ምድራዊ ሰማያት


ምድራዊ ሰማያት የሰማያተ ሰማያት አምሳያ ሲሆኑ አሁን በምድር ላይ የምንመለከታትን ፀሀይን ከበው አስራ ሁለት ሰማያት በአራት ምድብ ተቀምጠው ይገኛሉ።

በምድራዊው ሰማያት በመጀመሪያው ምድብ ማለትም እኛ የምንኖርበት ምድር የምትገኝበት ስፍራ አራት ፊት ባለው የሰው አምሳል ይጠበቃል።

እኛ ከምንኖርበት በስተሰሜን የሚገኙት ሰባት ምድራዊ ሰማያት አራት ፊት ባለው የንስር አምሳል ይጠበቃሉ።
እኛ ከምንኖርበት መሬት በስተምዕራብ ሶስተኛው ምድብ አራት ፊት ባለው የአንበሳ አምሳል ይጠበቃሉ። እኛ ከምንኖርበት በስተደቡብ የሚገኘው ስፍራ አራት ፊት ባለው የላም አምሳል ይጠበቃሉ። ምድራዊ ሰማያት በምድር ላይ ሆነን የምንመለከታትን ፀሀይን በአራት ምድብ ከበው ይገኛሉ።

በሰሜን የቅዱሳንና የአእዋፍ መኖሪያ ሲሆን በስተምሥራቅ የሰዎች መኖሪያ በስተምዕራብ የዱርአራዊት መኖሪያ እና ሲኦል የሚገኝበት ሰፍራ ሲሆን በስተመጨረሻ በስተደቡብ እንደ ዳይኖሰር ግዙፍ የሆኑ እንስሳትና  ስማዝያ(የአየር ላይ ጋኔኖች) የሚኖሩበት ነው። ነጮቹ ፕላኔት የሚሉዋቸው እነዚህ ምድራዊ ሰማያት ሲሆኑ UFO የሚሉዋቸው  ደግሞ በስተደቡብ የሚገኙትን የስማዝያ ወገኖች ነው። ማርስ ደግሞ ምድር በምትገኝበት የመጀመሪያ ምድብ የምትገኘውን ፍጡር የማይኖርባት ግን ከመሬት ጋር የምትመሳሰለውን ባዶ ስፍራ ነው።


Post a Comment

0 Comments