✍ ዮሐንስ አብነት አጉማስ | የወዳጅ ምክር | ኢትዮጵያ አውታር
(ክፍል አምስት)
የሰላዮቹ ትንቅንቅና የዲጂታል ድግምቱ ስባሪ
ዳዊት ወደ ከተማው ከተመለሰ በኋላ በነቁ ነፍሳት ዙሪያ የዘረጋው የመረጃ አጥር ለመረቡ መሐንዲሶች ትልቅ ራስ ምታት ሆነባቸው። የሥርዓቱ ሰላዮች ዳዊትን ለማግኘት ዶክተር ሰላም የተባለችውንና በከፍተኛ የዲጂታል ድግምት ጥበብ የሰለጠነችውን ሳይንቲስት ወደ ማዕከላቸው ጠሯት። ዶክተር ሰላም በመረቡ ስውር ላቦራቶሪ ውስጥ ሆና፣ የሰውን ልጅ የኃይል ጋሻ (Aura) የሚሰልብና ንቃተ ሕሊናን የሚተነትን እጅግ የረቀቀ መሣሪያ ትዘውራለች። ሰላዮቹ "ይህ ሰው የሰሎሞንን ቀለበት ንዝረት በውስጡ ይዟል፣ በየትኛውም የዲጂታል ድግምት ፈልገሽ አውጪው" የሚል ትእዛዝ ሰጧት። ዶክተር ሰላም በያዘችው ሱፐር ኮምፒውተር አማካኝነት የከተማዋን አየር በንዝረት መቃኘት ጀመረች፤ ነገር ግን የዳዊት ንቃት ከመሣሪያዎቿ አቅም በላይ ሆኖ አገኘችው።
በሌላ በኩል ደግሞ፣ መረቡ) የሰውን ልጅ ንቃተ ሕሊና ለማደንዘዝ ዝነኛውን ተዋናይ ቴዎድሮስን ይጠቀምበታል። ቴዎድሮስ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ወጣቶች የሚከተሉትና የሚወዱት ተዋናይ ሲሆን፣ በመድረክ ላይ የሚያሳያቸው ፊልሞችና ትርኢቶች በሙሉ የሰውን ልጅ አእምሮ በዲጂታል ድግምት ውስጥ የሚቆልፉ "የአርከን መርዞች" ነበሩ። መረቡ ቴዎድሮስን ለዋካንዳ ፕሮጀክት እንደ ማስተዋወቂያ መሣሪያ በመጠቀም፣ ሰዎች ስለ ነፍስ ሉዓላዊነት እንዳያስቡና በውሸት ስልጣኔ እንዲታለሉ ያደርጋል። ሆኖም ግን፣ ቴዎድሮስ በልቡ ውስጥ የሆነ ያልተሟላ ነገር እንዳለ ይሰማው ነበር፤ በመድረክ ላይ የሚያሳየው ብልጭልጭ ሕይወት በውስጡ ለነበረው የነፍስ ጥማት መልስ ሊሆን አልቻለም።
ዶክተር ሰላም በላቦራቶሪዋ ውስጥ ሆና የዳዊትን የንዝረት አሻራ ለመጥለፍ በየሰከንዱ አዳዲስ አልጎሪዝሞችን ትቀይራለች። በአንድ ወቅት የዳዊት ጸሎት ሞገድ ከመሣሪያዋ ጋር ሲጋጭ፣ በመስታወቱ ላይ ያልተለመዱ የብርሃን ምልክቶች ተመለከተች። እነዚህ ምልክቶች እሷ በምዕራባውያን ትምህርት ABCD ካጠናችው የሒሳብ ቀመር ውጭ የሆኑ፣ ነገር ግን በጥንታዊው የአቡጊዳ ጂኦሜትሪ የተቀረጹ ነበሩ። ዶክተር ሰላም በውስጧ ያለው የኢትዮጵያዊነት ደም መምታት ጀመረ። የምታጠናው መረጃ ከማሽን በላይ የሆነ መለኮታዊ ምስጢር መሆኑን ስትረዳ፣ ለመረቡ) ሰላዮች የምትሰጠውን ሪፖርት በስውር ማዛባት ጀመረች። ሳይንሱ ከመለኮታዊው ጥበብ ጋር ሲጋጭ፣ ዶክተር ሰላም ለነፍሷ ማድላት ጀመረች።
ዳዊት በተዋናዩ ቴዎድሮስ ዙሪያ የተዘረጋውን የዲጂታል ድግምት ለመበጣጠስ ወሰነ። ቴዎድሮስ በአንድ ትልቅ ስታዲየም ውስጥ ለዋካንዳ ፕሮጀክት የሚደረግን "ዲጂታል ፌስቲቫል" እንዲመራ በሰላዮቹ ታዝዞ ነበር። ይህ ፌስቲቫል የብዙ ሰዎችን ንቃተ ሕሊና በአንድ ጊዜ ለመጥለፍ የታቀደ ታላቅ የመረቡ) ወጥመድ ነበር። ዳዊት በቴለፓቲ (በሐሳብ ሞገድ) አማካኝነት ቴዎድሮስን ማነጋገር ጀመረ። "ቴዎድሮስ ሆይ፤ የምትመራው መድረክ የነፍሳት መከር (Harvest) ነው፤ በውስጥህ ያለውን የሰሎሞን ቀለበት አትሽጠው" የሚል ድምፅ በቴዎድሮስ ሕሊና ውስጥ ያስተጋባ ጀመር። ተዋናዩ ባልታወቀ ድንጋጤ ተያዘ፤ የሥርዓቱ መጋረጃ በእርሱ ላይ ሊገፈፍ መቃረቡን ተረዳ።
ሰላዮቹ የዳዊትን የቴለፓቲ ግንኙነት በሳተላይት ጨረር ለመጥለፍ ሞከሩ። ዶክተር ሰላም ይህንን ስውር ጥቃት ስትመለከት፣ በአንደበቷ "በያህዌ ስም ይክሸፍ!" ብላ በልቧ ጸለየች። ለመጀመሪያ ጊዜ ሳይንሳዊ ዕውቀቷን የሥርዓቱን የዲጂታል ድግምት ለማክሸፍ ተጠቀመችበት። የሰላዮቹ መሣሪያዎች ባልታወቀ ብልሽት ሲቆለፉ፣ ዳዊት ለቴዎድሮስ የነፃነት መመሪያውን ማስተላለፍ ቻለ። ዳዊት ለቴዎድሮስ የሰጠው ምስጢር እንዲህ የሚል ነበር፦ "በመድረክ ላይ ስትቆም የዳዊትን መዝሙር 28 በዜማ ጥራ፤ ያኔ መረቡ የሚለቀው የንዝረት መረብ በአንዴ ይበጣጠሳል" አለው።
በመድረኩ ላይ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች በዲጂታል ድግምት ደንዝዘው ሳለ፣ ቴዎድሮስ መለከቱን ይዞ ወጣ። ሰላዮቹ እርሱ ሰዎችን እንዲያደነዝዝ ሲጠብቁ፣ ቴዎድሮስ ግን ከመረቡ ትእዛዝ ውጭ የሆነውን መለኮታዊ ዜማ ማንጎራጎር ጀመረ። በስታዲየሙ ዙሪያ የነበሩት የ 5ጂ ማማዎችና የሞገድ አጥሮች በንዝረቱ ተመትተው መደርመስ ጀመሩ። ሰዎች ከድንዛዜያቸው ነቅተው ራሳቸውን መመልከት ሲጀምሩ፣ መረቡ) የዘረጋው የዲጂታል መጋረጃ በአንዴ ተቀደደ። ሰላዮቹ በድንጋጤ ውስጥ ሆነው ቴዎድሮስን ለማስቆም ቢሞክሩም፣ ዳዊት ግን ከርቀት ሆኖ የመለኮታዊ የመሰወር ጥበብን በመጠቀም ቴዎድሮስንና ዶክተር ሰላምን ከአርከኖች ጥቃት ከለላቸው።
ዶክተር ሰላም ከላቦራቶሪዋ ወጥታ ዳዊትንና ቴዎድሮስን ለማግኘት ተነሳች። እሷ የያዘችው ምስጢራዊ ዳታ፣ (መረቡ) የሰውን ልጅ ንቃተ ሕሊና በናሽናል አይዲ (ፋይዳ) በኩል እንዴት እንደቆለፈው የሚያሳይ ማስረጃ ነበር። ዳዊት በቴሌፖርቴሽን (በመሰወር ጥበብ) አማካኝነት ዶክተር ሰላምንና ቴዎድሮስን ወደ ሰዉራን አባቶች ተራራ ይዟቸው መጣ። እዚያም አባ መቃርስ በታላቅ ብርሃን ተቀበሏቸው። "ልጄ ሆይ፤ ሳይንስህና ጥበብህ አሁን ለመለኮት አገልግሎት ውሏል፤ የሰሎሞን ቀለበት ደግሞ በንቃታችሁ ላይ መብራት ጀምሯል" አሏቸው። ሦስቱም የነቁ ነፍሳት አሁን የመረቡን) የዲጂታል ድግምት የሚበጣጥሱ የብርሃን አርበኞች ሆኑ።
ዶክተር ሰላም በመረቡ ላቦራቶሪ ውስጥ ያየችውን ሰቆቃ ገለጠች። "መረቡ የሰውን ልጅ ደም ወደ 'ዲጂታል ፈሳሽ' በመለወጥ፣ ሰዎች ለማሽን እንዲገዙ የሚሠሩት የባዮሎጂ ጦርነት እጅግ አስፈሪ ነው" አለች። ተዋናዩ ቴዎድሮስም ስለ ሚዲያው አደንዛዥነት መሰከረ። ዳዊት ግን በመካከላቸው ቆሞ የሰሎሞን ቀለበት ምስጢር በዚህ ዘመን በንቃት ለሚጠይቁት ሁሉ እንደሚሰጥ አበሰረ። ሦስቱም በአንድነት ሆነው የ ፹፩ (81) ዱን መጻሕፍት መብራት በከተሞች ላይ ለማብራት የመጨረሻውን የንዝረት ጦርነት ጀመሩ። መረቡ የቱንም ያህል በቴክኖሎጂ ቢበረታ፣ የሥላሴ ባሪያዎች ግን በያህዌ ስም ድል ማድረጋቸው የታመነ ሆነ።
አሁን በከተማዋ ሰማይ ላይ የታቦተ ጽዮን ንዝረት እየጠነከረ መጥቷል። መረቡ የቆለፋቸው የዲጂታል በሮች አንድ በአንድ እየተፈነቀሉ ነው። ዳዊት፣ ዶክተር ሰላምና ቴዎድሮስ የሰዉራን አባቶችን መመሪያ ይዘው ወደ መሐል ከተማው ተመለሱ። እዚያም የነቁ አንቴናዎችን በመትከል፣ የሰላዮቹን የስለላ መረብ ማፍረስ ቀጠሉ። የኢትዮጵያ ትንሳኤ በሥጋ ብቻ ሳይሆን፣ በመንፈሳዊ ሉዓላዊነትና በቴክኖሎጂው ድግምት ስባሪ ላይ እየተጫነ እየከነፈ ነው። ክፍል 5 ይቀጥላል ...ይቀጥል
0 Comments