✍ ሔኖክ ኃይለገብርኤል | አባወራ | ኢትዮጵያ አውታር
በጾታ እኩልነት፣ መብትና ነፃነት እንዲኹም ጸረ-ጾታዊ ጥቃት ሰበብ በትውልዱ መካከል ጥርጣሬና ስጋት የሚዘራው ጠላትና ምንደኛው ማኅበረሰቡን ለምክነት ይዳርገዋል!
ጆሮ ያለው ይስማ!
ትውልዴ መስማትን እንቢ ብሏልና እውነትን ይናገሩበት ዘንድ መድረክና ዕድል የተሰጣቸውም ሰዎች ስለዚህ ጉዳይ ማውራት አይፈልጉምና ወገኔ እየጠፋ ነው።
አስተውሉ! የተደቀነብን አደጋ ከጥይት ጦርነቱ፦
🚨 ትውልድ እያጣን ነው!
🚨 ቤተሰብ እየፈረሰ ነው!
🚨 ልጆቻችን እየተበተኑ ነው!
🚨 ጋብቻ ትዳራችን መጠቋቆሚያ እየኾነ ነው!
🚨 ትዳርን ታናናሾቻችን እየፈሩት እየጠሉትም ነው!
🚨 ምን ቢማር ዶክተርና ኢንጂነር፣ ሊቅና ሊቀ ሊቃውንት ቢባል አልጫና አስመሳይ አድርባይ ሆዳደርም ትውልድ እያፈራን ነው!
🚨 የጠላቶቻችን መሳቂያና መሳለቂያም እየኾንን ነው!
🚨 ማኅበረሰባችንም እየመከነ ነው!
🚨 ሆዳደር ምሁራን ደግሞ በቁማችን እየነገዱብን ነው!
በጾታ እኩልነት፣ መብትና ነፃነት እንዲኹም ጸረ-ጾታዊ ጥቃት ማራኪ ቃላት ተሸፍኖ በልጆቻችን መካከል የሚዘራው የጥላቻ መርዝ ማኅበረሰብን አምካኝ ነው።
ለዚህ ትልቁ ማሳያ ደቡብ ኮሪያ ናት። በወንዶቿና በሴቶቿ መካከል መተማመንን አጥፍታ፣ እርስ በርስ እንዲጠራጠሩና እንዲቃረኑ አድርጋ ዛሬ ትውልድ አልባ ኾና እየጠፋች ነው።
ሴቶቻቸውን በትምህርትና በሥራ ስም ብቻ ሳይሆን፣ ወንዶቻቸውን እንዳያምኑ፣ ትዳርን እንደ ጭቆና እንዲያዩ ተደርገው ድርቅ ብለው እንዲቀሩ ተደርገዋል። ውጤቱስ? ዛሬ ደቡብ ኮሪያ የዓለም ዝቅተኛው የልደት መጠን ላይ ትገኛለች።
ይኸውም ሀገሪቷን የሚረከብ ተተኪ ትውልድ አጥታለች፤ የሰው ዘር ሊተካ የማይችልበት የጥፋት አፋፍ ላይ ቆማለች። ይህ “እኩልነት” ሳይኾን “ምክነት” ነው!
(በዚህ ዙሪያ ከዚህ በፊት የጻፍኩትን አንብብ)
ምዕራባውያን ዓለምን ያበጁ መስሏቸው በልጆቻቸው መካከል የዘሩት የጥላቻ ዘር ዛሬ መርዛማ ፍሬ አፍርቷል። ልጆቻቸው መውለድ እስካይችሉ፣ እስካይፈልጉና ትዳርን እስኪጠየፉ ደርሰዋል።
ዛሬ ለሀገር ግንባታ የሚኾን የሰው ኃይል አጥተው፣ አዛውንቶቻቸውን የሚንከባከብ ሞግዚት ፍለጋ በባህልም በእምነትም የማይመስሏቸውን ወደ ሀገራቸው ለማስገባት ይማስናሉ። እናውቃለን በሚል እብሪት ታጅረው የሄዱበት የትዕቢት መንገድ ዛሬ ራሳቸውን ወደ ማጥፋት አድርሷቸዋል።
ይህ ቅዱሱን ትዳር(ቤተሰብ) ቀሳፊ፣ ትውልድን አጥፊ መቅሰፍት ዛሬ እኛም ደጃፍ ደርሷል። ብዙዎች ይህንን እውነት እያዩት ነው፤ ነገር ግን ለማውራት፣ ለመወያየትና ማኅበረሰቡን ለማንቃት ወኔ የላቸውም።
ፈርተዋል! ልብ አልባ ሆነዋል! በሆዳቸው የታሰሩ “ምሁራን” እና “መሪዎች” ትውልዱ ሲታረድ እያዩ ዝምታን፣ አንዳንዶቹም ጥፋት ሞቱን እየጋቱት ምንዳን መርጠዋል።
ሴቶቻችን ወንዶቻቸውን እንደ ጠላት፣ ትዳርን እንደ እስር ቤት፣ መውለድን እንደ ኋላ ቀርነት እንዲያዩ በየሚዲያውና በየሥልጠናው የሚሰጠው መርዝ ነገ ቤታችንን ባዶ ያስቀረዋል።
በ”ጸረ-ጾታዊ ጥቃት” ስም ወንዱን በጅምላ “በዳይ”፣ አባወራዊውን አርበኛውን ሥርዓት “ጨቋኝ”፣ ሴቷን ደግሞ በዘላቂነት “ተበዳይ” አድርጎ የሚፈርጀው ትረካ ዓላማው አንዱን ወገን መጥቀም ሳይኾን ቤተሰብን ብሎም ማኅበረሰብን ማፍረስ ነው።
እሴታችንን ካላከበርን፣ በልጆቻችን መካከል የሚዘራውን የጥላቻ መርዝ ካላቆምን፣ እንደ ደቡብ ኮሪያና እንደ ምዕራባውያን በቁማችን መድረቃችን አይቀሬ ነው።
ይህ የጥፋት መርዝ በስውር፣ በመሃይሞችና በመንደር ወንበዴዎች የሚሰራጭ አይደለም። ይልቁንስ ከቤተ-መንግሥት እስከ ቤተ-ክህነት ባሉ ልሂቃንና ሊቃውንት ማስትሬትና ዶክትሬት በሠሩት፣ የጥቅም ሰንሰለቶችና “የግብረ-ሰናይ” ተቋማት በከፍተኛ የውጭ ብር ሞተርነት ይንቀሳቀሳል እንጂ።
ሰሞኑን ካሉን በርካታ የሲቪል ማኅበራት ድርጅቶች ጥቂቶቹ በዐዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ያቀረቡትን የ”ግብረ-ሰናይ” ሥራ ብትታዘቡ፣ ሁሉም ለማለት በሚቻል ደረጃ SRHR (Sexual and Reproductive Health and Rights) የሚባለውን ትውልድ አጥፊ መርዝ የማሰራጨት ግዴታ እንዳለባቸው እንደተቀበሉ ትረዳላችሁ።
🚨 ሴቶች ልጆቻችን ገና አፋቸውን ካልፈቱበት ልጅነታቸው ጀምረው “ወንድ ስለሚያደርስባቸው ጥቃት” ይማራሉ።
🚨 ወንዶቻቸውን በጥርጣሬ እንዲመለከቷቸውና፣ የትኛውም ቅርርብ ደስ ካላሰኛቸው “በጾታዊ ጥቃት” ስም አሳልፈው እንዲሰጧቸው ይበረታታሉ።
🚨 ወንዶቹ ደግሞ ይህንን ስጋት በተፈጥሮ ቀድመው፣ ደፍረው፣ ገፍተው ትውውቅን መጀመርና ለእጮኝነት ብሎም ለትዳር መጠየቅ እስካይችሉ ድረስ ይሰለባሉ።
🚨 ያገቡትም ወንዶች ለዓይነቱ፣ ለዝርዝሩ፣ ለመጠኑ፣ ለትርጉሙ፣ ለማብራሪያው፣ ለምሳሌው ኁልቁ መሳፍርት በሌለው “ጾታዊ ጥቃት” ትዳራቸው ፈርሶ ልጆቻቸወን ይበትናሉ።
ይህን የትውልድ ጥፋት የማኅበረሰብም ምክነት ከጠላታችን ይልቅ በራሳቸው በስሜታቸው ላይ መሠልጠን የተሳናቸው የራሳችን ሆዳደር ልሂቃንና ሊቃውንት በ”ግብረሰናይ” ስም በሚመጣ ከፍተኛ ገንዘብ እናታቸውን፦ ወላጅ እናትን፣ ቤተክርስትያንን፣ ሀገርን፤ ይሸጡበታል።
በዐዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን የተዘጋጀውን በብዙ ምሁራን የተዋቀረውን የሲቪል ማኅበራት እንቅስቃሴ “ለትውልዱ በተለይም ለሴቷ ያዘነና የተቆረቆረ” በሚል ካባ (camouflage) ስታዩ ከዚህ በፊት ያወጋኋችሁ ማርክሳዊ አብዮት በደንብ ይገባችኋል።
እናንተዬ! ለካ ገቢዎች ተመላልሶ፣ የንግድ ድርጅት ከፍቶ፣ አየር በሌለው ድርቁ-ገበያ ተመቶ፣ ከገቢዎች ጋር ከመነታረክ፤ በትውልዱ ላይ የሚነግድ፣ የገቢ ግብር የማይከፍል፣ በገቢዎችና በደንቦች የማይባረር “ግብረሰናይ” ድርጅት ማቋቋም “አዋጪ ነው!”
በእርግጥ እንደ እኔ ዓይነቱ መሃይም ሳይኾን የተማረ፣ ማስትሬትና ዶክትሬት ላይ የደረሰ እንዲሁም ከእውነት፣ እምነትና እሴቱ ተለይቶ ልብ አልባ የኾነ “ሰውነት” ይሻል!
አሁንም ብዙዎች የመናገር ዕድሉና መድረኩ ተሰጥቷቸው እምቢ ያሉትን የትውልድ ጥፋት በድጋሚ እናገረዋለሁ፦
0 Comments