ልሳን ስጦታ ወይስ የቋንቋ ዝባዝንኬ?

መግቢያ 

ልሳን ስጦታ ወይስ የቋንቋ ዝባዝንኬ? 

(Investigation into the Tongue Phenomenon) በአሁኑ ዘመን በክርስትናው ዓለም ውስጥ እጅግ አነጋጋሪና አጨቃጫቂከሆኑት ጉዳዮች መካከል "የልሳን ስጦታ" ቀዳሚውን ስፍራ ይይዛል።

በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች "መንፈሳዊ" እንደሆኑ ለማሳየትየሚጠቀሙባቸው ትርጉም አልባ ድምፆች፣ በውኑ በመጽሐፍ ቅዱስውስጥ ከተገለጠውና ጥንታውያን አባቶች ካስተማሩት እውነት ጋር ይገጥማሉ? ወይስ በ20ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ላይ የተፈጠረሥነ-ልቦናዊ ማጭበርበር? 

ይህ የምርመራ ጽሑፍ የችግሩን ሥርመሠረት ከቋንቋ፣ ከታሪክና ከጥንታውያን አባቶች ጽሑፎች አንጻር ይመረምራል።

1. የ"ልሳን" ቋንቋዊ መሠረት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ "ልሳን" ተብሎ ለተተረጎመው ቃል የግሪኩንመሠረት ስንመረምር፣ ቃሉ የሚያመለክተው ግልጽ የሆነ "ሰዋዊ ቋንቋን" እንጂ ትርጉም የሌለው ጩኸትን እንዳልሆነ እንረዳለን።

የግሪክ ቃል γλῶσσα 

አነባበብ ግሎሳ (Glōssa) 

 "The tongue; a language used by a particular peop.

"ምላስ (ብልት)፤ ወይም አንድ የተወሰነ ሕዝብ የሚግባባበት ቋንቋ።" በአዲስ ኪዳን ውስጥ ይህ ቃል ቋንቋን ለማመልከት ጥቅም ላይ የዋለ ሲሆን፣ ለዚህም ዋነኛው ማሳያ በሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 2 ላይየተጠቀሰው "ዳያሌክቶስ" (διάλεκτος) የሚለው ቃል ነው።

የግሪክ ቃል διάλεκτος አነባበብ (ዳያሌክቶስ (Dialektos) 

"Language or dialect of a country or district." 

አማርኛ፦ "የአንድ አገር ወይም የአካባቢ ቋንቋ/ዘዬ።" 

ሐዋርያት በጰንጠቆስጤ ዕለት የተናገሩት "ግሎሳ" (ልሳን) በሰሚዎቹዘንድ "ዳያሌክቶስ" (የአገር ቋንቋ) ተብሎ መታወቁ፣ ልሳን "ተፈላጊናሥርዓት ያለው ቋንቋ" መሆኑን እንጂ "ዝባዝንኬ ድምፅ" አለ መሆኑንያረጋግጣል።

2.የጥንታውያን አባቶች ምስክርነት (Patristic Testimony) ከ1900 ዓመታት በኋላ የተነሳው የዘመኑ ልሳን "አዲስ ፈጠራ" መሆኑን ለማረጋገጥ፣ የጥንት አባቶች ስለ ልሳን የነበራቸውን ግንዛቤእንመለከታለን።

ሀ. ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ (St. John Chrysostom) በ4ኛው ክፍለ ዘመን የነበረው ይህ ታላቅ አባት፣ በቆሮንቶስ መልእክትትርጓሜው ላይ ልሳን በሐዋርያት ዘመን ለምን እንደ ነበረና በኋላ ግንለምን እንደ ጠፋ ሲያስረዳ እንዲህ ይላል፦

 "This whole place is very obscure: but the obscurity is produced by our ignorance of the facts referred to and by their cessation, being such as then used to occur but now no longer take place." (Homily 29 on First Corinthians) 

"ይህ (ስለ ልሳን የሚናገረው) ክፍል እጅግ ግራ የሚያጋባ ነው፤ ግራ የሚያጋባ የሆነውም ስለ ተጠቀሱት እውነታዎች ባለን እውቀት ማንስና እነዚያ ነገሮች አሁን ስለ ቆሙ (ስለ ቀሩ) ነው። በዚያ ዘመን ይከሰቱ የነበሩት ነገሮች አሁን ከእንግዲህ አይከሰቱም።" 
 
ለ. ቅዱስ አውግስጢኖስ (St. Augustine of Hippo) ቅዱስ አውግስጢኖስም በተመሳሳይ ሁኔታ ልሳን ለወንጌል መስፋፋትተብሎ የተሰጠ ጊዜያዊ ምልክት እንደ ነበር ይገልጻል፦

"In the earliest times, the Holy Ghost fell up on them that believed: and they spake with tongues... These were signs adapted to the time... That thing was done for a be tokening, and it passed away." (Ten Homilies on the First Epistle of John, Homily 6:10) 

"በጥንቱ ዘመን መንፈስ ቅዱስ ባመኑት ላይ ወረደ፤ እነርሱም በልሳን ተናገሩ... እነዚህ ለጊዜው የተሰጡ ምልክቶች ነበሩ... ያ ነገር (ልሳን) ለምልክት ተደረገ፣ ከዚያም አለፈ (ቀረ)።" 

3. የምርመራው ጥያቄ (Investigative Question) እነዚህ ታላላቅ አባቶች ገና በ4ኛው ክፍለ ዘመን ላይ "ልሳንአቁሟል/ቀርቷል" ብለው ካስተማሩ፣ ከ1900 ዓመታት በኋላ በ1901 ዓ.ም በአሜሪካ የተነሳው "የአዙዛ ስትሪት" ንቅናቄ የመጣው ከየት ነው? 

አባቶች ያልተቀበሉትና በታሪክ ውስጥ ጠፍቶ የነበረው ይህ "ልምምድ" እንዴት በዘመናችን ለብዙዎች የማታለያ መሣሪያ ሆነ?


Post a Comment

0 Comments