የጾታ እኩልነት፣ መብትና ነፃነት የመጨረሻ ግቡ “የሴቶች እኩልነት” አይደለም! ይልቁንስ “ጾታ የሚባል ነገር የለም” ብሎ ተፈጥሮን ፈጣሪንም መካድ እንጂ!
ዓለም አቀፉ ግራ ዘመም ኃይልና UN እያበረታቱት የመጣው ዐዲስ አስተሳሰብ፣ ጾታ በተፈጥሮ የሚገኝ ሳይኾን “ማኅበረሰብ ሠራሽ፣ አባወራው አመጣሽ ነው” በማለት ትውልዱን ይግታል።
ላዩን ሲያዩት ፍትሃዊ የሚመስለው “የጾታ እኩልነት” ጥያቄ፣ ዋና ግቡ ወንድንና ሴትን እኩል ማድረግ ሳይኾን፣ ወንድነትንና ሴትነትን ማጥፋት ነው።
ይህ ትርክት በዋናነት የሚመነጨው ከማርክሳዊው ፍልስፍና ነው። ማርክሳውያንና ለሴታዊ ንቅናቂያቸው ማርክሳዊ መነጽር የደረቡት ፌሚኒስትስ ቤተሰብን እንደ መጀመሪያው “የመደብ ጭቆና” መድረክ አድርገው ይፈርጁታል።
ለእነርሱ የቤተሰቡ ጠባቂና መሪ አባወራው (The Patriarch) ትልቁ ጠላትና አንባገነን ነው። ጾታን “ማኅበረሰብ ሠራሽ” ብለው የፈረጁት፣ አባወራው ሴቷንና ልጆቹን ለመቆጣጠር የፈጠረው “የጭቆና መሣሪያ” ነው ብለው ስለሚያምኑ ነው።
ስለዚህም “እኩልነት” ለማምጣት በመጀመሪያ አባወራውን ማጥፋት፣ ከዚያም ጾታ የሚባለውን የተፈጥሮ መለያ መሰረዝ አለብን ይላሉ።
“የሴቶች እኩልነት እስካልተረጋገጠም ፍትሕ የለም!” የሚሉት ይህ “የጾታ ልዩነት እስካልተሻረና እርሱን ተከትለው የሚመጡት ትምህርቶች፣ ሚናዎችና ባህሎች፣ ፖሊሲዎች ሁሉ እስካልተደመሰሱ ድረስ አናቆምም” ሲሉን ነው።
በዚህም ምክንያት ልጆቻችን ወንድ ወይም ሴት መኾናቸውን በጸጋ ተቀብለው እንዳያድጉ፣ ይልቁንም “የፈለጋችሁትን መኾን ትችላላችሁ” በሚል ግራ መጋባት ውስጥ እንዲወድቁ ይደረጋሉ።
ወንድልጅ ተፈጥሮአዊ የኾነውን የመሪነት፣ የጥበቃና የኃላፊነት ሚናውን እንዲተው “በእኩልነት” ስም ስልብ፣ ድልብ፣ ቅልብ፣ ሙክት ወኔቢስ ጃንደርባ እንዲኾን ይቀጠቀጣል።
ሴት ልጅም እናትነትንና ተፈጥሮአዊ ክብሯን እንደ “አባወራ አመጣሽ ጭቆና” እንድታየው ትገፋፋለች። በዚያም ወንድን እንድትጠላና ከእርሱ ጋር አንድነትና ውህደት ኖሯት ቤተሰብ እንዳትመሠርት፤ ሲቀጥልም አባቷን እንድትጠላና ፈጣሪዋንም እንድትክድ የሚሠራ ሸፍጥ ነው።
ይህ ጾታን የማጥፋት ዘመቻ ቤተሰብን ከሥሩ የሚንድና የሰው ልጅን ተፈጥሮአዊ መሠረት የሚነቅል የታሪክ ትልቁ የማንነት ማጥፊያ ዘመቻ ነው።
ጾታ በጠፋበት ማኅበረሰብ ውስጥ ቤተሰብ የሚባል ተቋም ሊኖር አይችልም፤ ቤተሰብ ካልኖረ ደግሞ ትውልድ አይቀጥልም፤ ትውልድ ካልቀጠለ ደግሞ ሀገርና እሴት በታሪክ መዝገብ ላይ ብቻ ቀርተው ይጠፋሉ።
ወንድምዓለም! ዛሬ በልጆችህ ትምህርት ቤት በሥነ-ተዋልዶ ጤና አገልግሎትና መብት (SRHR) የሚሰጠው ትምህርት ግቡ ይህ ነው።
ይህ ዘመቻ አንተን ከአባወራነት፣ ሚስትህን ከእናትነት፣ ልጆችህን ደግሞ ከተፈጥሮአዊ ማንነታቸው ለማፈናቀል የተዘረጋ ማርክሳዊ መረብ ነው። ጾታን ማጥፋት ማለት መለኮታዊውን ሥርዓት መቃወም ነው፤ ተፈጥሮን መካድ ነው።
ቤታችሁን ጠብቁ! ልጆቻችሁ ወንድነታቸውንና ሴትነታቸውን በክብርና በልዕልና እንዲቀበሉት አድርጋችሁ አንጹ፤ አንድም በተሰጣቸው ጸጋ አንጻር ሚናቸውን እየተለማመዱት እንዲያድጉ እናንተ በሚናችሁ ተገኝታችሁ ዐሳዩ።
የዓለም አቀፍ ተቋማት “መብትና ነፃነት” የሚሉት ቃል መጨረሻው ተፈጥሮን ማጥፋትና አባወራነትን መናድ መኾኑን ተረድታችሁ ይህንን ጉዳይ ከአሁኑ በትኩረት ተከታተሉ።
እውነተኛ እኩልነት በተፈጥሮ ሕግ ውስጥ እንጂ፣ ተፈጥሮን በመካድና ጾታን በማጥፋት ውስጥ አይገኝም። ጾታን ለማጥፋት የሚጠቀሙትን ጾታዊ ጥቃትንና፣ የቤት ውስጥ ሚናን በቅርበት ታዘቡ።
ይህ የሰው ልጅ በመብትና በነፃነት ስም በፍጥረቱና በፈጣሪ ላይ አመጽን የሚለማመድበት የጥፋት መንገድ ነው። በምንም ዓይነት የዘመናዊነትና የመንፈሳዊነትም ትንታኔም ሊደገፍ የማይችል ለትውልዱ ጥፋትን ይዞ የመጣ ርዕዮተ-ዓለምም ነው።
ይህንንይህንን የምንቀለብሰው ደግሞ ወደ ነባሩ፣ ባህላዊው፣ ሃይማኖታዊው፣ ተፈጥሮአዊው አባወራዊ ሥርዓት ስንመለስ ነው።
ይኹን እንጂ ሚዲያው፣ የመገናኛ ብዙኃኑ የቀደመውን የሚቃወመውን እና የሚከላከለውን ጠንካራ አባወራ ሳይኾን ከመጣው፣ ከተሰጠው ጋር “ተስማምቶ” ለመኖር የሚፈልገውን፣ እርሱንም በዘመናዊነትና በመንፈሳዊነት አጽድቆ የሚቀበለውን እንከፍ ምስኪኑን፣ አላዛኝ ነፍራቃውን ጃንደርባ ያበረታቱ ዘንድ መመሪያ የተሰጣቸው እስኪመስል ድረስ ተመሳሳይ ትርክትን ሲያስተላልፉ እየተመለከትን ነው።
ጀግናው! ልጆቻችን የመታደጉ የቤት ሥራ እኔንና አንተን ይጠብቃል! ማንም አይሠራልንም!
0 Comments