✍ ሔኖክ ኃይለገብርኤል | አባወራ | ኢትዮጵያ አውታር
ኮሚኒስት ማርከሳውያን፣ ፌሚኒስት ግራምሺያውያን፤ ትውልዱን ከእሴቱ መነጠል ልባልባ እንደሚያደርገው በዚያም ገፊ፣ ደፊ ሳይኖረው ራሱን በራሱ፣ ተቋማቱን በእጁ እንደሚያጠፋ ያውቃሉ! ይህም በግልጥ በአደባባይ በእኛ ዘንድ እየኾነ ነው!
ከፍተኛ ገንዘብ ለፖለቲከኞች በመለገስ፣ የፖለቲካ ተጽዕኖ በመፍጠር እና በ”ግበረሰናይ” ስም የተሰበሰቡ “ግብር የማይከፍሉ ሱቆችን” ተቋማትን በመደጎም በሀገራትና በማኅበረሰቦቻቸውም ላይ ከፍተኛ የእውነት፣ የእምነት፣ የእሴትም ቀውስ በማስከተል ይታወቃል።
🚨 ማ?
🚨 IPPF(PPFA)
🚨🚨🚨 International Planned Parenthood Federation
IPPF በሰሜን አሜሪካ የሚገኝ ውርጃን በተለይ አስቀድመው አባት አልባ ባደረጉት የጥቁሩ ማኅበረሰብ ትውልድ ዘንድ በማስፋፋት የሚታወቅ ነው።
በእርሱ ትይዩ በእንግሊዝ ያለውና በዓላማም ኾነ በተልዕኮው ከእርሱ የማይለየው ኢትዮጵያን ጨምሮ በምስራቅ አፍሪካ የተስፋፋው ደግሞ የቀድሞው የሕጻናት አራጁ፣ ጽንስ አስወራጁ ሜሪ ስቶፕስ የአሁኑ MSI ነው።
ሁለቱም በዋናነት የተሰማሩት ሴቶች በእኩልነት፣ መብትና ነፃነት ሰበብ ተፈጥሮአዊ እሴታቸውን እንዲጠሉ ፣ በዚያም ከሰማዩም ኾነ ከምድራዊው አባታቸው እንዲለዩ ማድረግ ነው።
ለምሳሌ ከPPFA መፈክሮች መካከል፦ ጾታዊ ሚና፣ ጾታም ኾነ የሴት ልጅ ድንግልና ማኅበረሰብ ሠራሽ፣ አባወራው አመጣሽ ነው፤ ሲል ይኮንናል!
ይህ ዘመቻ መጀመሪያ ያደረገው ጥቁር አባቶችን ከቤት በማስወጣት ማኅበረሰቡን “አባት-አልባ” ማድረግ ነበር። አባት የሌለው ቤት ደግሞ ለጥቃትና ለባዕድ ተጽዕኖ የተጋለጠ ነው።
በዚህም ሴቶች “በመብትና በነፃነት” ስም ተፈጥሮአዊ የእናትነት ጸጋቸውን እንዲጠሉ፣ ጽንሳቸውን እንዲያስወርዱና ራሳቸውን እንዲያመክኑ ተደረገ።
ውጤቱም ዛሬ በጥቁሩ ማኅበረሰብ ዘንድ የታየው ቅጥአንባሩ የጠፋ ማኅበረሰቦ፣ የቤተሰብ መፍረስና የማንነት መጥፋት ነው። IPPF አሜሪካውያንን ልብ-አልባ አድርጎ ራሳቸውን እንዲያጠፉ ካደረገ በኋላ፣ ዛሬ ያንኑ መርዝ እና ገንዘብም ይዞ ከአቻው MSI ጋር በእኛ ዘንድም እያስፋፋው ይገኛል።
ይህን በመሰለውን ትውልድን የሚያጠፋ ተቋም ወደ ሀገር ውስጥ የሚያስገቡት ደግሞ ዳጎስ ባለው ገንዘቡ፣ በማርከሳዊ ርዕዮተ-ዓለሙ እና በሌሎችም የመጣበት መንገዱ የተማረኩቱ ናቸው።
በአባወራ ንቅናቄያችን ጽድቁን ከመፈጸም በፊት በራስ ላይ መሠልጠንን ግድ የምንለው ለዚህ ነው። አንድ ሰው በራሱ ላይ መሠልጠኑን ባዘገየ፣ በናቀና በተወ ጊዜ በአድርባይነት ማደሩ፣ በባንዳነት እናቱን(ወላጁን፣ ሀገሩን ቤተክርስትያኑን) ለጠላት ማስማማቱ የማይቀር ነው።
IPPF እና MSI በጾታ እኩልነት ሰበብ እሴቶቻችንን ኮንነው ሲያበቁ ትውልዱ ልብ አልባ ይኾናል። በዚያም ልብ አልባው ትውልድ ራሱን ጠልቶ፣ በራሱ ላይ አምጾ፣ ራሱን የሚያጠፋ ይኾናል።
በእርግጥ ይህ ጽሑፍ በእነዚህ ተቋማት ስር ተጠልለው ቀለብ ለሚሠፈርላቸው ወይም ደመወዝ ለሚቆረጥላቸው፣ የቤትና የመኪና ሌሎችም ጥቅማጥቅም ለሚሰጣቸው፣ በዚያም ልጆቻቸውን ውድ ትምህርት ቤቶች ለሚያስተምሩቱ፣ ማስትሬትና ዶክትሬት ሠርተው ለተቀጠሩቱ ይከብዳል።
ይኹን እንጂ ተልዕኮው ትውልድን በማጥፋት በሚጠናቀቀው ተቋም ውስጥ እየሠሩ፣ ከእርሱም ጋር አብረው ትውልድ እያጠፉ መብላት ሰውነት የተበየነበት ልቡ መጥፋት ምልክት ነው።
ሴቶቻችንን በራሳቸው በማንነታቸው ላይ አሳምጸው ሚስት እናት መኾንን ጠልተው መክነው እንዲቀሩ፤ ወንዶቻችንን ደግሞ ወንድነት አባወራነታቸውን አስጠልተው እንከፍ ምስኪንና ጃንደርባ አልጫም አድርገው ሲያበቁ ትውልድ ይጠፋል ማኅበረሰብ ይመክናል።
ይኸው ትውልድ የሚጠፋበት ማኅበረሰብ የሚመክንበት መንገድ እየተዘረጋ፣ እርስ በእርሱም እየተሳለጠ፣ ልጆቻችንም እየቦረቁበት ነው።
አንድ ቀን ድምጻቸው እስኪጠፋ፣ ቤታቸው ኦና እስኪኾን፣ ተተኪም አጥተው እስኪባዝኑ፣ መንደሮቻቸውም ሰው አልባ እስኪኾ፣ እኛንም “ይህን ሲያውቁ እንዴት አልከላከሉንም” እስኪሉን ድረስ።
ትውልድ እያጣን ነው!
🚨 ቤተሰብ እየፈረሰ ነው!
🚨 ልጆቻችን እየተበተኑ ነው!
🚨 ጋብቻ ትዳራችን መጠቋቆሚያ እየኾነ ነው!
🚨 ትዳርን ታናናሾቻችን እየፈሩት እየጠሉትም ነው!
🚨 ምን ቢማር ዶክተርና ኢንጂነር፣ ሊቅና ሊቀ ሊቃውንት ቢባል አልጫና አስመሳይ አድርባይ ሆዳደርም ትውልድ እያፈራን ነው!
🚨 የጠላቶቻችን መሳቂያና መሳለቂያም እየኾንን ነው!
🚨 ማኅበረሰባችንም እየመከነ ነው!
🚨 ሆዳደር ምሁራን ደግሞ በቁማችን በልጆቻችን እየነገዱብን ነው!
ምን እየሠራችሁ ነው?
0 Comments