ለምዕራባውያን እንዲገዙት የኛዎቹ የሸጡት ቤተሰባችን

 

ሔኖክ ኃይለገብርኤል | አባወራ | ኢትዮጵያ አውታር 
  
ቤተሰባችንን የማፍረሱን ዘመቻ ከማያውቁት ምዕራባውያን ይልቅ የሚያውቁት፣ የተማሩት፣ የወጡበት፣ የኖሩበት ነገር ግን ባፍጢም የተደፉት የራሳችን ሆዳደር ምሁራን ያጣድፉታል!

“ዠሆዳደር ምሁራን” የሚባለው ትምህርት የአባታዊ መዋቅር ምን ማድረግ ያስፈልገናል፤ በተለይም ሴቶች የሚበዛበትን ቤተሰብ፣ የሚደገውን የሕይወት ዘንባሌ እና ሃይማኖቱን የሚያይደለት በሆነ መንገድ ሊቀጠራ ይችላል። እዚህ ግዳጅ ትምህርት ልጆችን ለልቅነትና በሰውነት ላይ የሚያውቁ እሴቶች ለማጥፋት ይጠብቅ ይላል።

ቤተሰብ እንዲሁ በአጋጣሚ የቆመ ድንገቴ ስብስብ አይደለም። ቤተሰብን የመሠረተው፣ እንደ ምሰሶና መሠረት ኾኖ የተሸከመው፣ በቅጥና በሥነ-ሥርዓት ያነጸው፣ ለክብርና ስብዕና ግድ የሚለው አባታዊ (Patriarchal) መዋቅር ነው።

ይህ መዋቅር ልጆች፣ በተለይም ሴቶች፣ በአስመሳይ አታላዮች እንዳይጎዱ፣ በአድርባይ ሆዳደሮች እንዳይሸጡ፣ ክብራቸውም እንዳይገፈፍ እንደ ጽኑ አጥር ኾኖ ጠብቋቸዋል። ዛሬ ግን ይህ አጥር እየፈረሰ ነው።
የሚገርመውና የሚያሳዝነው፣ ይህንን የማኅበረሰብ ማምከኛ ዘመቻ በቀጥታ የሚያስፈጽሙት ከባዕዳን ይልቅ የራሳችን “የተማሩ” ልጆች መኾናቸው ነው።
በማስትሬትና በዶክትሬት ደረጃ የጠነቀቁ፣ “ሊቅ” የተባሉ ሰዎች በምዕራባውያን በባትሪ ተፈልገው ለዚህ ጥፋት ይሰማራሉ። “የግብረሰናይ” ተቋም ይከፍታሉ ወይም በከፍተኛ ደመወዝና ጥቅማጥቅም ከሚከፍላቸው “የግበረሰናይ” ድርጅት ይቀጠራሉ።

እነዚህ ሰዎች የወጡበትን ማኅበረሰብ እሴት፣ የኖሩበትን የቤተሰብ ሥርዓትና ያደጉበትን ሃይማኖታዊ ወግ በሚገባ ያውቃሉ። ነገር ግን ለሆዳቸውና ለጥቅማቸው ሲሉ፣ የማኅበረሰቡን የእሴት፣ የእምነት ሰነድ አሳልፈው ለጠላት በጥናትና ምርምር ስም የሚሸጡ፣ የትውልዱንም ደካማ ጎን ተጠቅመው ለጥፋትና ሞቱ አሳልፈው ለሚሰጡት ትምህርት ያጋልጣሉ።

ምዕራባውያንንና ልጆቻቸውን ያጠፋው የግዳጅ ወሲብ ትምህርት (Compulsory Sex Education)፣ ዛሬ በሀገራችን ተማሪዎች ላይ እንዲጫን ግፊት እየተደረገበት ነው። ይህ ትምህርት ልጆች ያለ እድሜያቸው ስለ ልቅ ወሲብና ስለ “መብት” እንዲያውቁ በማድረግ፣ የቤተሰብን ቁጥጥርና የአባትን ኃላፊነት ይንዳል።

የሚገርመው የነዚህ ሆዳደር ምሁራን ሸፍጥ ነው፦
የሃይማኖት አባቶችንና የሀገር ሽማግሌዎችን “እንዳያስቆጡ” ሲሉ፣ የመርዙን ስም “የሕይወት ክህሎት ትምህርት” (Life Skills Education) በማለት አሳምረው አቅርበውታል።

ስሙ ቢለወጥም፣ ይዘቱ ግን ያው ትውልዱን ከቤተሰቡና ከሃይማኖቱ ነጥሎ ለልቅነትና ለባርነት የሚዳርግ መኾኑን እነዚህ ምሁራን ጠንቅቀው ያውቃሉ።
በሌሎች ሀገራት ላይ ያደረሰውን የትውልድ ጥፋት መመርመር ሳይሳናቸው፣ ኾን ብለው ልጆቻችንን መርዝ ይግታሉ፤ የትምህርቱን ስም፣ የዝርዝሩን ዓይነት ስትሰሙ “ምን ችግር አለው...” ያስብላል። ለምሳሌ፦ የወርአበባ ንጽሕና አጠባበቅ።

እነዚህ ምሁራን አባታዊውን መዋቅር እንደ ጭቆና በመፈረጅ፣ ሴት ልጆቻችንን ከቤተሰብ ጥበቃ፣ በተለይም ከአባታቸው እቅፍ፣ ከባሎቻቸው ክንድ እንዲወጡ ይፈልጋሉ።

ለምን?

ዓላማው ሴቶችን ነፃ ማውጣት ሳይኾን፣ ከቤተሰባቸው አጥር አውጥቶ ለምዕራባውያን የባህልና የኢኮኖሚ ብዝበዛ “ሲሳይ” ማድረግ ነው። አባወራ የሌለው ቤተሰብ፣ ወንድ ጠባቂ የሌለው ቤት ለጠላት የተመቸ እንኾነ በደንብ ያውቃሉና!

ትውልዱን እያረዱ፣ ለበላተኛው ተኩላ በብልት በብልቱ እያወራረዱት ያሉት “ምሁር” የተባሉ የራሳችን ልጆች መኾናቸውን አስተውል።

ድግሪና ማስትሬት፣ ሊቅና ሊቀ-ሊቃውንት ተብለው ትውልዱ ከታነጸበት ማኅበረሰቡ ከተገነባበት እውነት፣ እምነት፣ እሴት የሚለዩት፣ ባፍጢማቸው ተደፍተው የባዕዳን ቅጥረኛ የኾኑት እነዚህን አስመሳይ፣ አድርባይ ባንዳዎች ናቸው።

አባወራው ስማኝማ! ቤተሰብህ መቅደስህ፣ አንድም ቤተመንግሥትህ ነው፤ መቅደስህ ቀዳሽ አወዳሽ ቤተመንግስትህም አርበኛ ነጋሽ አባወራ ያስፈልገዋል። ልጆቻችንን ከነዚህ “ዠሆዳደር ምሁራን መርዝ መጠበቁ ዛሬ ነገ የሚያስቦል አይደለም!

አልጨረስኩም! እመለሳለሁ!

Post a Comment

0 Comments