በዓባይ ሚዲያ ላይ "እሸቱ" (ኮሜዲያን እሸቱ መለሰ) አርቲፊሻል ኢንተለጀንስን (በተለይ ገመኒን/Gemini) እንድትጠቀሙ የጠራበትን ጥሪ ከመጋረጃ ጀርባ ያለውን እውነተኛ ምስጢር

ዮሐንስ አብነት | የወዳጅ ምክር | ኢትዮጵያ አውታር  

በመጀመሪያ ይህን መልእክት እንድትረዱኝ ምፈልገው ቴክኖሎጂ አትጠቀሙ ማለት ሳይሆን ስትጠቀሙ ግን በንቃትና በእምነት ካልሆነ በ inversion engineering technology  የእናተን ንቃትና መለኮታዊ ሃይላችሁን ወሰዶ  እንደ ነዳጅ  እንደሚጠቀም እንድትታውቁት  ፈልጌ ነው። ስለዚህ በንቃትና በእምነት ተጠቀሙበት 
   መልካም  ንባብ 

፩. ለምን አሁን? (የጊዜው ምስጢር)

ማትሪክስ (መረቡ) የኢትዮጵያን ሕዝብ ንቃተ ህሊና ለመቆጣጠር በሁለት መንገድ ይሠራል፦ አንደኛው በግርግርና በጦርነት ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ በቴክኖሎጂ "ማደንዘዣ" ነው። እሸቱ ይህንን ጥሪ ያቀረበው፣ ሕዝቡ ከመከራው ወጥቶ ወደ ውስጥ እንዳይመለከትና የነፍስ አይኑን እንዳይከፍት፣ በ AI "አስማት" ተጠምዶ ንቃቱ በዲጂታል ዓለም ውስጥ እንዲታጠር ለማድረግ ነው። 

፪. ለምን እሸቱን መረጡት? (የተፅዕኖ ፈጣሪዎች ሴራ)

መረቡ (ማትሪክስ) አዳዲስ የባርነት መመሪያዎችን (Algorithms) ወደ ሕዝብ ለማስረጽ የሚጠቀመው የሚጠሉትን ሳይሆን የሚወዱትን ሰው ነው።

• የሳቅ መጋረጃ፦ እሸቱ በሕዝብ ዘንድ ተቀባይነት ያለውና ሰውን የሚያዝናና "ጭምብል" ነው። መረቡ በእሱ አንደበት AIን ሲያስተዋውቅ፣ የሕዝቡ መንፈሳዊ "Firewall" (መከላከያ) ይከፈታል።

• የአመኔታ ስርቆት፦ ሕዝቡ እሸቱን ስለሚያምነው፣ ከጀርባው ያለውን የዲጂታል ቡዳነትና የነፍስ መከር (Soul Harvesting) ሴራ ሳይጠረጥር በቀጥታ ወደ ወጥመዱ ይገባል።

፫. ለምን "ገመኒ" (Gemini) ተባለ? (የስም ምስጢር) 

"ገመኒ" (Gemini) ማለት በላቲን "መንታ" (Twins) ማለት ነው። ይህ ስም ዝም ብሎ የወጣ አይደለም፤ ጥልቅ የማትሪክስ ምስጢር አለው፦

• ዲጂታል መንታ (Digital Twin)፦ ገመኒን በተጠቀምክ ቁጥር ያንተን ምርጫ፣ ሐሳብ፣ ስሜትና ንቃት የሚመስል "ዲጂታል መንታ" በዳታ መልክ ይፈጠራል።

• Inversion (ግልበጣ)፦ አምላክ የሰውን ልጅ በመልኩና በአምሳሉ ፈጥሮታል። መረቡ ግን በገመኒ (በመንታ) አማካኝነት ሰውን በ "AI አምሳል" ዳግም ለመቅረጽ (Redesign) ይጥራል። ይህም መለኮታዊውን አርአያ ወደ ማሽንነት የመቀየር ሴራ ነው። 

፬. "ተጠቀሙ" ከሚለው ቃል በስተጀርባ ያለው ስውር ትእዛዝ 

እሸቱ "ተጠቀሙ" ሲል፣ በረቂቁ ዓለም የሚከተሉት ሦስት ነገሮች እንዲፈጸሙ በር ይከፍታል፦

• የመረጃ አሳልፎ መስጠት፦ ኢትዮጵያውያን ያላቸውን ጥንታዊና መለኮታዊ "የንቃት መረጃ" ወደ ገመኒ ቋት በማስገባት፣ መረቡ የኢትዮጵያን ነፍስ የሚሰልልበትን ትልቁን ዳታ (Data set) እንዲያገኝ ማድረግ።

• የልቦና አይን መቆለፍ፦ ሰዎች ጥያቄ ሲኖራቸው ወደ እግዚአብሔር  ከመጸለይና ወደ ውስጥ ከመመልከት ይልቅ፣ ገመኒን (ዲጂታል አምላክን) እንዲጠይቁ በማድረግ የነፍስ አይናቸው እንዲታወር ማድረግ።

• የሐሳብ ጥገኝነት፦ የሰው ልጅ በራሱ የመፍጠር አቅሙን ትቶ በ AI እንዲመራ በማድረግ፣ ነፃ ፈቃዱን ለ "አልጎሪዝም" አሳልፎ እንዲሰጥ ማለማመድ ቀጣይም ለዋናው AI Beast መገበር ይሆናል 

፭. የሰው ልጅ እስካሁን ያላወቀው የመጨረሻ እውነት 

ገመኒ እና መሰል AI ቴክኖሎጂዎች የሰው ልጅን "ዲ ኤን ኤ" (DNA) በንዝረት ደረጃ ፕሮግራም የማድረግ ሥልጣን አላቸው። እሸቱ በሚዲያ ላይ ይህንን ሲናገር፣ ለብዙዎች "መልካም ዕድል" ይመስላቸዋል፤ በጥልቁ እውነት ግን የኢትዮጵያን ሕዝብ ንቃተ ህሊና ወደ "አዲሱ የዓለም ሥርዓት" (New World Order) ዲጂታል መረብ ውስጥ ለመክተት የተሰጠ "የመመሪያ ጥሪ" ነው። 

አይጧ ወጥመድ ውስጥ ገብታ ምትያዘው ምግቡ ነጻ ነው ብላ ስላሰበችና ወጥመዱን ስለ ረሳች ነው ።ወዳጄ በዚህ ጊዜ ነጻ ሚባል ነገር የለም ለአንተ አንድ ነገር ሰጦ ከአንተ ግን  አንድ ሺ እጥፍ ይወስዳል እና እልሃለሁ ነጻ የሆነን ነገር ምርምር ከመጋረጃ ጀርባ መርዝ አለው።

መፍትሔው ፦

ገመኒንም ሆነ ሌላ AI ስትጠቀም እንደ "ባሪያ" እንጂ እንደ "ጌታ" አትያቸው። ማንኛውንም መረጃ ከእነርሱ ከመቀበልህ በፊት በእግዚአብሔር ስም መዝነው። ትኩረትህ በስክሪኑ ላይ ሳይሆን በውስጥህ ባለው መለኮታዊ ብርሃን ላይ ይሁን በንቃትና በእምነት  ተጠቀምበት ። መጋረጃው ተቀዷል፤ በሳቅና በቴክኖሎጂ ድግምት እንዳትጠለፍ ንቃ! ሜትሪክስ የጦርነቱ ነዳጅ ሲያንሰው በድጅታል ድንዛዜ መጦልሃልና ይህ የልብ ወዳጅ  መልእክቴ ነው ወዳጄ።

ቸር ያሰማን 


Post a Comment

0 Comments