| የኒዮርክ ከተማ ዋና አቃቢ ሕግ |
✍ ሔኖክ ኃይለገብርኤል | አባወራ | ኢትዮጵያ አውታር
ምዕራባውያን ከሚያድጠው አፋፍ ላይ በዕውቀታቸው ታጅረው ቆሙ፤ እርሱ እንደሚያራምዳቸው ታበዩ፤ ነገር ግን አንድ እግራቸው ከተነሳ በኋላ መቆም አልኾነላቸውም፤ ከድጡ ወደ ማጡ ወደቁ! ዛሬ እሴቶቻቸው ሲፈራርሱ፣ ቤተሰባቸው ሲበተንና ትውልዳቸው መዳረሻ ሲያጣ እያየን ነው! ልብ ያለው ያስተውል!
ለጥፋት ኃይሎች በተቀጠሩለት ምንዳ፣ በሆዳደርነት ስሜት ተገዝተው የሀገርን እሴት የመበረዝ፣ የመደለዝና የመሰረዝ ሸፍጥ የሚፈጽሙ “ምሁራን” እና “አገልጋዮች” ተበራክተዋል። እነዚህ ግለሰቦች ለጥቂት ዲናር ሲሉ፦
ውጤቱም ነገ የሚመጣው “ልብ-አልባ” ትውልድ ነው። ልብ የሌለው ትውልድ ደግሞ ለባርነት የተመቸ፣ በክፋት ላይ የማይጨክን፣ ጽድቁን መፈጸምም የሚሳነው ማንነቱን የጠላ ራሱንም ለጠላት አሳልፎ የሚሰጥ አልጫ ነው።
የቤተሰቡ፣ የማኅበረሰቡ፣ የሀገሩ መሠረትና ምሰሶ የኾነውን “አባወራ” ከአስኳላ እስከ መንፈሳዊ ሊቃውንቱ ድረስ “በዝባዥ፣ ጨቋኝና በዳይ ነው” ብለው ዘምተውበታል።
🚨 አሳፋሪ እኮ ነው!
🚨🚨 እጅግ አሳፋሪ እኮ ነው!
🚨🚨🚨 እጅግ በጣም አሳፋሪ እኮ ነው!
በተለያየ መንገድ በትውልዱ መካከል ጥላቻና ጥርጣሬ የዘሩት ሁሉ ለትውልዱ መጥፋትና ለማኅበረሰቡ መምከን በቀጥታ ተጠያቂ ናቸው።
🌟 አባትን ከልጁ፣ ባልን ከሚስቱ በማጣላት የቤተሰብን አንድነት መናድ አንዱ ሲኾን፤ የአምልኮ መልክ ያላቸው አስመሳዮች ሁሉ ግን ከጠላታቸው ጋር የሚፈልጉት ዋነኛ ዓላማ ትውልዱ አባት ጠል ኾኖ አባትነትን በተለይ አባቱን ይበልጡንም የሰማዩን እንዲጠላ እንዲለይ ነው!
አባትነትን እንደ የአንባገነት አምሳያ በማድረግ፣ እናትነትን ደግሞ ከባርነት በማመሳሰል፣ ማኅበረሰቡን ያለ መሪና ያለ ጠባቂ ለማስቀረት በዚያም የጠላት ሲሳይ እንዲኾኑ ይተጋሉ።
በእርዳታና በምርምር ስም ለባዕድ ጌቶቻችሁ የምትላላኩ ሆዳደሮች ሆይ፤ የታሪክ ተጠያቂነት ክንድ ያርፍባችኋል። ትውልድን የማምከን ተግባራችሁ በዝምታ አይታለፍም።
የሚያድጠውን መንገድ አይጀምሩም፣ አይቆሙበትምም! ጠላት በዕውቀትና በገንዘብ ተኩሎ፣ ተሞሽሮ፣ ተሽሞንሙኖ ቢመጣብህም፣ በአባቶችህ እምነት፣ እውነት፣ እሴት ዐለት-መሠረቱ ላይ ጽና!
💪 ወንድምዓለም ቤተሰብህን፣ ማኅበረሰብህን፣ ሀገርህን ከእንዲህ ያሉ አስመሳይ፣ አድርባይ፣ ሸቃላ “ሊቃውንት” ጠብቅ!
💪 አባትነትህ ትውልድን ወደ ጽድቁ፣ አንተ በምትሄድበት መንገዱ አርአያ ኾነህ የምትመራበት የምትጠብቅበትም የፈጣሪ ጸጋ እንጂ የጭቆና መሣሪያ እንዳልኾነ በተግባር ተገልጠህበት ግለጠው!
💪 እሴቶችህን አትልቀቅ፤ ቀስ በቀስ የሚመዘዙ እሴቶችህን መልሰህ አጽና። ልብ ያለው ትውልድ የሚታነጸው በቤትህ ውስጥ ባለው ጠንካራ አባወራዊ ሥርዓት፦ እሴቱ፣ እምነቱ እውነቱም ነው።
ባፍጢም የተደፋችሁ ሆዳደሮች ጉዳይ ይቆየን! 💪
0 Comments