✍ ሔኖክ ኃይለገብርኤል | አባወራ | ኢትዮጵያ አውታር
ትውልዱን በእኩልነት፣ መብትና ነፃነት ስም ለማጥፋት፣ ማኅበረሰቡን ለማምከን በሁለቱ ተቋማት መንግሥትና ቤተክርስትያን ውስጥ ሰርገው የገቡት በሀገሪቷ ፍቅር የተቃጠሉት ምዕራባውያን ሸፍጥ ሲገለጥ!
"ኢትዮጵያን እንወዳለን" የሚሉ ድምፆች በበዙበት በዚህ ዘመን፣ ከቃላቱ በስተጀርባ ያለውን መርዛማ ሸፍጥ መመርመር ግድ ይላል።
በተለይ እንግሊዛውያን "የበግ ለምድ ለባሾች" በሀገሪቱ የጀርባ አጥንት በሆኑት በመንግሥትና በቤተክርስቲያን ተቋማት ውስጥ ሰርገው በመግባት፣ ትውልዱን የማምከንና ቤተሰብን የመበተን ሥራቸውን በረቀቀ መንገድ እያከናወኑ ይገኛሉ።
የመጀመሪያው የእንግሊዛውያን "ትውልድን አጥፊ መርዝ" የሚረጨው በሮሚና ስትራቲ ፕሮጀክት ድልድል አማካኝነት ነው።
ይህ አካል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ክርስቲያናዊ ተራድዖ ኮሚሽን (EOC-DICAC) በኩል መንገዱን አመቻችቶ፣ በቤተክርስቲያኗ ስር ባሉ ነባር ተቋማት (እንደ ማኅበረ ቅዱሳን) እና ዐዳዲስ (እንደ ፍኖት የማማከርና ሥልጠና...) ባሉ ንዑስ ተቋማት ውስጥ ስር እንዲሰድ ተደርጓል።
በ"ጾታ እኩልነት፣ በመብት፣ ነፃነትና እና በ"ጸረ-ጾታዊ ጥቃት" ስም የሚካሄደው ይህ ዘመቻ፦
ሴቷ የሥነ-ተዋልዶ ጤና አገልግሎትና መብቷን (SRHR) ያለገደብ መጠቀም እንዳለባት ይህም "መብትና ነፃነቷ" እንደኾነ ይሰብካል።
በአካሏ ላይ "ያለማንም—እንኳን ለባዕድ ለባሏም" ጣልቃ ገብነት የመወሰን፣ የወደደችውን የማድረግና ያልወደደችውንም ሕይወት (ጽንስ) የማስወገድ ሙሉ መብት እንዳላት መርዝ ይረጫል።
ማስረጃ፦በልማት ተራድዖዋ በኩል ያሳተመቻቸውን ሦስት መጻሕፍት ተመልከት፦
1ኛ የፕሮጀክት ድልድል የተዘጋጀ የማሠልጠኛ መመሪያ (2013)
2ኛ በሥርዓተ ጾታ እኩልነት የተቃኘ ወንድነት
3ኛ የማኅበረሰብ ውይይቶች
ይህ መርህ የቤተሰብን ቅዱስነት የሚንድ፣ አባወራውን ከኃላፊነቱ የሚያገልና ሴቷን ለብቻዋ ለጥፋት አሳልፎ የሚሰጥ ስልት ነው። ሮሚና ስትራቲ በዚህ የጥፋት መንገድ ላይ ሙሉ ፈቃድ አግኝታ በመስራት፣ የቆዩ እሴቶችን አዳክማ የራሷን የጥፋት መዋቅር አጠናክራ ትገኛለች።
ያቋቋመቻቸውም ኾኑ ነባሮቹ ባገኙትጨሥልጠናና የገንዘብ ድጋፍ የሚጠበቅባቸውን በመፈጸም፣ በቤተክርስትያኗም በመበረታታት ቀጥለዋል።
በሌላ በኩል፣ "ኢትዮጵያዊና ሀገር ወዳድ" ተብሎ የሚታወቀው አሉላ ፓንክረስት፣ በ"ያንግ ላይቭስ" (Young Lives) ፕሮጀክት አማካኝነት ሌላ የጥፋት ግንባር ከፍቷል። ይህ አካል ነባር፣ ትውፊታዊና ሃይማኖታዊ የሆነውን የአባወራ ሥርዓት በምርምር ስም እየኮነነ ይገኛል።
ሴቶች ገና በለጋ እድሜያቸው ስለ ሥነ-ተዋልዶ ጤና አገልግሎትና መብት (SRHR) እንዲማሩ፣ ይህ ትምህርት ከመደበኛው የባዮሎጂ ትምህርት ወጥቶ "በተናጥል" እንዲሰጥ የፖሊሲ ማሻሻያ ምክረ ሐሳብ አቅርቧል።
Schools can play an important role in increasing adolescents’ understanding of SRH issues. Increasing the coverage of SRH in curriculums beyond basic biology lessons could help to ensure both girls and boys receive ageappropriate information.
Promoting discussion of SRH through peer group support networks in schools (including girls’ clubs) and community groups (including youth clubs), could also provide a supportive environment to improve knowledge and help to shift cultural beliefs and challenge discriminatory gender norms.
ይህን የጥፋት ሪፖርት ለማዘጋጀት ከ25 ዓመት በላይ "ጥናት" ሲያደርግ መቆየቱና ውጤቱንም ለኢትዮጵያ መንግሥት ሳይኾን ለገዛ ሀገሩ (ለእንግሊዝ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ማቅረቡ፣ ዓላማው የኢትዮጵያን ትውልድ ማነጽ ሳይሆን የጌቶቹን የጥፋት ተልእኮ መፈጸም መኾኑን ያሳያል።
የእንግሊዝ መንግሥትም ይህንን "የጥናት ውጤት" ይዞ የኢትዮጵያ አቻውን "የሰዎችን መብት ካላከበርክ እርዳታ አታገኝም" እያለ የሚያስጨንቅበት ይኾናል።
እነዚህ አካላት የሚሰብኩት የሥነ-ተዋልዶ ጤና አገልግሎትና መብት (SRHR)፣ ምዕራባውያን የገዛ ልጆቻቸውን ያጠፉበት መሣሪያ ነው።
ይህ ስልት፦
🚨 ልጆች ያለ ዕድሜያቸው ስለ ወሲብ እንዲያውቁ ያደርጋል።
🚨 በመብት ስም በልቅነት እንዲዳሩና ዝሙትን እንደ ሥልጣኔ እንዲቆጥሩ ይገፋፋል።
🚨 ፅንስን ማስወረድና ራስን ማምከንን እንደ "ነፃነት" በመስበክ ትውልዱ እንዲጠፋ ያደርጋል።
🚨 በማኅበረሰባችን ዘንድ የተወገዙና ኃጢያት የኾኑ ልማዶችን ያበረታታል።
ጠላትህ በሩቅ አይደለም፤ በቤተክርስቲያንህ ቅጽርና በልጆችህ የትምህርት ፖሊሲ ውስጥ ሰርጎ ገብቷል። "ኢትዮጵያን እንወዳለን" የሚሉህ የበግ ለምድ ለባሾች ተኩላዎች፣ ዓላማቸው አንተን ማዳከም፣ ሚስትህን ማሳሳትና ትውልድህን ማጥፋት ማኅበረሰብህንም ማምከን ነው።
ቤተሰብህንና ሀገርህን ለመጠበቅ ንቃ አትፍዘዝ! እነዚህን በምርምርና በእርዳታ ስም የሚመጡ የጥፋት መርዞችን አጥብቀህ ተቃወም። የአባቶቻችን የጸና አባወራዊ ሥርዓት ለትውልድ መድኃኒት እንጂ የጭቆና መሣሪያ አይደለም!
"Life Skills Based Health Education" ወይም "በህይወት ክህሎት ላይ የተመሰረተ የጤና ትምህርት" ስለሚባለውስ ምን ያክል ታውቃለህ? ከዘጠነኛ ክፍል ጀምሮ የሚማሩ ወንድም እህቶቻችሁን ጠይቃችሁ ኑ አካፍሉን እስቲ!
ከዚህ በተጨማሪ የቅድመ ጋብቻ ሥልጠናዎች የሴቷ መብት ምን እንደኾነ ሲያስተምሩ የሥነ-ተዋልዶ ጤና አገልግሎትና መብት ጭምር እንደ እኩልነት የሚካተትበት ነው።
አላችሁ ግን?
ስለዚህ ጉዳይ ማንም ማውራት አይፈልግም! አንድም ራሳችንንም ኾነ ልጆቻችንን አንወድምና፤ አንድም እንዲህ ዓይነት ርዕስ ነክተን ተመልካችና ገቢ ማጣት የማንፈልግ አስመሳይ አልጮች ነንና፤ ትውልዱ ላይ እየነገድን ይጠፋል!
0 Comments