የጸረ ሰላም ኃይሎች ዝርፊያ ከምዕናባዊው ነጃሺ ትርክት እስከ መስቀል ዐደባባይ!


ሚካኤል ዘኢትዮጵ

ሃይማኖትና የእምነት መገለጫዎች ከአንድ ማኅበረሰብ ታሪክና ማንነት ጋር በጥብቅ የተሳሰሩ ናቸው። መስቀል ዐደባባይ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ታሪክ ውስጥ የዘመናት ባለቤትነትና መንፈሳዊ ትርጉም ያለው ስፍራ መሆኑ የዐደባባይ ሐቅ ነው። ይህ ቦታ በተለይም በዩኔስኮ የተመዘገበው የመስቀል በዓል የሚከበርበት በመሆኑ፤ ለኦርቶዶክሳዊያን ካለው ሃይማኖታዊ ፋይዳ ባሻገር እንደ ሀገር ቅርስ የሚወሰድ ነው። ቤተክርስቲያኗ ለዓመታት ስታቀርበው የቆየችው ዋነኛው የሕግ መከራከሪያ፣ ስፍራው በይፋዊ ካርታ የተመዘገበ የቤተክርስቲያኗ ርስት መሆኑን ነው። ቤተክርስቲያን በይዞታ ማረጋገጫ (ካርታ) ቁጥር 1/385/877/00 የተመዘገበና በቤተክርስቲያኗ ስም ያለ ርስት መሆኑን በይፋ ገልጻለች። የደርግ መንግሥት ስሙን "አብዮት አደባባይ" ብሎ ቢቀይረውም፣ ይዞታው ግን ለቤተክርስቲያኗ የተሰጠ እንጂ የመንግሥት እንዳልሆነ በሕግ የተደገፈ ማስረጃ አለ።

ይህ የታሪክ ባለቤትነት ጥያቄ አሁን ላይ ከሚቀርቡ አዳዲስ ትረካዎች ጋር በቀጥታ ይጋጫል። "ነጃሺ ለሀገር" በሚል መሪ ቃል የሚነሱ እንቅስቃሴዎች የታሪክ ዘረፋና የባሕል ወረራ ተደርገው የሚወሰዱባቸው ግልጽ ምክንያቶች አሉ። በመጀመሪያ ደረጃ፣ "ነጃሺ" የሚባል የግል ስም ያለው ንጉሥ በኢትዮጵያ የታሪክ ድርሳናት ውስጥ የለም። "ነጃሺ" የሚለው ቃል "ነጋሢ" ከሚለው የግዕዝ ቃል የተወሰደና "ንጉሥ" የሚል ትርጉም ያለው የሹመት መጠሪያ እንጂ የአንድ የተወሰነ ግለሰብ ስም አይደለም። በወቅቱ ለነበሩት ክርስቲያን የኢትዮጵያ ነገሥታት (ለምሳሌ አርማህ) የተሰጠ መጠሪያን እንደ ግል ስም በመጠቀም፣ አዲስ "የነጃሺ" ታሪክን ለመፍጠር መሞከር የሀገሪቱን ጥንታዊ የነገሥታት ታሪክ የማዛባትና የራስ ለማድረግ የመፈለግ ዝንባሌን ያሳያል። ይህ ዓይነቱ የታሪክ ሽሚያ፣ የቆየውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊ ማንነት በመሸርሸር አዲስና ባዕድ የሆነ ትረካን በቦታው ላይ ለመተካት የሚደረግ ስልታዊ አካሄድ መሆኑን በርካታ የታሪክ ምሁራን ይገልጻሉ።

በቅርብ ዓመታት "ኢድ ዐደባባይ" በሚል ስያሜ የጎዳና ላይ ኢፍጣር ማድረጊያ ሆኖ መቅረቡ፣ በሁለቱ እምነቶች መካከል ያለውን የቆየ የመከባበርና የሰላም ድልድይ ሊያናጋ የሚችል ተግባር ነው። አንድ የእምነት ተቋም የራሱን ማንነትና ሥርዓት ለማራመድ ሲል የሌላውን ታሪካዊ ይዞታና ስያሜ ለመጋራት ወይም ለመቀየር መሞከሩ፣ ከሰላማዊ አብሮነት ይልቅ የግጭት መንስኤ ለመሆን መፍጨርጨርን ያሳያል። የቤተክርስቲያኗ የበላይ አካል የሆነው ቅዱስ ሲኖዶስ፣ "መስቀል ዐደባባይ የኦርቶዶክሳውያን እንጂ የጋራ አይደለም" የሚል ጽኑ አቋም እያአለው፤ ይህ አዲስ የስያሜ ለውጥም ሆነ በ"ነጃሺ" ስም የሚደረጉ የታሪክ ማዛባት እንቅስቃሴዎች፣ የቤተክርስቲያኗን የታሪክ ባለቤትነት የሚጋፋና ማኅበራዊ ቀውስን የሚጋብዝ "ጠብ ጫሪ" ተግባር መሆኑን በተደጋጋሚ አሳስቧል።

ከሃይማኖታዊ አስተምህሮ አንጻርም፣ እስልምና በጽሑፎቹ ውስጥ የሰላም ትርጉሙን በሚመለከት ለተለያዩ ትርጓሜዎች ሲጋለጥ ይታያል። በቁርዓን ውስጥ ጂሃድ (ተጋድሎ) የሚለው ጽንሰ-ሀሳብ በታሪክ ውስጥ ለእምነቱ መስፋፋትና ለግዛት ማስፋፊያነት በጦርነት መልክ ሲተገበር ቆይቷል። በተለይም በሱረቱ አል-በቀራህ እና በሱረቱ አል-ተውባህ ላይ የሚገኙት የሰይፍ አንቀጾች፣ እምነቱን የማይቀበሉ ወገኖችን ስለመዋጋት የሚያነሱት ሃሳብ፣ ሃይማኖቱ በፍጹም ሰላማዊ መንገድ ብቻ የተጓዘ ነው የሚለውን መከራከሪያ ጥያቄ ውስጥ ይከተዋል። ይህ ዓይነቱ አስተምህሮ በተግባር ሲተርጎም፣ እንደ መስቀል ዐደባባይ ባሉ ስፍራዎች ላይ የሚታየውን ዓይነት የባለቤትነት ጥያቄና የታሪክ ሽሚያን በማበረታታት ማኅበራዊ ውጥረትን ሲፈጥር በተግባር እየታየ ነው።

የኢትዮጵያ ታሪካዊ ዕሴቶችና የቆየው የአብሮነት ባሕል አደጋ ላይ እንዳይወድቅ ጥንቃቄ ያስፈልጋል። በአሁኑ ወቅት የሚታየው የፖለቲካ ድጋፍን ተገን በማድረግ የሌላውን እምነት ታሪካዊ ስፍራዎችና የነገሥታትን ታሪክ የመቀየር ዝንባሌ፣ በረጅም ጊዜ ሂደት በሀገሪቱ ሰላምና አንድነት ላይ ጠባሳ ጥሎ የሚያልፍ ነው። እውነተኛ ሰላም የሚገኘው በታሪክ የተረጋገጡ ይዞታዎችን በመቀማት፣ ስያሜን በማዛባት ወይም የሌለ "የነጃሺ" ንጉሥ ታሪክን በመፍጠር ሳይሆን፣ እያንዳንዱ ሃይማኖት የራሱን ድንበር አውቆና የሌላውን ክብር ጠብቆ ሲንቀሳቀስ ነው። አሁን ያለው አካሄድ የታሪክን እውነት በመጋፋትና አዲስ ትረካን በኃይል ለመጫን በመሞከር፣ በሕዝቦች መካከል ያለውን አብሮነት የሚሸረሽርና ጥላቻና ግጭትን የሚፈጥር ነው።

Post a Comment

0 Comments