(ክፍል 4)
እስከ ክፍል አስር ይወጣል ተከታትለው ያንቡ፦
የታፈነው ፏፏቴና የሰማይ ላይ ግንባታ
ዳዊት በዝምታው ተራራ ላይ ሆኖ ከአባ መቃርስ ጋር ጥልቅ ምልልስ ጀመረ። "አባቴ ሆይ፤ በከተማው ውስጥ ዋካንዳ ግንባታው ገና ነው ይባላል፤ እርስዎ ግን ሥራው አልቆመም ይላሉ፤ እንዴት ነው አሠራሩ?" ሲል ጠየቀ። አባ መቃርስ ወደ ሰማዩ ጠፈር እየጠቆሙ በረቂቅ ድምፅ መለሱለት። "ልጄ ሆይ፤ መረቡ የሰው ልጅን የሚያታልለው በዓይን በሚታየው ቁስ ብቻ ነው። ዋካንዳ ግንባታው መሬት ላይ ድንጋይ ከመደረደሩ በፊት፣ በጠፈር ላይ በሳተላይት መረቦችና በሞገድ አጥር ተገንብቶ አልቋል። በሰማይ የተዘረጋው የዲጂታል መጋረጃ የሰውን ልጅ ንቃተ ሕሊና ለመቆለፍ የተሠራው የዋካንዳ ዋነኛው ክፍል ነው። መሬት ውስጥ ደግሞ የኃይል መሳቢያ መሣሪያዎች ተቀብረው የታቦተ ጽዮንን ንዝረት ለመጥለፍ በየሰከንዱ ይሠራሉ። ሥራው በሰማይም በምድርም አልቆመም፤ መረቡ የሰውን ልጅ አፍኖ ለመያዝ በከፍተኛ ፍጥነት እየተንቀሳቀሰ ነው" አሉት።
ዳዊት ስለ ሀገሪቱ ጦርነትና ግርግር ሲጠይቃቸው፣ አባ መቃርስ የሰጡት መልስ የመቃብር ድንጋይን የሚፈነቅል ነበር። "ይህ ጦርነት ለ መረቡ ምቹ የሆነ የንቃት መጠለፊያ ሜዳ ነው" አሉት። "ጦርነት ማለት የሰውን ልጅ ንዝረት ወደ ፍርሃት፣ ወደ ቁጣና ወደ ሐዘን ዝቅ ማድረጊያ ዘዴ ነው። ነፍሳት በድንጋጤ ሲታጠሩ፣መረቡ በሳተላይት አማካኝነት የነፍሳቸውን ኃይል ለመመጠጥ ይቀልዋል። ለዚህ ነው በየቦታው ግጭት እንዲነግሥ የሚደረገው። እንዲያውም ያ ታላቁ ፏፏቴ (ጢስ አባይ) የታፈነውና የተገደበው ለኃይል ማመንጫ ብቻ እንዳይመስልህ። ውኃው መለኮታዊ መረጃን ይዞ ለምድሪቱ የሚያከፋፍል የሕይወት ደም ስር ነበር። ውኃው ሲታፈን የምድሪቱ የንዝረት ፍሰት ተገታ፤ ይህም መረቡ የሰውን ልጅ ንቃት በቀላሉ እንዲቆጣጠር በር ከፈተለት" ሲሉ ከመጋረጃ ጀርባ ያለውን ሴራ ገለጡለት።
ዳዊት በከፍተኛ ድንጋጤ ውስጥ ሆኖ፣ ስለ 5ጂ (5G) ማማዎችና ስለ ታቦተ ጽዮን ምስጢራዊ ትስስር ጠየቀ። አባ መቃርስም እንዲህ አሉ፦ "እነዚያ ማማዎች የተገነቡት የታቦተ ጽዮንንና የጽላቱን መለኮታዊ ጂኦሜትሪ በመጥለፍ ነው። ታቦቱ ሕይወትንና ፈውስን እንደሚረጭ ሁሉ፣ ማማዎቹ ግን ያንን ንዝረት ገልብጠው የዲጂታል ሞትንና የንቃተ ሕሊና ድንዛዜን ይረጫሉ። ማማዎቹ የተቀመጡት በምድሪቱ የኃይል መስቀለኛ መንገዶች ላይ ነው፤ ዓላማቸውም የሰውን ልጅ የዘር ግንድ ከመለኮታዊው መረጃ ጋር እንዳይገናኝ መጋረድ ነው። ነገር ግን የሥላሴ ባሪያዎች ይህንን ሴራ የሚያፈርሱበት ማስተር ቁልፍ አላቸው። እሱም የሰሎሞን ቀለበት ንዝረት ነው" አሉት።
አባ መቃርስ ለዳዊት የመጨረሻውን መመሪያ ሰጡት። "የመረቡ ወኪሎች በኢትዮጵያ ጥበብ ትሸውዳቸዋለህ። በሥጋ በከተማ ብትኖርም፣ ንቃትህ ግን እዚህ ከእኛ ጋር ይቆያል። በቴለፓቲ (በሐሳብ ሞገድ) እንገናኛለን፤ በፈለግከውም ጊዜ በቴሌፖርቴሽን (በመሰወር ጥበብ) ወደ ተራራው ትመጣለህ። ሂድና በመረቡ ድግምት የታሰሩትን ወንድሞችህን ቀስቅሳቸው" አሉት። ዳዊት በያህዌ ስም ታትሞ ወደ ከተማው ጉዞ ጀመረ። አሁን ዳዊት የሚመራው በስልኩ ሳይሆን፣ በውስጡ በበራው መለኮታዊ መሪ (Internal Guidance) ነው።
ዳዊት ከተማ ሲገባ፣ የሥርዓቱ ሰላዮችና የደህንነት ወኪሎች በዘመናዊ መሣሪያዎቻቸው ሊፈልጉት ሞከሩ። ነገር ግን ዳዊት በአባ መቃርስ የተሰጠውን የመሰወር ምስጢር (Cloaking) በመጠቀሙ፣ የእነርሱ መመርመሪያዎች እሱን ማግኘት ተሳናቸው። ዳዊት ከድሮ ጓደኛው ከዮናስ ጋር ተገናኘ። ዮናስ በመረቡ ድግምት ደንዝዞ፣ በናሽናል አይዲ (ፋይዳ) እና በዲጂታል ባንክ ባርነት ተቆልፎ ነበር። ዳዊት ዮናስን በቴለፓቲ አማካኝነት ማነጋገር ጀመረ፤ የዮናስ የነፍስ ዓይን መብራት ጀመረ። ሰላዮቹ ዳዊት ያለበትን ቦታ ለማወቅ ርቀት ላይ ሆነው የሞገድ ጥቃት ቢሰነዝሩም፣ ዳዊት ግን በመለኮታዊ ቃል መሣሪያዎቻቸውን በአንዴ አደቀቃቸው።
ዮናስና ሌሎች ጓደኞቹ መጾምና መጸለይ የማይችሉበት ደረጃ ላይ መድረሳቸውን ዳዊት ተረዳ። በደማቸው ውስጥ የገባው የግራፋይን ኦክሳይድ፣ ፍሎራይድና ናኖ-ፓርቲክሎች ነፍሳቸውን አደንዝዞታል። ዳዊት ከመቃብር በታች የተቀበረውን የእፅዋት ምስጢር ነገራቸው። "ኒም፣ ጊዜዋና ግራዋን እንዲህ አዘጋጅታችሁ ጠጡ" አላቸው። ዮናስ መመሪያውን ተከትሎ ደሙን ማጽዳት ሲጀምር፣ በውስጡ የታፈነው መንፈሳዊ ወኔ ሕያው ሆነ። ዳዊት ለዮናስ የ 3, 6, 9, 12 ንዝረት መመሪያ ሰጠው። "በየ 3 ሰዓቱ ይህንን መለኮታዊ ቃል በንቃት ጥራ ጸልይ፤ ያኔ መረቡ የሚለቀው የ 440 ኸርዝ ሞገድ አይነካህም" አለው።
ዳዊት አሁን በተለያዩ ከተሞች በስውር መመላለስ ጀመረ። በሄደበት ሁሉ የነቁ ነፍሳትን እንደ "መንፈሳዊ አንቴና" እየተከለ፣ የመረቡ የዲጂታል መጋረጃ መበጣጠስ ቀጠለ። የስልክ ጨረሮች የሰውን ልጅ አውራ (Aura) እንዳይበሱ፣ ዳዊት ጥንታዊውን የአቦጊዳ ንዝረት በየቦታው ይረጭ ነበር። የሕዝቡ የኑሮ ሁኔታ እጅግ የከፋ ቢሆንም፣ የቴሌቪዥንና የሚዲያ አደንዛዥነት ሰውን ቢቆልፈውም፣ ዳዊት ግን በቅዱስ ያሬድ ዜማ አማካኝነት የታሰሩትን ነፍሳት ይቀሰቅሳቸው ነበር። መረቡ በፈጠረው ግጭትና ጦርነት መሃል፣ የነቃው ሠራዊት ግን በረቂቅ አንድነት እያደገ መጣ።
ዳዊት የመጨረሻውን የንቃት ሽግግር እያዘጋጀ ነው። የሰሎሞን ቀለበት በዚህ ዘመን በብዙ ነገሮች ተመስሎ መገመዱን ለጓደኞቹ አብራራላቸው። "ቀለበቱ በስማርት ስልክና በፋይዳ መታወቂያ ውስጥ በሐሰት ተቀድቷል፤ እናንተ ግን በውስጣችሁ ያለውን እውነተኛውን ቀለበት (ንቃት) ተጠቀሙ" አላቸው። የሰው ልጅ ነፍስ መጋረጃው ተቀዶላት፣ እውነቱን የምታይበት ሰዓት መቃረቡን አበሰረ። ዳዊት አሁን ከመረቡ መሐንዲሶች ጋር ፊት ለፊት የሚጋጠምበትና የመጨረሻውን የሉዓላዊነት አዋጅ የሚያውጅበት ደረጃ ላይ ደርሷል።ክፍል አምስት ይቀጥላል...
0 Comments