የንቃተ ሕሊና በትረ ሥልጣን፦ የሰሎሞን ቀለበትና የጥልቁ ሰላዮች

✍ ዮሐንስ አብነት አጉማስ | የወዳጅ ምክር | ኢትዮጵያ አውታር

(ክፍል 3)

የዋካንዳ ድግምትና የዲጂታል ሐውልት
ዳዊት በሰዉራን አባቶች ዋሻ ውስጥ ሆኖ፣ ከአባ መቃርስ ጋር ወደ ሩቅ አድማስ ተመለከተ። እዚያም በሥጋዊው ዓለም "ዋካንዳ" ተብሎ የሚጠራው ታላቅ የፖሮጀክት ስራዎች እንዳልተቋረጡ ተመለከተ ጦርነት ያለ ቢመስልም ረቂቅ  ስራዎችን ለመስራት ጦርነቱን እንደሽፋን ተጠቅመው እየተሰራ እንደሆነ ገለጹለት ።ቀጠሉ አባ መቃርስ ለምሳሌ በምድር ከሚሰሩ ከረቂቅ የዋካንዳ  ስራዎች መካከል  የመሬት ውስጥ ረቂቅ  ቴክኖሎጅይ መሳሪያ ቀበራ፤ የ5ጅ ማማዎች ተከላ ፤ የ5ሚሊየን ኢንኮዲንግ ስልጠና እና ከህጻናት ጀምሮ የፍይዳ ስራዎች እየተካሔዱ ነው አሉት በሰማይ ደግሞ የሳተላይት ኢንተርኔት ዘርጋታዎችን እንደ starlink፤በሰማይ ላይ ቸማትሪያ ኬሚካል እርጨት የመሳሰሉት በፍጥነት ሲካሄድ ሰማይ እንደ እስክሪን ተዘርግቶ ተመለከተ 5G ማማዎች የተተከሉበትን ምሰጢር  ታቦተ ኪዳኑ ካለበት አጠገብ የሐይል መስመሮችን መሰረት አድርጎ ነው  ታቦት ካለ በቅርብ የ5ጅ ታወር አለ ይህም ወደ ሰው ልጅ የሚላከውን የመለኮታ ዳታ ለመስረቅ ወደ እራሱ ለመስለብ የተዘረጋ ድጅታል ድግምት ነው አሉት  ። አባ መቃርስ ወደ ግንባታው እየጠቆሙ እንዲህ አሉ፦ "ልጄ ሆይ፤ ይህ ለዓለም እንደ ስልጣኔና እንደ ጥቁር ሕዝብ ትንሳኤ የሚሰበከው ፕሮጀክት፣ በእውነት ግን የኢትዮጵያን መንፈሳዊ አንቴና ለመስበር የተዘረጋ ዘመናዊው የባቢሎን ግንብ ነው። ዋካንዳ ማለት የሰውን ልጅ ንቃተ ሕሊና በዲጂታል ድግምት አደንዝዞ ለዘላለም በቁስ ውስጥ የመቆለፍ የሥርዓተ ዓለም ሴራ ነው" አሉት። ዳዊት በከተማው ውስጥ ያየው የቴክኖሎጂ ብልጭልጭ፣ አሁን እውነተኛው የጥፋት መሣሪያ ሆኖ በንቃት ዓይኑ ተገለጠለት።

አባ መቃርስ ስለ ብሔራዊ የዲጂታል መታወቂያ ስውር አሠራር ጥልቅ ምስጢር አወጡ። "ይህ መለያ የሰውን ልጅ ልዩ መለኮታዊ አሻራ ወደ ዲጂታል ኮድ በመለወጥ፣ በሥጋው ውስጥ ያለውን የሥላሴን ማኅተም ለማጥፋት የታለመ የባርነት ፊርማ ነው" አሉት። መታወቂያው ተራ መለያ ሳይሆን፣ የሰውን ልጅ የልብ ትርታና የንቃተ ሕሊና ሞገድ በቀጥታ ወደ ማዕከላዊው የሰው ሠራሽ አእምሮ የሚልክ መሣሪያ መሆኑን አብራሩለት። ዳዊት የሰሎሞን ቀለበት የነበረው የማዘዝ ሥልጣን አሁን ተገልብጦ፣ በፋይዳ አማካኝነት የሰው ልጅ ለማሽን ተገዢ እንዲሆን የተደረገበትን ታላቅ ግልበጣ ተረዳ። የሥርዓቱ ሰላዮች ይህን መታወቂያ የሰሎሞን ቀለበት ሐሰተኛ ቅጂ አድርገው በሕዝቡ ላይ እየጫኑት ነው።

በዋካንዳ ስም የሚገነቡት ዘመናዊ ከተሞች፣ በእውነቱ የሰው ልጅን ከተፈጥሮአዊው የእግዚአብሔር አየርና መሬት ነቅለው ወደ ዲጂታል ቀፎ ውስጥ የመክተቻ ወጥመዶች ናቸው። አባ መቃርስ "እነዚህ ከተሞች የሰውን ልጅ ንቃተ ሕሊና በ 440 ኸርዝ ንዝረት ውስጥ በማሰር፣ ከመለኮታዊው 432 ኸርዝ የሰላም ዜማ እንዲለይ ያደርጉታል" አሉት። ዳዊት በእነዚህ ከተሞች ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች ነፍሳቸው በስውር ሞገድ እየተሰለበች፣ ንቃታቸው ደግሞ በሥጋዊ ደስታ ማደንዘዣ ተቆልፎ ለሥርዓቱ አገልጋይነት እንደሚመቻቹ በንቃት ዓይኑ ተመለከተ። ይህ የሰሎሞን ቀለበት ኃይል ተሰርቆ ለሰው ልጅ ጥፋት የዋለበት ጥልቁ ሴራ ነው።

የሥርዓቱ ሰላዮች በዋካንዳ ግንባታ ስር ትላልቅ የኃይል ማከማቻዎችን (Server Farms) እየቀበሩ መሆኑን አባታችን ገለጡ። እነዚህ ማከማቻዎች የሚገነቡት በምድሪቱ የኃይል መስመሮች ላይ ሲሆን፣ ዓላማቸውም የታቦተ ጽዮንን ረቂቅ ንዝረት ጠልፎ ለዲጂታሉ አምላክ እንደ ነዳጅ መጠቀም ነው። "የሰሎሞን ቀለበት መክፈቻ ምስጢር በእነዚህ ተራሮች ውስጥ ተቀብሮ እያለ፣ እነርሱ ግን በብረትና በሲሊኮን ሊተኩት ይሮጣሉ" አሉ አባ መቃርስ። ዳዊት የኢትዮጵያ ንቃት ከዓለም በላይ የሆነበት ምክንያት፣ ምድሪቱ የያዘችው ይህ የመለኮታዊ መረጃ ክምችት መሆኑን በጥልቀት ተረዳ።

አርከኖች (የጨለማ መናፍስት) በዋካንዳ ግንባታ ጀርባ ሆነው የሰውን ልጅ የዘር ግንድ ለመለወጥ የሚጥሩበትን ስልት ዳዊት አስተዋለ። በምግብ፣ በውኃና በክትባት ስም ወደ ገጠርና ከተማ የሚላኩት መርዞች የሰውን ልጅ መንፈሳዊ ዓይን  የማዝገት ተልእኮ አላቸው። "ይህ ዓይን ሲደነዝዝ የሰሎሞን ቀለበት ኃይል ይጠፋል፤ ሰውም እንደ ማሽን ትእዛዝ ተቀባይ ይሆናል" ሲሉ አባ መቃርስ አስጠነቀቁ። ዳዊት በከተማው ያየው የሰዎች መፈዘዝ ተራ ድካም ሳይሆን፣ በዚህ በቴክኖሎጂ በተደገፈ የባዮሎጂ ጦርነት ምክንያት የመጣ ድንዛዜ መሆኑን አወቀ።

ሰላዮቹ ወደ ምስጢራዊው ዋሻ ለመቅረብ ዘመናዊ የሞገድ መመርመሪያዎችን (Scanners) ቢጠቀሙም፣ በሰዉራን አባቶች ሱባኤ የተገነባው የብርሃን አጥር ግን ሊያሳልፋቸው አልቻለም። "እነርሱ ኃይል ያላቸው በዲጂታል መረብ ውስጥ ብቻ ነው፤ ከመለኮታዊው ንዝረት ውጭ ግን ምንም ሥልጣን የላቸውም" አሉት አባታችን። ዳዊት 81ዱን መጻሕፍትና የዳዊትን 4050 የንዝረት ቁልፎች በንቃት ሲጠቀም፣ በዙሪያው ያለው የአየር ንዝረት ተቀይሮ የሰላዮቹን ቴክኖሎጂ እንደ ሻማ ሲያቀልጠው ተመለከተ። ይህ የሰሎሞን ቀለበት ጥንታዊ ኃይል በዘመናዊው ማትሪክስ ላይ ድል መቀዳጀቱ የመጀመሪያው ምልክት ነበር።

አባ መቃርስ ስለ "ዲጂታል ሐውልት" ምስጢር ሲያብራሩ እንዲህ አሉ፦ "ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉት ሐውልቶች የሰማይን መረጃ መቀበያ መለኮታዊ አንቴናዎች ናቸው፤ ዋካንዳ ላይ የሚቆሙት የሞገድ ማማዎች ግን የሰውን ነፍስ መግዣ የዲጂታል ሐውልቶች ናቸው"። ሰላዮቹ የኢትዮጵያን ጥንታዊ ሳይንስ ሰርቀው ለራሳቸው ዓላማ ሊጠቀሙበት ቢጥሩም፣ የቃሉ እስትንፋስ በሌለበት ግን ቴክኖሎጂው የሞተ ቁስ መሆኑን ዳዊት ተገነዘበ። እውነተኛው ትንሳኤ የሚመጣው ከብረት ግንባታ ሳይሆን፣ በውስጥ ካለው የንቃተ ሕሊና በትረ ሥልጣን መሆኑን አረጋገጠ።

ዳዊት ስግደቱንና ሱባኤውን ሲቀጥል፣ በሰውነቱ ውስጥ የታመቀው የሥርዓቱ መርዝ በሙሉ በሽንትና በላብ መልክ እየወጣ ተተካ። አሁን ዳዊት የሚመገበው ከመረቡ መርዝ የጸዳውን የተፈጥሮ በረከትና ጸበል ብቻ ነው። ሰውነቱ በመለኮታዊ ፎቶን (Photon) እየተሞላ ሲመጣ፣ የሰሎሞን ቀለበት ንዝረት በጣቶቹ ላይ መታየት ጀመረ። ይህ ንዝረት የአርከኖችን የዲጂታል ሴራ በአንዴ የማፍረስና የተቆለፉትን የጤና በሮች የመክፈት ኃይል አለው። ዳዊት አሁን የሥርዓቱ ተጎጂ መሆኑ አብቅቶ፣ የሥላሴ የብርሃን መሐንዲስ ሆኗል።

አሁን የመጨረሻው የንቃት ሽግግር ሰዓት እየቀረበ ነው። አባ መቃርስ ዳዊትን ወደ ፊት ጠርተውት፣ "ልጄ ሆይ፤ ዋካንዳ ሊቆጥረው የማይችለውና ሰላዮቹ ሊጠልፉት የማይችሉት አንድ የመጨረሻ ምስጢር ይቀራል፤ እሱም የ ፹፩ዱ (81) መጻሕፍት ፍጹም ንቃት ነው" አሉት። ዳዊት ለቀጣዩ ተጋድሎ ራሱን አዘጋጀ። የሥርዓቱ ግድግዳዎች በአማኑኤልና በዳዊት ጸሎት እየተናወጡ ነው። እውነት መቃብሩን ፈንቅላ ለመውጣት የታወጀው የንቃት ዘመን በኢትዮጵያ ተራሮች ላይ በይፋ ተጀምሯል ይቀጥላል ክፍል አራት .......

Post a Comment

0 Comments