የቅርብ ዘመን ትንቢቶች እና ፍጻሜያቸው

 


በሃገራችንም ብዙ ቅዱሳን እና ጉሁሳን እየመጣ ስላለው ነገር ብዙ ትንቢት የተናገሩ ቢሆንም  የአንዳቸውም ተመዝግቦ አይገኝም በአንዳንድ አባቶች እና ምእመናን ዘንድ የሚገኙ ትንቢቶች ቢኖሩም በቤተክህነቱ እውቅና ተሰጥቶአቸው የተቀመጡ አይደሉም ፡፡

በአለም ስለሚደረገው የሚሳኤል እና የኒዩክሌር ጦርነት ትንቢት ከተናገሩ አባቶች አንዱ አባ ወልደትንሳኤ ናቸው ፡፡ አባ ወልደትንሳኤ አባ ዲዮስቆሮስ በሚል የጵጵስና ስማቸው የሚታወቁ ሲሆን 3ኛው የአለም ጦርነትን በ80ዎቹ አከባቢ በግጥም እና ምሳሌ አድርገው ተንብየዋል፡፡

የሃገራችን ባህታዊያን እና ቅዱሳን ብዙ ጊዜ ትንቢት የሚናገሩት ስለ ሃገራዊ ጉዳዮች ነው፡፡
ስለ አለም አቀፉ ሁኔታ ብዙ ጊዜ ትንቢት የሚናገሩት የምስራቃውያን አባቶች ነው ፣

በምስራቃውያን አበው ከተነገሩት ዝነኛ ትንቢቶች መሃል ሦስቱን ያህል እንይ

"የፍልስጤም ህንጻዎች ወደ ሜዳነት ከተቀየሩ በኋላ አንድ ቀን ቁጭ ብላችሁ ቡናችሁን እየጠጣችሁ ሳለ እስራኤል የኢራንን የኑዩክሌር ማምረቻ መታች የሚል ዜና ትሰማላችሁ ከዛን ጊዜ በኋላ የአለም ሁኔታ በእጅጉ ይቀየራል" የገዳመ አቶሱ(mount athos)  አባ ገብርኤል

"ታላቁ ክስተት የሚጀመረው እስራኤሎች የፋርሶችን ኒዩክሌር ሲያወደሙ እና ጦርነት ሲያውጁ ነው " አባ ቴዎዶር 

" ኤርዶጋን ይወድቃል የቱርክም ታሪክ ሌላ ይሆናል  "
አባ ፓዮሲስ 


ከላይ ያሉት ትንቢቶች በ90ዎቹ እና 80ዎቹ አከባቢ የተነገሩ ትላልቆቹ ትንቢቶች ናቸው መናኞቹ የተናገሩት አብዛኛው ትንቢት በገዳማት እና የምስራቃውያን አባቶች ዘንድ ነው ያለው

እነዚህ መናኞች በገዳመ አቶስ እና መሰል ታላላቅ ገዳማት ላይ በተጋድሎ የነበሩ እና አንዳንዶቹም በሲኖዶስ ቅድስና የተሰጣቸው ናቸው ፡፡

የአብዛኞቹ ትንቢቶች  ሃሳብ ኢራን ላይ ጥቃት እንድሚከፈት ይህም አዲስ  ክስተትን እንድሚያመጣ የሚጠቁም ሲሆን ይህንም ተከትሎ  የኦርቶዶክሳዊያንን ደም  በመቶ ለሚቆጠሩ አመታት ያፈሰሰችው ቱርክ መሪዋ ኤርዶጋን ከስልጣን እንደሚወገድ እና የቱርክ ተጽእኖ ፈጣሪነት እንደሚያሽቆለቁል ይባስ ብሎም ከአመታት በኋላ ሩሲያ እንደ ምታጠፋት የሚያሳዩ ትንቢቶች ናቸው፡፡

ስለእነዚህ ትንቢቶች ተጠይቀው  ማብራሪያ ከሰጡት አባቶች አንዱ የግሪኩ ጳጳስ ሜትሮፖሊታን አባ ኒዮፋይቶስ ናቸው፡፡ 


Post a Comment

0 Comments