1. የሁለት ጌቶች ባሪያ መሆን አይቻልም
በምስሉ ላይ የሚታዩት ገመዶች በሙሉ የራሳቸውን ፍላጎት ለማርካት ሰውዬውን ይጎትቱታል። መጽሐፍ ቅዱስ ግን እንዲህ ይላል፦
📖 "ለሁለት ጌቶች መገዛት የሚቻለው ማንም የለም... ለእግዚአብሔርና ለገንዘብ (ለዓለማዊ ምኞት) መገዛት አትችሉም።" (ማቴዎስ 6፥24)
▫️ልባችንን ለብዙ ዓለማዊ ነገሮች በሰጠን ቁጥር ማንነታችን ይከፋፈላል ፤ ሰላማችንም ይደፈርሳል።
2. የዚህ ዓለም ሃሳብና ጭንቀት
ሰውየው የታሰረባቸው ገመዶች (ሥራ ፣ ዝና ፣ ራስን መውደድ. . . . ) በወንጌል ቃል "እሾህ" ተብለው ተገልጠዋል።
📖 “በእሾኽ መካከል የተዘራው ዘር ቃሉን ሰምቶ ለዚህ ዓለም በመጨነቅና በብልጽግና ሐሳብ በመታለል ታንቆ ያላፈራውን ሰው ይመስላል።” — ማቴ 13፥22 (አዲሱ መ.ት)
▫️ እግዚአብሔርን ፊት ላይ ካላስቀደምን መልካም የሚመስሉ ነገሮች (ቤተሰብ ፣ ሥራ . . .) ሳይቀሩ ነፍሳችንን የሚያንቁ ገመዶች ሊሆኑብን ይችላሉ።
3. እውነተኛው የእረፍት ምንጭ
ሰውየው ፊቱ ላይ የሚታየው ስቃይና ውጥረት የብዙዎቻችን የዕለት ተዕለት ገጽታ ነው። ለዚህ መፍትሄው ገመዶቹን በገዛ ጉልበት ለመበጠስ መሞከር ሳይሆን ወደ ክርስቶስ መጠጋት ነው።
📖 ““እናንት ሸክም የከበዳችሁና የደከማችሁ ሁሉ ወደ እኔ ኑ፤ እኔም ዕረፍት እሰጣችኋለሁ።”— ማቴ 11፥28 (አዲሱ መ.ት)
📌 የእኔ ተወዳጆች 🧐
▫️ ቅድሚያ የሚሰጠውን ለዩ፦ በምስሉ ላይ ያሉት ገመዶች ሁሉ መጥፎ አይደሉም (ለምሳሌ፦ ቤተሰብ ፣ ጤና. . .) ነገር ግን ከእግዚአብሔር በላይ ቦታ ሲይዙ ጣዖት ይሆኑና ይጎትቱናል። ታዲያ መፍትሄው ምንድነው ትሉኝ ይሆናል "አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግስት ጽድቁንም ፈልጉ" የሚለውን መመሪያ መከተል ነው።
▫️ወገኖቼ ከ"ሰው" ገመድ ተላቀቁ፦ ማህበረሰብ የሚጎትተው ገመድ የሰዎችን ይሁንታ የመፈለግ እስራት ነው። ሰው ደስ እንዲለው ስንኖር የክርስቶስ ባሪያ መሆን አንችልም።
▫️ ውስጣዊ ሰላም፦ አእምሮአችን ሰላም የሚያገኘው በዙሪያችን ያሉት ነገሮች ሲስተካከሉ ሳይሆን ውስጣችን ያለው ማንነት በክርስቶስ ሲታሰር ብቻ ነው።
📍ስናጠቃልል
ዓለም በብዙ ገመድ ትጎትተናለች ፤ ክርስቶስ ግን በፍቅር ይጠራሃል/ይጠራሻል። ገመዶቹ እንዲበጠሱ ዛሬ ሸክምህን ለእርሱ አውርደህ ስጠው/ስጪው።
ለወዳጅዎ ያጋሩት! ሼር በማድረግ የብዙዎችን የአእምሮና የነፍስ እስራት ለመፍታት ምክንያት ይሁኑ።
0 Comments