁ ሲሆን፣ ከምሥራቅ አውሮፓ የመጡት ፖላንዳዊው፣ ቤንጃሚን ኔታኒያሁን የመሳሰሉት አሽከናዚ አይሁድ ፣ ሲባሉ፣ ከስፔን የመጡት፣ ሴፋርዲም፣ ይባላሉ፣ ከኢራቅ፣ኢራን፣የመን፣ ሞሮኮ፣ እና ከሌሎች መካከለኛው ምሥራቅ ሐገራት የመጡት ደግሞ፣ መዝራሂም ተብለው ይታወቃሉ። ከኢትዮጲያ የሄዱት ቤተ እስራኤልን፣ ምን ብለው እንደሚጠሯቸው፣ ያገኘሁት መረጃ የለም። ከኢትዮጲያ የሄዱት ብዙዎች አይሁድ በዘር ለመሆናቸው፣ ያለው መረጃ ድብልቅልቅ ያለ ነው። ብዙ ጥቁር አይሁዶች፣ በናይጄሪያ፣ ጋና፣ በዚምባብዌ፣ የሚኖሩ ሲሆን፣ ዘመናዊው የእስራኤል መንግስት ዕውቅና ሊሰጣቸው አልወደደም። 

ከራሺያ ወደ እስራኤል አይሁድ ነን ብለው የሄዱት አብዛኛዎቹ፣ የእስራኤል ዜግነትን በማግኘት፣ ወደ አሜሪካ እና ወደ አውሮፓ በመሄድ፣የተሻለ ኑሮን ለመኖር የወጡ ናቸው። 

የጽሑፌ መደመደሚያ የሚሆነው፣ አንዳንድ ለሆዳቸው ያደሩ የፕሮ ሰባኪዎች እስራኤልን የረገመ ይረገማል፣ የመረቃቸው ይመረቃል፣ ብሎ በማስፈራራት፣ ክርስቲያን ሁሉ፣ ከእስራኤል ጎን መቆም አለበት፣ በማለት፣ የሰይጣንን አጀንዳ፣ ያስፈጽማሉ። 

እውነተኛ ክርስቲያን፣ ለሰብአዊነት፣ እና ለእውነተኛ ፍትሕ ይቆማል፣እንጂ፣ በዘር፣ በሃይማኖት፣ በሐገር ልጅነት፣ ወገንተኝነት፣ በመነሳሳትና፣ በመገናኛ ብዙኅን የሚቀነቀነውን ሁሉ፣ዝም ብሎ በጭፍን ሳይመረምር፣ የሚቀበል፣ ሞኝ አይደለም። 

አሁን ያሉት አይሁድ፣ እስራኤላውያን የክርስቶስ ተቃዋሚዎች ( Antichrists)፣ እና ክርስቲያኖች ጌታችን እና አምላክችን ብለን የምናምነውን፣ ማሪያም የተባለችው እናቱ ፓንዴራ ከተባለ የሮማ ወታደር፣ ከጋብቻ ውጪ፣ የወለደችው፣ ሐሰተኛ መሲህና፣ ሐሰተኛ ነቢይ ነው በማለት የሚያስተምሩ፣ ናቸው።

በዘመናችን ያሉ እስራኤልውያን አብዛኞቹ " አይሁድ በምርጫ " ይህም እምነቱን በመቀበል የሆኑ ሲሆን፣ የተቀሩት ደግሞ፣" ከአይሁድ ቤተሰብ በመወለድ " የሆንን አይሁድ ነን ይላሉ። 

የዛሬው እስራኤላውያን፣ የአይሁድ፣ የቢኒያም እና የሌዊ ነገድን ብቻ የያዘ ሲሆን፣ የተቀሩት አሥሩ ነገዶችስ የት ነው ያሉት ብሎ የሚጠይቅ የለም።

- The Synagogue of Satan. Andrew C. Hitchcook.      
                   
-  The End of America.   Jeff Kinley                         
- DNA Science and Jewish Bloodline. Texe Marrs.      

-  The Thirteenth Tribe. The Khazar Empire and its heritage. Arthur Koestler                              
-  The Invention of Jewish People. Prof. Shlomo Sand

-  Israel 1948. Countdown to Nowhere. Don K. Preston. p.1-65

-  Exploding the Israel Deception.  Steve Wohlberg. p.63-72

-  Introduction to Judaism. Nicholas De Lange

-  The Invention of the Land of Israel. From Holy Land to Home Land. Prof. Shlomo Sand.

-  Armageddon. The Truth About the End of Times. Prof. Bart Ehrman.

- Nobody left behind. Insight into End-Time prophecies. p. 73-82

- Whose Land is Palestine. The Middle East problem in historical perspective. Prof. Frank H. Epp. p.104-212


Post a Comment

0 Comments