“ያለ ዕድሜ ጋብቻ”ን ኮንነን “ያለ ዕድሜ መዳራትን” ያጸደቀን ያስተማርን እኛ ጠፊዎች ነን!

✍ ሔኖክ ኃይለገብርኤል | አባወራ | ኢትዮጵያ አውታር  

በሕይወት ክህሎት (SRHR) ትምህርት ልጆች እንዲታቀቡ የሚመከሩት ከጋብቻ(ከትዳር) እንጂ በልቅ ወሲብ ከመዳራት፣ በዚያም ውርጃን(ነፍሰገዳይነትን) ከመለማመድ አይደለም!

በማኅበረሰባችን ላይ የተደቀነው ትልቁ አደጋ የቃላት ጨዋታና የትርጉም ግልበጣ ነው። በ”ሕይወት ክህሎት” (SRHR/CSE) ስም ትውልዱን የሚጋቱት መርዝ፣ ስሙ “ሕይወት” ይባል እንጂ ትርጉሙ ግን “ምክነትና ሞት” ነው።

🚨 “በማኅበረሰቡ መካከል ስር የሰደደ አባታዊ፣ አባወራዊ ጎጂ ልማድ” (Entrenched Patriarchal Norms) ብለን “ያለ ዕድሜ ጋብቻ”ን “የሚያስከስስ ወንጀል ነው” ብለን እንኮንናለን፤ የተባረከውን ትዳር እንደ እስር ቤት ቆጥረን ኮንነን ልጆቻችን በማስተማር ቤተሰብ ከመመስረት እናዘገያቸዋለን።

🚨 እነርሱም የትዳር ውጤት የኾነውን እርግዝና ኮንነው፣ ጠልተውና እንደ በሽታና እርግማን ቆጥረው ሳያረግዝ ሳያምጥ ሳይወልድ እንደሚኖረው ወንድ መኖር ይመኛሉ። ይህም “እኩልነት ነው” ተብለው ተነግሯቸዋልና።

🚨 ልጆቻችን ተምረው፣ ተቀጣሪ ደመወዝተኛ፣ አልያም “የሥራ ፈጣሪ ሕልማቸውን” ሲያባርሩ ቆሞ ቀሮች፣ ትውልድ አልባዎች፣ እንዲኾኑ እንጂ ከብደው፣ ወልደው፣ ስመው፣ አዝለው፣ አሳድገው፣ በሥነ-ሥርዓትና በሥነ-ምግባር አንጸው ጠንካራ ቤተሰብ፣ ማኅበረሰብና ሀገር እንዲገነቡ አይፈለግም!

🚨 “ያለ ዕድሜ መዳራት”ን (በልቅ ወሲብ መማገጥን) ግን፣ “የሕይወት ክህሎት” በሚል ሥልጠና አጽድቀን፣ ኮንዶምና የወሊድ መከላከያ ለልጆቻችን በማደል፣ ውርጃንም “በመስኩ የተመሰከረለት ባለሙያ በቀላሉና በርካሽ” በማቅረብ እንደ ትልቅ ሥልጣኔና መብት እናቀነቅናለን።

🚨 በዚያም የወሊድ መከላከያ ቋሚ “ወዳጅ ጠባቂያቸው” የኾኑ የማንም ሳይኾኑ፣ የትም ከማንም፣ እንዴትም “ያለ ተጠያቂነት” የሚዳሩ፣ ስለ ትውልድ፣ ትውፊት፣ ቤተሰብ፣ ማኅበረሰብ ግድ የማይሰጣቸውን ልጆች እናፈራለን።

በ”ሕይወት ክህሎት” ስም የሚሰጠው የ(SRHR) ትምህርት ልጆች ከምን እንዲታቀቡ ነው የሚመክረው? 🚨 ከልቅ ወሲብ፣

🚨 ከሴጋ(masturbation)

🚨 ከጋብቻ ውጪ እርግዝና፣

🚨 የማንም ሳይኾኑ፣ የትም ከማንም ከመውደቅ፣

🚨 ለመውለድ ከመዘግየት፣

☀️🎯🌟 አይደለም! በጭራሽ!

🌟 ታቀቡ ቢል በተለይ በአንድ ነገር ነው! እርሱም መዳራትን በፈቀዱበት እድሜ ከመጋባት፣ ቤተሰብ ከመመስረት፣ ልጆችን ከመውለድ መታቀብን!

ምክንያቱም እርሱ የጠላትንና ምንደኛ የኾኑትን ሆዳደር “ሊቃውንት” ትውልድን አጥፍቶ ማኅበረሰብን አምክኖ ለባርነትና ሞቱ የመማገዱን ሸፍጥ ያከሽፋልና።

🎯 በዋናነት መዳራት፣

🎯 ለመዳራት የሚያስፈልጋቸውንም “እውቀት” ማግኘት፣

🎯 ሲዳሩ እንዳይታመሙ፣ እንዳያረግዙ፣ በትዳር በእርግዝና እንዳይታሰሩ፣

🎯 ድንገት ቢያረግዙ በመርዝ በጣጥሰው በመቀስ ቆራርጠው ማስወጣት፣

🎯 ከፈለጉት ጋር፣ ነገር ግን የማንም ሳይኾኑ የትም እንዴትም እንዲዳሩ....እነዚህም መብታቸው እንደኾኑ ያስተምራል እንጂ።

ስለኾነም ከጋብቻ (ከትዳር)! እንዲታቀቡ ይነገራቸዋል። ልጆቻችን በተለይም ሴቶቻችን ትዳርን እንደ ጭቆና፣ እንደ እስር ቤት፣ እንደ ኋላ ቀርነት እንዲያዩ ይደረጋሉ። በኮንዶምና የወሊድ መከላከያ የታጠረ ልቅ፣ በውርጃ (በነፍሰገዳይነትም) የተጠናከረ ልቅ ወሲብ ግን እንደ “መብት” እና “ነፃነት” ይሰበካል።

ለዚህም ግብዓት ይኾኑ ዘንድ ያለጊዜያቸው፣ ያለዕድሜያቸው፣ ስለወሲብ እንዲያውቁ እንዲሰሙ፣ እንዲያስቡ፣ እንዲሞክሩና እንዲገቡበትም ይበረታታሉ።

በዚህ ትምህርት ልጆች እርግዝናን “ስህተት” ወይም “ችግር” አልያም እንደ “በሽታ” እንዲቆጥሩና እንዲጠሉት እንጂ የሰማይ አባታቸው የሰጣቸው ጸጋ እንደኾነ እንዲያዩት አይደረግም።

ውርጃን ደግሞ እንደ “መፍትሄ” ወይም “ሕክምናው” አድርገው እንዲቀበሉ ይህም “ሰብዓዊ መብታቸው” እንደኾነ ይማራሉ።

🚨 ይህ ስሙ “የሕይወት ክህሎት” ይባል እንጂ ጥፋት ሞታቸውን የሚለማመዱበት “ራስን፣ ትውልድን በማጥፋት ማኅበረሰብ የሚመክንበት ልምምድ” ነው!

ምዕራባውያን ይህንን የተመረዘ ዘር በልጆቻቸው ልብ ላይ ዘርተው ዛሬ መርዛማ ፍሬ አፍርተዋል። ሰሜን አሜሪካ፣ እንግሊዝ፣ ምዕራብ አውሮፓ ኹነኛ ማስረጃ ናቸው።

በ”ጾታ እኩልነት” እና “መብት” በሚሉ ማራኪ ቃላት ተሸፍኖ፣ SRHRን በመተግበር በትውልዱ መካከል መተማመንን ማጥፋት ብቻ አይደለም፤ ከፍተኛ የሕጻናት ደም የሚፈስባቸው፣ ለአጋንንት የሚሰዉባቸው፣ የነፍሳቱን ፈጣሪ አባታችን የሚያዝንባቸው ሀገራት ኾነዋል።

🚨🚨🚨 በኢትዮጵያም ይኸው እየተደገመ ነው! በቀን በቀላል ግምት ከ3,000 በላይ የአባታችን ልጆች የኾኑ ነፍሳት “በመስኩ በተካኑ ባለሙያ ነፍሰገዳዮች”፣ ከቀዶ ጥገናው የመስዋዕት ጠረጴዛ ላይ “በሥነ-ተዋልዶ ጤና አገልግሎት ስም” ለአጋንንት እንደሚሰዉ ስንቶቻችሁ ታውቃላችሁ?

ምዕራባውያን ሴቶቻቸው ወንዶቻቸውን እንደ ጠላት፣ ትዳርን እንደ ጭቆና፣ መውለድን እንደ ኋላ ቀርነት እንዲያዩ ተደርገው ቆመው፣ ደርቀው፣ ትውልድ አልባ ኾነው እንዲቀሩ ተደርገዋል።

በፕላንድ ፓረንትሁድ አስተባባሪነት በተሰጠው የሁሉን አቀፍ የሥርዓተ ጾታ ትምህርት የልጃገረዶች እርግዝና፣ ውርጃና ፍቺም ከትውልዱ ነቅሎ መጣል እስካይቻል ድረስ እጅግ ተንሰራፍቷል።

እነዚህን ፕሮግራሞች “የዓለም የወሲብ ቱሪዝም” መዳረሻ በኾነችው ታይላንድ እንዲሁም በርካቶች የHIV-AIDS ሰለባ በኾኑባት ደቡብ አፍሪካ በገንዘብ ኃይል ያስገቡ NGOዎች፣ ትውልዱን ከማዳን ይልቅ ለበሽታና ለሥነ-ልቦና ቀውስ አሳልፈው ሰጥተውታል።

ልጆች ስለ ወሲብ ቴክኒክ ንቁ፣ አዋቂ፣ ሞካሪ፣ ተለማማጅ፣ ተግባሪ፣ ተዳሪ ኾነው ስለ ሥነ-ምግባር፣ ኃላፊነት፣ ሀገር ግንባታ ግን ባዶ እንዲኾኑ ተደርገዋል።

የእኛዎቹ ባፍጢም የተደፉ፣ በመቶ ሺዎች የሚከፈላቸው፣ ሆዳደር ሊቃውንት በከፈቷቸው ግብር በማይከፍሉባቸው ገቢ አስገኝ ”ግብረሰናይ” ሱቆቻቸው የሚሠሩትን ሥራ፣ ከሸራተን ዐዲስ እስከ ዐዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን በአደባባይ የሚከተሉትን የምዕራባውያን የጥፋት ፈለግ ይነግሩናል።

ሁሉም ግልጥ ነው! አንዳችም የተደበቀ የደበቁንም የለም!

እኛ ግን የልጆቻችን፣ የትውልዳችንም ነገር አይገደንም! አንድም ቢገደንም እነርሱንም ኾነ አምላካችንን “እንወዳቸዋለን” ከምንልበት ከአስመሳይነታችን የተነሳ ነውና፤

አንድም ጽድቅ ከምንፈጽምበት ልባምነት፣ ጭካኔ፣ ወኔ ጥብዓቱ ተሰልበን፤ ልባልባ፣ ጃንደርባ፣ አልጫ ኾነን በባርነት የምንኖር እንከፎች ነንና፤

አንድም ዕድሉን ስላጣን እንጂ እንደእነዚህ “ምሁራን” ቢከፈለን እኛም የምንነግድባቸው፣ የተሻለ ዋጋ ላቀረበው ማንም “በመብትና ነፃነት” ስም የምንሸጣቸው ነንና፤

“ዝም” እንላለን!

የቤተሰቡን፣ የልጆቹን፣ በተለይም ደግሞ የሴቶቹን ጠባቂ አባወራውን፤ “በዝባዥ፣ ጨቋኝ፣ በዳይ” ብሎ ከልጆቹ እንዲርቅ፣ እንዲጠላና እንዲኮነን የተደረገው ይህንኑ ትውልድን የማጥፋት ማኅበረሰብን የማምከን ሥራቸውን ያለከልካይ ለመፈጸም ነው።

በዚህ በአባወራው ንቅናቄ ግን፦ ወንዱን ወደ ልቡ አባወራውን ወደ ክብሩ በመመለስ፤ ልጆቻችንን በተለይም ሴቶቻችንን፦ እናቶቻችንን፣ እህቶቻችንን፣ ሚስቶቻችንን፣ ልጆቻችንን፤ ከአስመሳይነት በራቀ፣ ከሰማዩ አባታችን በተሰጠ የጥበቃ ሚና እንጠብቃቸዋለን!

ማ? እኛ የአባቶቻችን ልጆች አባወራዎች!💪

Post a Comment

0 Comments