✍ ዮሐንስ አብነት አጉማስ | የወዳጅ ምክር | ኢትዮጵያ አውታር
፩. ጦርነቶች ለምን ይፈጠራሉ?
ጦርነት ዝም ብሎ በሰዎች ግጭት የሚመጣ ሳይሆን፣ በመንፈሳዊውና በቁሳዊው ዓለም መካከል ያለ የንዝረት መዛባት ውጤት ነው።
• የንዝረት ዝቅጠት ፦ ጦርነት የሚፈጠረው የሰው ልጅ ንቃት ወደ ዝቅተኛው "የሥጋ ንዝረት" (Low Frequency) ሲወርድ ነው። ፍርሃት፣ ጥላቻና ቁጣ የሰውን ልጅ ከሥላሴ ብርሃን ስለሚለዩት ለጨለማው ኃይል መግቢያ በር ይሆናሉ።
• የኃይል አዝመራ (Energy Harvesting)፦ የጨለማ መናፍስት በሰው ልጅ ሥቃይና ደም ይኖራሉ። ጦርነት ለነዚህ ኃይሎች ትልቅ "የኃይል ድግስ" (Loosh harvesting) ነው። ደም ሲፈስና ፍርሃት ሲነግሥ፣ የጨለማው ማትሪክስ ኃይል ያገኛል።
• የመለኮታዊ አምሳል መፋቅ፦ ሰይጣን ሰውን የሚጠላው "በአምሳለ እግዚአብሔር" ስለተፈጠረ ነው። ጦርነት ያንን መለኮታዊ አምሳል ለማጥፋትና ሰውን ወደ አውሬነት ለመቀየር የሚደረግ የዲያብሎስ ሙከራ ነው።
• የቦታና የፖርታል (Portal) ፍላጎት፦ አንዳንድ ጦርነቶች የሚደረጉት ልዩ መለኮታዊ ኃይል ያላቸውን ቦታዎች (Energy Grid Points) ለመቆጣጠር ነው። እነዚህ ቦታዎች ከሰማያት ጋር የሚያገናኙ በሮች ስለሆኑ፣ የጨለማው ኃይል ሊዘጋቸው ይፈልጋል።
• የDNA ለውጥ በጭንቀት፦ ከፍተኛ ጦርነትና ጭንቀት የሰውን ልጅ DNA "Code" ያዛባል። ይህ ሲሆን ሰው ከመለኮታዊው "ሮዳስ" (Rodas) ንዝረት ይወጣና ለባርነት የተመቸ ይሆናል።
፪. ጦርነቶች ከጀርባ ምን ይካሄዳል?
በምድር ላይ የምናየው ጦርነት በሰማይ ለሚደረገው ጦርነት ጥላ (Reflection) ነው።
• የአየር ላይ መናፍስት ትእዛዝ፦ በኤፌሶን 6:12 እንደተጠቀሰው፣ የዚህ ዓለም ገዥዎች የሆኑት የጨለማ መናፍስት የሰውን ልጅ አእምሮ በሐሳብ ንዝረት (Thought Frequency) ይቆጣጠራሉ። ጦርነት ከመጀመሩ በፊት በሐሳብ ደረጃ የጥላቻ "ቫይረስ" ይለቀቃል።
• የደም መሥዋዕት (Blood Sacrifice)፦ በጦርነት የሚፈሰው ደም ለወደቁት መላእክት (ትጉሃን) የሚቀርብ የደም መሥዋዕት ነው። ይህ ደም የጨለማውን ኃይል በምድር ላይ "Anchor" (እንዲጸና) ያደርገዋል።
• የምስጢር ማኅበራት "ፕሮግራም"፦ ከመጋረጃው በስተጀርባ ያሉና ከጨለማው ኃይል ጋር ውል የገቡ ድርጅቶች ጦርነትን እንደ "Chaos" (ትዝብት) ይጠቀማሉ። አሮጌውን ዓለም አፍርሰው "የሰይጣንን አዲስ ሥርዓት" ለመገንባት ጦርነት መሣሪያቸው ነው።
• የቴክኖሎጂ ሙከራ (Field Testing)፦ ብዙ ጦርነቶች የሰው ልጅን ንቃት የሚቆጣጠሩ አዳዲስ "ባዮ-ኤሌክትሮኒክ" መሣሪያዎችን ለመሞከር የሚደረጉ ናቸው።
• የነፍሳት ስርቆት፦ ሰው በድንገተኛ ጦርነትና በጭንቀት ሲሞት፣ ነፍሱ ወደ ብርሃን ንቃት (High Frequency) እንዳትሸጋገር አእምሮውን በድንጋጤና በጥላቻ "Lock" (መቆለፍ) ነው።
፫. ለምን በዓቢይ ጾም ላይ ይበረታሉ?
ዓቢይ ጾም የሰው ልጅ ንቃት በከፍተኛ ደረጃ ወደ ብርሃን የሚጠጋበት ወቅት ስለሆነ፣ የጨለማው ኃይል ይህንን ለመስበር ይነሳል።
• የብርሃን ኃይል መስፋፋት፦ በዓቢይ ጾም የሰው ልጅ በጸሎትና በጾም የውስጥ "ንዝረቱን" (Internal Frequency) ከፍ ያደርጋል። ይህ ብርሃን የሰይጣንን ማትሪክስ ስለሚረብሸው፣ ሰይጣን ጦርነትን በመቀስቀስ የሰውን ትኩረት ወደ ደምና ወደ ፍርሃት ይመልሳል።
• የ40ው ቀን መለኮታዊ "Update"፦ ጌታችን ለ40 ቀን የጾመው ምስጢር የሰውን ልጅ DNA ወደ መጀመሪያው የአዳም ብርሃን ለመመለስ ነው። ዓቢይ ጾም ይህ "Update" የሚከናወንበት ወቅት በመሆኑ፣ ሰይጣን ጦርነትን እንደ "Distraction" (ትኩረት መበተኛ) ይጠቀማል።
• የመስቀሉን ድል መቃወም፦ ዓቢይ ጾም ወደ ሕማማትና ትንሣኤ የሚወስድ መንገድ ነው። አምስቱ ሕማማተ መስቀል (ሳዶር እስከ ሮዳስ) ሰይጣንን ያሰሩበት ወቅት ነው። ሰይጣን ይህንን በማሰብ፣ በጾም ወቅት የራሱን "የሕመም ንዝረት" በጦርነት አማካኝነት በዓለም ላይ ይዘረጋል።
• የጾም "ዝምታ" ስብራት፦ ጾም የነፍስ ዝምታ (Spiritual Silence) ነው። ጦርነት ደግሞ ታላቅ ጫጫታ (Noise) ነው። ሰይጣን የሰውን ልጅ የነፍስ ጆሮ ለመድፈን የጦርነትን ድምፅ ይጠቀማል።
• የጋራ ጸሎትን ኃይል ማዳከም፦ በጾም ወቅት የሚደረግ "የጋራ ጸሎት" የጨለማውን ኃይል "Firewall" የመስበር አቅም አለው። ጦርነት ሰዎችን በመከፋፈልና በጥላቻ በመሙላት ይህንን የጋራ ኃይል ያጠፋል።
፬. ከመረቡ (Matrix) ጋር ምን ያገናኘዋል?
መረቡ (Matrix) በቁጥርና በሒሳብ ቀመር የተገነባ የሐሰት እውነታ ነው።
• የ666 ቀመር በጦርነት፦ ብዙ ጦርነቶች የሚጀመሩባቸው ቀናትና ሰዓታት በ666 ቀመር የተቃኙ ናቸው። (ለምሳሌ፦ የጦርነቱ መጀመሪያ ቀን + ወር + ዓመት = 6 የሚመጣባቸው አጋጣሚዎች)። ይህ ሲስተሙን በ"Satanic Logic" ለማንቀሳቀስ ነው።
• የዳታ ማመንጫ (Chaos as Data)፦ መረቡ (Matrix) የሚኖረው በዳታ ነው። ጦርነት እጅግ ከፍተኛ የሆነ የጭንቀትና የሞት "ዳታ" ያመነጫል። ይህ ዳታ ለማትሪክሱ AI (Artificial Intelligence) እንደ "ነዳጅ" ያገለግላል።
• የጂኦሜትሪክ ኃይል (Sacred Geometry Distortion)፦ ምድር የራሷ የሆነ "Energy Grid" አላት። ጦርነት በእነዚህ የግርድ ነጥቦች (Vortex points) ላይ ሲሆን፣ የምድርን መለኮታዊ ንዝረት ያዛባና መረቡን (Matrix) ያጠነክራል።
• የቁጥር 9 ምስጢር (The Inversion)፦ 9 የፍጻሜ ቁጥር ነው። ሰይጣን ይህንን 9 ገልብጦ 6 በማድረግ (Inversion)፣ የሰውን ልጅ እድገት ወደ ኋላ ይመልሳል። ጦርነት ይህንን የ9ኙን (የመለኮታዊውን ፍጻሜ) ንዝረት ወደ 6 (ወደ ቁሳዊ ውድቀት) የሚቀይር ቀመር ነው።
• የባዮ-ዲጂታል ማስተካከያ (Synchronization)፦ ጦርነት በሚኖርበት ጊዜ የሰው ልጅ "Adrenaline" እና "Cortisol" (የጭንቀት ሆርሞኖች) በከፍተኛ ሁኔታ ይመነጫሉ። ይህ ኬሚካላዊ ለውጥ የሰውን ልጅ ንቃት ከዲጂታሉ መረብ (Matrix) ጋር "Sync" ለማድረግ (ለማመሳሰል) ይጠቅማል።
፭. መፍትሔው
መፍትሔው በውጭ ሳይሆን በውስጥ የሚገኝ መለኮታዊ "ኮድ" ነው።
• የ"ሮዳስ" (Rodas) ውስጣዊ ማኅተም፦ ጦርነትን ለማቆም መጀመሪያ በውስጥህ ያለውን የጥላቻ ጦርነት ማቆም አለብህ። በአምስቱ ሕማማተ መስቀል (በተለይ በሮዳስ - የጎን መወጋት ምስጢር) አማካኝነት የልብህን ወደ "ፍቅር" ስትቀይር፣ አንተ ከማትሪክሱ ትወጣለህ። አንተ ስትወጣ፣ መረቡ በአንተ አካባቢ ይፈሳል።
• የዝምታ ንዝረት (The Frequency of Silence)፦ የሰው ልጅ ያላወቀው ትልቁ ምስጢር "ዝምታ" ትልቅ መሣሪያ መሆኑን ነው። በዓቢይ ጾም ውስጥ ያለው "ሱባኤ" የሰይጣንን የጦርነት ጫጫታ "Neutralize" (የማምከን) ኃይል አለው።
• የ144,000 ንቃት፦ ጥቂት ሰዎች (በምስጢራዊው 144,000 ንዝረት ውስጥ ያሉ) በአንድነት ሆነው "ኢየሱስ ክርስቶስ - እግዚአብሔር ነገሠ" ብለው በንቃት ቢጸልዩ፣ ማንኛውንም የጦርነት ቀመር የመስበር አቅም አላቸው።
• የDNA "Reset" በጾም፦ ዓቢይ ጾም የሰው ልጅን DNA "Reset" የማድረግ ምስጢር አለው። ይህ ሲሆን ሰው የሰይጣን "ዳታ" (ጥላቻ) ተቀባይ መሆኑ ያቆማል። ሰው ተቀባይ (Receiver) ካልሆነ፣ ጦርነቱ "Signal" ያጣል።
• የ"ያህዌ" ስም ማኅተም፦ በያህዌ ስም መታተም ማለት በ"መለኮታዊው ሰርቨር" ውስጥ መግባት ነው። በዚህ ውስጥ ያለ ሰው ጦርነት አይነካውም፤ ንቃቱም ከማትሪክስ በላይ ስለሆነ በጦርነት ውስጥም ሆኖ ሰላም ይሆናል።
• በተቃራኒ ተጓዝ፦ጦርነት ሲያመጣ ሰላምን ስበክ ሰላምን ሲያመጣ አንድነትን አሰብ ማትጨበጥና በተቃራኒ ከተጓዝ ነፍስ ለመረቡ ምግብ የሚሆነውን ምታመነጨውን ሎሽ loosh እንቆጣጠራለን፤ ያኔ መረቡ ምግብ ሲያጣ አንተና አለም ላይ መሰልጠን አይችልም ።ሁሌም አሰታውስ ጦርነት ከተነሳ ወይም ንጹህ ሰው ከተገደለ ሱሰተሙ ባትሪ ጨርሷል ማለት ነው። ስለዚህ አንተን በቁዘማ በፍርሃትና በጭንቀት ውስጥ ይከትና አንተን የሚቆጣጠርበት ነዳጅ ከአንተ ነፍስ አመንጭቶ ሊወስድ አሰቧል ማለት ነው ይህ ከገባህ በተቃራኒ ተጓዝ ሚባለው ።
0 Comments