✍️ ጦማሪው ፈላስፋው ጭሰኛ
ስለ ደሃ አገራት ጦርነት ሲነግሩህ "የዘር ግጭት" ነው ይሉሃል። "የሃይማኖት ጦርነት" ነው ይሉሃል። "የፖለቲካ ሽኩቻ" ነው ይሉሃል። ይሄ ለህዝብ የሚነገር ተረት ነው! እውነተኛው ታሪክ ግን... ትርፍ (Profit) ነው! ነዳጅ፣ ወርቅ፣ አልማዝ፣ ኮባልት፣ ዩራኒየም፣ ሊቲየም... ያንተ ስልክ የሚፈልጋቸው፣ የሚሳኤል ፋብሪካዎች የሚራቡላቸው፣ ኃያላን መንግስታት የሚገነቡባቸው ማዕድናት ናቸው የጦርነቱ ሞተሮች!
የዘመናዊ ጦርነት "ቆሻሻ" ሚስጥር!
ኃያላን አገራት አሁን ፊት ለፊት አይጋጠሙም። በደካማ አገራት ውስጥ ወኪል ያበጃሉ።
* አማፂያንን በገንዘብ ይረዳሉ
* መንግስታትን ያስታጥቃሉ
* መሪዎችን ይሾማሉ፣ የማይመቻቸውን ይሽራሉ
* መጀመሪያ "ትርምስ" ይፈጥራሉ... ከዚያም
"መፍትሄ" እንሸጥላችኋለን ብለው ይመጣሉ!
ጦርነት ለእነሱ "ኢንቨስትመንት" ነው፤ ትርምስ ለእነሱ "ገበያ" ነው፤ የሰው ልጅ ሬሳ ደግሞ "ትርፍ" ነው!
የንግዱ አሰራር እንዲህ ነው፦
* ሀብታም ግን ደሃ የሆነች አገርን መለየት።
* በፖለቲካ ወይም በኢኮኖሚ ማተራመስ።
* ተፋላሚ ወገኖችን በድብቅ ማስታጠቅ።
* አገሪቱ በደም እንድትታጠብ መተው።
* "ሰላም አስከባሪ"፣ "ብድር" እና "ኮንትራት" ይዞ መግባት።
* ሀብቷን ለብዙ አስርት ዓመታት መጋጥ። ጦርነቱ መቼም አያልቅም፤ ምክንያቱም ሰላም ለንግዳቸው አይበጅም!
ጦርነት የማይቆምባቸው አገራትና "ምክንያቱ"፦
* 🇨🇩 ኮንጎ፦ ኮባልት፣ ወርቅና አልማዝ አላት። ከ1990ዎቹ ጀምሮ 6 ሚሊዮን ህዝብ አልቋል። ያንተ ስልክ ባትሪ ከዚህ ደም ጋር የተያያዘ ነው!
* 🇱🇾 ሊቢያ፦ የአፍሪካ ትልቁ ነዳጅ አላት። ኔቶ ከገባ በኋላ አገሪቱ ፈረሰች። አሁን የባሪያ ገበያና ማለቂያ የሌለው ጦርነት አለ፤ ነዳጁ ግን ይፈሳል!
* 🇸🇩 ሱዳን፦ ወርቅና የቀይ ባሕር ስልታዊ ቦታ። የውጭ መሣሪያ፣ የውጭ ገንዘብ፣ የውጭ ዝምታ! በየአስር ዓመቱ ስሙ የሚቀየር የደም ንግድ!
* 🇾🇪 የመን፦ የንግድ መርከቦች መተላለፊያ። የውጭ ቦምቦችና ረሃብ። የአለም ትልቁ ሰብአዊ ቀውስ ቢሆንም በአለም ችላ ተብሏል!
ለመሆኑ የኃያላኑ ፍላጎት ምንድነው?
* አሜሪካ፦ የንግድ መስመሮችን፣ የነዳጅ ዋስትናንና የድርጅቶቿን የበላይነት ትፈልጋለች።
* ቻይና፦ ማዕድናትን፣ የመሰረተ ልማት ቁጥጥርንና የብድር ወጥመድን ትፈልጋለች።
* ሩሲያ፦ ወታደራዊ ይዞታን፣ የማዕድን ኮንትራቶችንና ጂኦ-ፖለቲካዊ መናጋትን ትፈልጋለች።
ሁሉም ባንዲራቸው ቢለያይም... "ርሀባቸው" ግን አንድ ነው!
የጭሰኛው ማጠቃለያ፦⚠️
እነዚህ ጦርነቶች ለሰላም ቢሆን ኖሮ... ከረጅም ጊዜ በፊት ያበቁ ነበር። ስለ ሽብርተኝነት ቢሆን ኖሮ... መፍትሄ ያገኙ ነበር። ስለ ዲሞክራሲ ቢሆን ኖሮ... በአንድ አገር ላይ ለ50 ዓመት አይደገሙም ነበር። ጦርነቶቹ የሚቀጥሉት ጥቅም ስላለ ነው! ጥቅሙ ግን መቃብር ለሚቆፍረው ህዝብ ሳይሆን፣ ርቀት ላይ ሆኖ ቼክ ለሚፈርመው ነጋዴ ነው!
ኢትዮጵያዊ ሆይ... ንቃ! አያቶችህ ዓድዋ ላይ የተዋጉት ይሄንኑ የደም ነጋዴ ስርአት ነው!
0 Comments